www.maledatimes.com የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ (ማንዴባ)ከዚህ አለም በሞት በ95 አመታቸው ተለዩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ (ማንዴባ)ከዚህ አለም በሞት በ 95 አመታቸው ተለዩ

By   /   December 5, 2013  /   Comments Off on የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ (ማንዴባ)ከዚህ አለም በሞት በ 95 አመታቸው ተለዩ

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 1 Second

ታላቁ የአፓርታይድ አርበኛ የጥቁርህዝብ መመኪያ የሆኑት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕረዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ህይወታቸው ዛሬ ጠዋት በደቡብ አፍሪካ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 4 ሰአት ላይ ማለፉን መረጃዎች ሁሉ ሲዘግቡት ውለዋል ። ማንዴላ በአፓርታይድ ስርአት ህዝብን ለአመጽ ቀስቅሰሃል በሚል የእድሜልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው 27 አመታትን በእስራት ካሳለፉ በኋላ ከእንግሊዙ የዘረኝነት አፓርታይድ ስርአት አስተዳደር መሪዎች ጋር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሰላማዊ መንገድን በመጠቀም ችግራቸውን ፈተው ለተቀረው ዘመናቸው አንቱ የተባሉ እና በማይጠፋ አሻራ ስማቸውን በክብር ያስቀመጡ የአፓርታይድ የነጻነት ታጋይ በሚል ስያሜ ትልቅ ክብር የተሰጣቸው ሰው እንደሆኑ ዛሬ አለም እየዘከራቸው በሚገኘው በህልፈተ ህይወታቸው ቀን ሲታወስ ውሎአል ።ኔልሰን ማንዴላ ዘረኛውን የደቡብ አፍሪካ መንግስት በመቃወማቸው ለ27 ዓመት እስር ቤት ማቀዋል። ከእስር ቤት እንደተለቀቁም የመጀመሪያዋ የነጻይቱ የደቡብ አፍሪካፕሬዚዳንት ሊሆኑ በቅተዋል ።

እንደ አጋጣሚ ከተለያዩ የሶሻል ኔትዎርኮች ያገኘናቸውን የሰዎችን አሰተያየቶች ለመቃረም ሞክረናል የህዝብ እይታዎችን ይመልከቱ ።ናቲ ማን የተባለው ወጣት በማለዳ ታይምስ ፌስ ቡክ ላይ ባሰፈረው መልእክት መሰረት ስንጀምር Nati Man ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው አፍሪካ የመንፈስ አባት ቢባሉ የማይበዛባቸው የዘጠና አምስት አመቱ ማንዴላ ዛሬ ህይወታቸው አለፈ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ብቻ አይደለችም መላዋ አፍሪካ፤ አፍሪካ ብቻም አይደለችም ጠቅላላ አለም እጅግ አሳዛኝ ዜና ሲል በሀዘን ጥቁር ለብሶ መርዶውን እያዳረሰ ይገኛል፡፡ ማንዴላ የዛሬን አያድርገውና “ሽብርተኛ” ተብለው ለ27 አመታት በእስር ቤት የተዘጋባቸው ሰው ነበሩ፡፡ ነገር ግን የሰሩትም የታሰሩትም ሞገስ የሚያስገኝ በመሆኑ አለም ሁሉ ሊያሞካሻቸው ቃላት ሲያጥረው አይተናል፡፡ ሽብርተኛ ተብሎ የታሰረ ሁሉ ፤ ሽብርተኛ ቢባል ኖሮ ዛሬ አለም እስራቸውንም ስራቸውንም አያቆላመጠ እኔ አፈር ልብላልዎ አይልላቸውም ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደ ማንዴላ ስለ ነፃነት በመጮሃችሁ ታሰራችሁ አበሳ የምታዩ ያገሬ ልጆችን አስባችሁ ዘንድ ግድ ይለኛል፡፡ ማንዴላ ቀጥታ ወደ ገነት እንደሚሄዱ ባውቀውም ነፍስዎን በገነት ያኑራት ማለት ደንብ ነው እና እላለሁ… መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን! አሜን! በቀጣዩ ደግሞ በኔልሰን ማንዴላ የፌስቡክ ፔጅ ላይ ይህንን አንብበናል Nelson Mandela
“Death is something inevitable. When a man has done what he considers to be his duty to his people and his country, he can rest in peace. I believe I have made that effort and that is, therefore, why I will sleep for the eternity.” ~ Nelson Mandela 1996 Hamba Kahle Tata

የሲፒጄ (cpj)የአፍሪካ ፕሮግራም ተጠሪ የሆነው መሃመድ ኬታ በፌስቡክ ፔጅ ላይ ይህንን ሲል ተናግሮአል Asim Keita Nelson Mandela was not a saint, but he dedicated his life to add to the freedoms of others, at the expense of his own. He wrestled with the worst impulses of humanity and confronted inhumanity with the best qualities of Man. Hamba Kahle #Madiba! In our hearts, you will live forever and in those still struggling for freedom and justice around the world, your indomitable spirit.የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍልም የተሰማንን ልባዊ ሃዘን ለተከበሩ የአለም የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እረፍትን  እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲሆን እንመኛለን !እርስዎም ታላቅ ሰው ነበሩ !obit_frame_Nelson_Mandela_1918_2013_v31x13_12x5_992
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 5, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 5, 2013 @ 8:25 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar