www.maledatimes.com የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ቴድሮስ ሃጎስ የወያኔ ስርዓት አልበኝነት ማሳያ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ቴድሮስ ሃጎስ የወያኔ ስርዓት አልበኝነት ማሳያ

By   /   December 19, 2012  /   Comments Off on የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ቴድሮስ ሃጎስ የወያኔ ስርዓት አልበኝነት ማሳያ

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 11 Second

 “አርቲስት ታማኝ በቅርቡ ሲናገር ‘የትግራይ ህዝብ እኮ በሪፈረንደም ህወሓት የኔ ብቸኛ ወኪል ነው ኣላለም’ ሲል ሰምተናል። ታማኝ በየነ ልክ ብሏል። እኛ ደግሞ የምንለው የትግራይ ህዝብ ወያኔን ካንጀቱ ካወጣውና ከጠላው ዓመታት ተቆጥሯል ነው።” – መምህር፣ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ

* * * * * *

በጀርመናዊው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንትና በዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ የተፈጠረውን እሰጥአገባ ከሳምንታት በፊት ዘግባችሁ እንደነበር እናስታውሳለን።

አቶ ቴድሮስ ሃጎስ የወያኔ ህወሓት የፕሮፓጋንዳ ሃላፊ የኢፈርት

/ ትእምት ቦርድ ሰብሳቢ የክልሉ ፕሬዚደንት የፖለቲካ አማካሪ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ እንደሆኑ ልብ በሉና ለምን ትምህርት ሚንስቴር እንኳን እንደሚፈራቸው ግን ታህሳስ 8/2005 ሪፖርተር ጋዜጣ ይዞት የወጣውን ዜና ማየት ብቻ በቂ ነው/http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/8883-2012-12-15-11-48-47.html/

ኮረም ኣልሞላም ተብሎ የዩኒቨርሲቲው ፕረዘደንት የጠየቁትን በሶስት ወራት ውስጥ ያልመለሱት አቶ ቴድሮስ አብረው የሚጠጡትና የሚሰርቁት በእንደ አቶ ንጉሰ ገብረ የመቀሌ ከንቲባ ስብሰባዎችን እንዲያስተጓጉሉ በማድረግ ነው። በተለያየ ጊዜ ኮረም አልሞላም እያሉ ስብሰባዎችን የሚያስተጓጉሉት እነ አቶ ቴድሮስ ተራው ህዝብን ግን ነጋ ጠባ

የመለስ ራእይንለማሳካት እያሉ ፕሮፓጋንዳ ያናፋሉ። ባለፈው ጉባኤያቸው ወንበዴዎቹ የኛ ዓላማ እጥፍቶ መጥፋት ነው ብለዋል!ይጥፉ ወይስ እንጥፋ ነው ጥያቄው?እንዳሉት ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም እንጠጣ ወይስ ዩኒቨርስቲው በስርዓትና በህግ ይገዛ ነው ጥያቄው ለኤርትራዊው አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ተስፋይ። አቶ ቴድሮስ መጠጥና ብክነትን እና ትውልድን መግደል መርጠዋል።

ለወራት ቦርድ እንዲሰበስብላቸውና አዲስ ሹመትን እንዲያፀድቅላቸው ሲማፀኑ የቆዩትን ፕረዚደንት ኸርዚግ ህግ ተላልፈሃል ብለው ለማባረር ይችሉ ዘንድ

TPLF ፕሮፓጋንዳ ሃላፊው ቴድሮስ ሃጎስ ትምህርት ሚንስቴር ውስጥ ባለው የበላይ ባለሟላቸው ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ሚንስትር ዲኤታ በኩል የላኩዋቸው አቶ ሰለሞንና ወልደገብርኤል የተባሉ ሁለት ተላላኪዎች ፕረዜደንቱን ገምግምሉን ሊሉን ከች አሉ በዚህ ሳምንት።

በዶ

/ር ክንደያ ገብረህይወት የምርምር ምክትል ፕረዚደንት አማካኝነት የተሾሙት ዲኖች /ህጉ የሚለው ሁሉም ስታፍ ምርጫ አድርጎ ሲያበቃ ምክትል ፕርዚደንቱ የዩኒቨሲቲው ፕረዚደንትን በማማከር ያሾማል ቢሆንም / ፕረዚደንት ኸርዚግ ይውረዱሉን ሲሉ ለተላላኪዎቹ እንደተናገሩ በምፀት ሰምተናል። ዲኖቹ በደሞዝ ሊሰሩዋቸው የማይችሉ ቪላዎችና በየከተማው የንግድ ቤቶችና ትላልቅ የጭነት ማመላለሻ መኪኖች ሊኖርዋቸው የቻሉት ከዶ/ር ክንደያ ጋር እና እርሱ ከመሰረተው የአቶ ቴድሮስ የሙስና ሰንሰለት ተጠቃሚ በመሆናቸው በፕረዚደንት ኸርዚግ ህጋዊ ጥያቄ መደናገጣቸው አያስገርምም።

በሚልዮኖች የሚቆጠር የመንግስትንና የህዝብን ገንዘብ ያባከነው ምክትል ፕረዚደንት ዶ

/ር ክንደያ ገብረሂወት እንኳንስ ሊገመገም ይቅርና የድርጅቱ ጉባኤ በመጪው ጥር ይሁን የካቲት ወር ሲደረግ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ይሆን ዘንድ በአሁኑ ጊዜ አቶ አዲሱ ለገሠ በሚመሩት የወያኔ ኢህአዴግ ‘’የበላይ አመራር ስልጠና’’ የሶስት ወር ስልጠና እየተሰጠው እንደሆነ ታውቋል።

አቶ ቴድሮስ ሃጎስ በየእለቱ ከዶ

/ር ክንደያ ገብረሂወት ጋር የሚጋቱት መጠጥና የሚጫወቱባቸው እንስቶች እየታወሱዋቸው ዶክተሩን ለቀናት እንኳን ከዓይናቸው እንዲለያቸው የሚሳሱለትን ሰው ጀርመናዊው ፕሮፈሰር ሲሹሩባቸው እንዴት ሆዳቸውን ባርባር አይላቸውም ትላላችሁ?

ለዚህም ነው ፕረዚደንቱን እንዲያስገመግሙላቸው በረጅሙ እጃቸው ዶ

/ር ካባ ኡርጌሳ በተባለው የጅማ ዩኒቨርሲቲ እውቅ ሌባ የነበረው ያሁኑ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ በኩል ሁለት የትምህርት ሚንስትር ተላላኪዎች መላካቸው።

ህገመንግስቱን ጥሰው ከሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮች ጋር በማዳበል ስልጣናቸው እንደጉም ያበነነባቸው አቶ ደመቀ መኮንን በምን እዳቸው ቴድሮስ ሃጎስን ይሞግታሉ? አንተ ደመቀ ወንበር እንጂ ስልጣን መች ሰጠንህ ቢሉዋቸውስ

?

ወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት አልበኝነቱ በሁሉም መስክ ገጥጦ የሚታይ እውነት ቢሆንም መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚታየው ሙስናና ስርዓት አልበኝነት ደግሞ ልዩ ባህርይ ያለው

‘’ምርጥ’’ ምስክሩ ነው።

አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ለሶስት ወራት ደጅ ያስጠኑዋቸውን የአዲስ ምክትል ፕረዚደቶች ሹመት ጊዜው ሲደርስ ፕረዚደንቱ በመሾማቸው የተቆጡትን ያህል ዶ

/ር ክንደያ የተባለው የአካዳሚክ ምክትል ፕረዚደንት ያለምንም ምርጫ ፕረዚደንቱ ሳያውቁ በአቶ ቴድሮስ አይዞህ ባይነት አብረውት የሚሰርቁ ወይም ሲሰርቅ የማይቃወሙ ዲኖችን እንደሚሾም ይታወቃል።

በቅርብ በጀርመናዊ ፕረዚደንት ጥረት ከተመረጡት ሁለት ወይም ሶስት ዲኖች በቀር ሁሉም ዲኖች ዶ

/ር ክንደያ በየመሸታቤቱ ሆኖ የመረጣቸው ዲኖች እንደሆኑ በሁሉም ትምህርት ኮሌጆች ያሉ ስራተኞች የሚያውቁት ፀሃይ የሞቀው እውነት ነው።

አዳዲስ ዲኖች በህጉ መሰረት በምርጫ መሆን አለበት ብለው ጀርመናዊ በመሟገታችውና ዶ/ር ክንደያን ከሹመቱ ስለተገዳደሩት እንግዳው ሰውዬ ከትምህርት ሚንስትሩ ዶ

/ር ካባ ኡርጌሳና ቦርድ ሰብሳቢው ቴድሮስ ሃጎስ ብዙ ያልተገባ ዘለፋ እንደደረሳቸው በምሬት ሲናገሩ ይሰማል።

የመቀሌ ህዝብማ በአቶ ቴድሮስ ሃጎስ ላይ ምስክርነቱን ከሰጠማ ዓመታት አልፎታል

በ

1992 E.C በተደረገው ምርጫ ለክልል ምክር ቤት ወያኔ ኢህአዴግ በመቀሌ ከተማ Tedros hagos ለውድ ድር ሲያቀባርቸው ይህ ሰው ሰካራም ነው፣ ይህ ሰው ሴሰኛና አጥፊ ነው ብሎ ህዝቡ ኡኡ ቢልም ፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ በትእቢት ስየ አብርሃን በተጠየፈ እንደበቱ ቴድሮስ ሓጎስ ፖሊት ቢሮ እንዲሆን ሽንጡን ገትሮ ተማጉትዋል።

እንደ ቴድሮስ ሓጎስ ያለ ብኩን እንደ ቴድሮስ ሓጎስ ያለ ሰካራምና ሴሰኛን የሚሸከም

TPLF የተባለ ድርጅት እንደምን የትግራይ ህዝብ ወኪል ሊሆን ይችላል?

አርቲስት ታማኝ በቅርቡ ሲናገር

‘’የትግራይ ህዝብ እኮ በሪፈረንደም ህወሓት የኔ ብቸኛ ወኪል ነው ኣላለምሲል ሰምተናል። ታማኝ በየነ ልክ ብሏል። እኛ ደግሞ የምንለው የትግራይ ህዝብ ወያኔን ካንጀቱ ካወጣው ና ከጠላው ዓመታት ተቆጥሯል ነው።

በመጨረሻም ኢሳት ቲቪና ሬድዮ የታማኝ በየነ ክፍል አንድ ካየን በሁዋላ በጣም እየታፈነ እንደሆነ ልንገልፅላችሁ እንወዳለን።

ሞት ህዝብን እያማረሩና በህዝብ እየነገዱ ለሚኖሩ ሰካራሞች!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on December 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: December 19, 2012 @ 5:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar