www.maledatimes.com ይድረስ ለደመራ ሪስቱራንት ባለቤት አቶ ግርማይ እና ወ/ሮ ትእግስት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ለደመራ ሪስቱራንት ባለቤት አቶ ግርማይ እና ወ/ሮ ትእግስት

By   /   May 6, 2013  /   Comments Off on ይድረስ ለደመራ ሪስቱራንት ባለቤት አቶ ግርማይ እና ወ/ሮ ትእግስት

    Print       Email
0 0
Read Time:18 Minute, 7 Second

የሰው ልጆች ክብር እንደሚገባቸው ሁሉ ክብርን መስጠት ልማዳችን ነው ሆኖም ግን ክብርን በጅምላ የመግፈፉ ባህሪ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በዚሁ የምግቤት አስተዳደር መገፈፉ አግባብ አለመሆኑን እያየን እኛ የችካጎ ነዋሪዎች ዝምታን መርጠን ተቀምጠናል ይኼውም የሆነበት የኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባህርይ ስለተጠናወተን ብቻ ነው ።

ይህንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ በትላንትናው እለት የፋሲካ በአልን አስመልክቶ በተከናወነው የበአል አከባበር እና የቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ፕሮግራም እኔን እና ሌሎች የችካጎ ህብረተሰብን እርር ድብን አድርጎ ስላበሳጨን ሃሳባችንን በነጻነት ሊተገበርበት በሚችለው መገናኛ ብዙሃን መጻፉ እና እውነታውን ለሌሎችም በማጋራት ጥፋትኛውን እርማቱን እንዲያስተካክል መምከር ተገቢ ሆኖ ስለታየን ወደ ዋናው አላማችን ልመጣ ወሰንን ።

በ$20.00 መግቢያ ዋጋ በመክፈል የምግብ ቤቱን አዳራሽ ሞልቶት የነበረው ታዳሚው በጊዜ ሙዚቃው ይጀምራል ተብሎ ሲጠባበቅ የነበረው ገና በጊዜ ቢሆንም የተጀመረው በሁለት ሰዎች ፉጨት ምክንያት ከለሊቱ 1፡22 ደቂቃ ላይ ነበር ከዚያ በፊት ግን ለጆሮ ሊሰሙ አይደለም ቢሰሙም ሊቆረቁሩ በሚችሉ ሙዚቃዎች ዲጄ በተባለችው ሴት ሲቀርብ ጊዜውን ሊደሰትበት የመጣው ሰው ሁሉ ከመዝናናት እና ከመደሰት ይልቅ ከያዘው ጠርሙስ ጋር መሳሳምን የመረጠ ታዳሚ እንደነበር ለመረዳት ተችሎአል ። እውነትም ታዳሚው ትእግስት ያለው ሰው መሆኑን እና አክብሮቱ ትልቅ የሆነ የችካጎ ህዝብ አስመስጋኝ መሆኑን ያሳየበት ሲሆን ታጋሽነቱ ገንዘቡን ከፍሎ መዝናናትን ሲመርጥ መገፋትን መርጦ ዝምታን የተቀበለ ህዝብ እንደሆነ አየሁ ።

በመጀመሪያ ደረጃ ደመራ ምግብ ቤት የምግብ እና የአልኮል መሸጥ ፈቃድ ከኢልኖይ ስቴት የተፈቀደለት ህጋዊ ድርጅት ቢሆንም ሙዚቀኛን አስመጥቶ በክፍያ ማስመጣት እያስከፈለ ለማሳየት የሚያስችል የማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን Event Promoters Ordinance license አውጥቶ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስ ድርጅት አይደለም ።

ሆኖም ግን ህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን ይዞ ስለሚንቀሳቀስ ብዙውን ጊዜ  የሚዝናናበት በእራሱ ዜጋ በከፈተለት የመዝናኛ ቦታ መሆኑ የሚያስገርም እና  ይበልጥ ይበል የሚያሰኝ ነገር ነው ። ታዲያ የፕሮሞሽን ፈቃድ የሌለው ሰው ወይንም ግለሰብ ወይንም ድርጅት በህገወጥ መልኩ ሲሰራ ቢገኝ በአገሪቱ ህግ መሰረት ህግን የሚተላለፍ ሰው ምን ሊያስቀጣው እንደሚች መገመት አያዳግትም ። ነገር ግን የምግብ ቤቱ ሙዚቀኞችን አስመጥቶ በነጻ ለምግብ ቤት ታዳሚዎቹ  ማዝናናት እንደሚችል ግልጽ ነው  ያለ ምንም ክፍያ ማለቴ ነው ። ሆኖም ግን ከፍተኛ የኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ በማይታይባት ችካጎ ግን ሁሉንም በአንድ ስራ ላይ እንዲሆን እድሉን ፈጥራዋለች እና ህብረተሰቡም ይህንን እድል እንዲጠቀሙ በማድረግ ግብዣውንም ተቀብሎ እድሉንም ሰጥቶ በአንድነት የሚጓዝበት ትልቅ ጎዳና ፈጥሮ ይጓዛል ።

ስለዚህ እንዲህ አይነቱ ህብረተሰብ ወደ ነጋዴው በቀረበ ጊዜ ነጋዴው ደግሞ በንቀት እየተመለከተው እና የደንበኛውን ብቻ ብር እየተመለከቱ ማስተናገዱ ተገቢ ባይሆንም ይህንን ሁሉ ችግር አይቶ የሚስተናገደው ጸባየ ሰናይ የሆነው ኢትዮጵያዊ ዛሬ ግን ያንገፈገፈው ይመስላል ።  ምክንያቱም በምድረ አሜሪካ አንድን የአሜሪካ ዶላር ለመስራት ምን ያህል ድካም እንዳለው የሚረዳው በትንንሽ ስራዎች ተጠምዶ ዶላሮችን የሚለቅመው ሰው ብቻ ነው እንጂ እንዲህ በቀላሉ የህብረተሰብን ገንዘብ ይሄን አምጥቼልሃለሁ ብሎ ከ እጁ ላይ እንደሚዘርፈው ወይንም እንደሚነጥቀው ነጣቂ በአንድ ጊዜ አጋብሶ እንዳልሆነ ጠንቅቆ መረዳት የሚገባ ይመስለኛል ። ከአንድ ሰው የተወሰደው 20 የአሜሪካ ዶላር የሶስት ሰአት ጉልበት ፈሶበት እንደመጣ የደመራ ባለቤቶች ተረድተውታልን ነው ወይስ ልክ እነርሱ እንደሚያስቡት እና ከሰዎች በአቋራጭ እነደሚመነጭቁት የአቋራጭ ጎዳና ለህብረተሰቡም ያለ ይመስላቸው ይሆን ?

ወደ ዋና መዘርዝሩ እንግባ እና በትላንትናው እለት የተደረገው ይሄው የሙዚቃ ድግስ ቅድሞውኑ ዝግጅቱ ምንም ዝግጅት ያልነበረው ቢሆንም ከሙዚቃ መሳሪያ እጥረት እና የቴክኒክ ችግር ጀምሮ እስከ ዘፋኞች መራበሽ ወይንም የሙዚቀኛ እና ሙዚቃ መሳሪያ አለመጣጣም እስከ ድርጅቱ ባለቤት የአንድ ሰአት የሙዚቃ ድግስ አጨዋችነት የሚከናወኑት ቴትሮች ትላንት ከትላንት ወዲያ ታይተው የነበሩት ችግሮች ተሻሽለው ዛሬ ቀረቡ ስንል ብሰው መምጣታቸው ነጋዴውን ከንግድ ማእከሉ ይውጣ እና ሌላ ሰው ንግዱን ይያዘው የሚል እትብት አስቆራጭ ቃላቶች ውስጥ እስከመግባት እና መደምደሚያ ሃሳብ እስከመፈለግ ድረስ የሚያስኬድበት መንገድ መቆፈር የተደረሰ ይመስላል የህበረተሰቡን ስሜት ከሙዚቃው ድግስ ጀርባ ።

የደመራ ምግብ ቤት ባለቤት አቶ ግርማይ ግን ለድርጅቱ ህልውና ሳይሆን የገንዘቡን አቋራጭ ማየት መልካም ባይሆንም  ግን ህብረተሰብን ማክበር ግን ባህላችን  ቢሆን መልካም ነው።

በአንድ ወቅት በዚሁ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ነጠቃ ይካሄድ እንደነበር አስታውሳለሁ ሂደቱም እንዲህ ይከናወን ነበር ፤-አንድ ሰው የአልኮል መጠጥ መጠጣቱ ሲታወቅ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ እንቁላል  መስተንግዶው በእንክብካቤ ይዥጎደጎድለታል ከዚያም በመጠጥ ናላው መዞሩ ሲታወቅ የአምስት አልኮል መጠጥ ሁለት እጥፍ ተጨምሮበት ክፍያው ጣሪያ ይሰቅል ነበር ። ለዚህም ምስክርነቱ እኔው እራሴው ስሆን ከቅርብ ጓደኞቼ ጋር በመሆን የአንደኛውን የጓደኛችንን ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ እናት አገር ምድሩ ለመሄድ ሻንጣውን ሲያሰናዳ እኛም ለሃገርህ ያበቃህ አምላክ ይመስገን ብለን የሽኝት ጠረጴዛችንን በዚሁ ምግብ ቤት በማድረግ የደስታችንን ጊዜ ለመጋራት በህበረት ጉዞ አደረግን ከዚያም የሚኪና አሽከርካሪነት እጣው እኔ ላይ ወደቀ እና ምንም አልኮል እንዳልቀምስ ተነገረኝ ያንንም አደረኩ የአጠቃላይ የመጠጥ ሂሳቡንም ቁጥጥር በእኔ እጅ ስር ወደቀ ይህም ሆኖ ሳለ እያንዳንዳችን ያዋጣነውን ገንዘብ በመሰብሰብ የአልኮል መጠጦች እንዲወርዱ ትእዛዝ ሲፈጸም አንድ ሄነሲ እና አንድ ብላክ ሌብል በቅድሚያ የአፍ ማሟሻ ተብሎ ቀምቃሚዎቹ ቅምቀማቸውን ሲቀመቅሙ እኔ ታዛቢ ሆኜ የለስላሳ መጠጥ አብሬ መዝናናትን ጨዋታ ማምጣት  ትውስታ መፍጠርን የግሌ ሆኖ የመድረኩ አጋፋሪያቸው ሆንኩ ።

በስተ መጨረሻም የታዘዘው ሁለቱ መጠጥ ሳያልቅ በደረቅ አልኮል ሁሉም አቅሉን ስቶ በስካር መንተባተብ ጀመሩ ይህንን ያዩት የቤቱ አስተናጋጆች የመጠጡ ዋጋ ተመን $450.00  መድረሱን ዜናውን አበሰሩን እንዴት ብለን ስንጠይቅ ከመካከላችሁ አንዱ ለሌሎችም ግብዣ ጋብዞአል የሚል መልስ መጣ “እኛም የምናውቀው ይሄንን ብቻ ነው ስንል እሱ እዚህ ላይ ሂሳቡን ጨምሪ ብሎአል በማለት የሌባ አይነ ደረቅ ሆና ቁጭ አለች ልጁም ሲጠየቅ ምንም እንደማያውቅ እና ለማንም ግብዣ እንዳላደረገ መናገሩን ልብ እላለሁ።

ይሄም አልበቃ ያለን ተስተናጋጆች በአጠቃላይ በኢትዮጵያኖች ምግብ ቤቶች ውስጥ የመስተንግዶ አናሳነትን አስተውለን እና ከባለቤት ጀምሮ እስከ አስተናጋጅ በነጭ እና በጥቁር እንዲሁም በኢትዮጵያዊያኖች ላይ ያለው የመስተንግዶ እና የሰላምታ ልዩነትን  አይተን “ተው ቻለው ሆዴ “ ብለን ከመግባት አልተቆጠብንም  ።ብንችልማ ኖሮ ድራሻችን እስኪጠፋ ድረስ እልም ብለን በጠፋን እና ምግቤቶቹን ሁሉ ባላየን ምንኛ ደስታ በዋጠን ነበር ።ምን ዋጋ አለው እንጀራ አፈር ይብላ  እንዲህ የሚያንከራትተን ሆዳችን ውስጥ ዘሩን ዘሮብን ያልበቀለውን ዘር ፍለጋ ወይንም የበቀለውን ዘር አጨዳ ለመሄድ አይደለምን ?።

በመጨረሻም የሙዚቃ ዝግጅቱ የተጀመረው  በበዛወርቅ አስፋው የትዝታ ዘፈን ሲሆን ከአምስት ዘፈን ሳትዘል አንድ ዘፈን እስራኤል በመዝፈን ሙዚቃው እንዲጠናቀቅ ተደረገ ከምሽቱ 2፡31 ደቂቃ የዉጡልኝ መብራት ጠፋ ከዚያ በፊት የነበሩት የኤሌትሪክ መቋረጦች የሙዚቃውን ውበት አጥፍቶት ወይ ሃያ ብሬ እያሰኘን በነበረበት ወቅት ውጡልኝ የሚለው የባለቤቱ ዝማሬ ሌሎቻችንን ለብስጭት ዳረገን ዳግም ላንገባ ቃለ መሃላ ገብተን ተለያየን እናንተስ ብለን ለሌሎቻችን ደግሞ ለማስተጋባት ወሰንን ከዚያ በፊት ግን ባለቤቶቹስ ምን ምላሽ ይሰጡን ይሆን ብለን መጠየቅን ወደድን እና እስኪ ለችካጎ ህዝብ ምን ትሉታላችሁ ይቅርታን ትጠይቃላችሁ ወይንስ ገንዘቡን ትመልሳላችሁ ወይንስ በሌላ መድረክ በሙዚቃ ድግስ ነጻ ታዝናኑታላችሁ መልሳችሁን ብናደምጥ ምን ይመስላችኋል? ስለዚህ ነጋዴ እና ህብረተሰብ መለያየት የለበትም እና ከገንዘብ ይልቅ ደንበኞችን ማካበት ይቅደም የሚለውን መፈክራችንን በማሰማት እለያችኋለሁ ።በየልብ ላይ እንደሚቀርቡት አስተያየቶች የእኛም ብ እሮች እንደጦር ይዋጋሉ እና ሃሳባችንን መሰንዘራችን የወደፊት የቀጥተኛነት ምእራፋችሁ እንዲስተካከል ያደርጋል እና እባካችሁ እንታረም ።ዘላለም ገብሬ

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 6, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 6, 2013 @ 11:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar