www.maledatimes.com የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው

By   /   December 5, 2013  /   Comments Off on የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 39 Second
source FBC 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው።

ተከሳሾቹ  አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።

ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም  የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ።

መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።

ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ  ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው  የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው።

አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና  ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310  ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል።

26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥  በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ  እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው።

ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን  መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።

ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ  ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል።

ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል።

ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።

እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል።

1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል።

2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ  በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ  ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።

3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።

ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።

የአቶ ወልደስላሴ የረዥም ጊዜ ጓደኛ እንደሆነ የሚነገርለት 4ኛው ተከሳሽ ዶሪ ከበደ አቶ ወልደስላሴ በቤተሰቦቹ ስም በሚስጥር የያዘውን ከፍተኛ ሃብት ይዞ በማቆየት የወንጀል ተሳትፎ አድርጓል ነው የሚለው ክሱ።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ንብረትና ገንዘብ ለማፍራት የሚያስችል ምንም አይነት አቅም ሳይኖራቸው በፈጸሙት ምንጩ ያልታወቀ  ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

ከአቶ ወልደስላሴ እና ከወንድማቸው በስተቀር ወይዘሪት ትርሃስ እና አቶ ዶሪ የዋስትና መብት ጥያቄ አቀርበው ፥ ከሳሽ አቃቤሀግ የተመሰረተባቸው ክሰ ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ በህጉ መሰረት የዋስትና መብት ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ቅዋሜ አቅርቧል።

ግራ ቀኙን የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነወው እንዲከታተሉ በመወሰን ፤ የክስ መቃወሚያቸውን ለመስማት ለታህሳስ 7   2006 ዓ.ም ተለዋጨ ቀጠሮ ይዟል።

 

በጥላሁን ካሳ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 5, 2013 @ 6:24 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar