www.maledatimes.com ኦ ማዲባ ========= - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኦ ማዲባ =========

By   /   December 6, 2013  /   Comments Off on ኦ ማዲባ =========

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 58 Second


የአፍላነትህ ትጋት – የጉልምስናህ ሩጫ
የመፃጉነትህ ሞገስ – የሕይወትህ ምሉዕ ዋንጫ
የዕድሜ ዘመንህ ጉዞ – የሽምግልናህ ፀጋ
የመከራህ ሁሉ መከር – የመስዋዕትነትህ ዋጋ
በክብር መዝገብ ላይ ሰፍሮ – በወርቅ ቀለም ተፅፎ
———– ለታሪክ ለትውልድ አልፎ
ሕያው ነው ለዘላለሙ -በእምነት በፍቅር ገዝፎ፡፡

ህያው ነው አንፀባራቂ – ለግፉአን ሰዎች ሁሉ
የሰውነት መብት ተነፍገው – በድቅድቅ ጨለማ ላሉ
በህሊና ለታወሩ
ክብራቸውን ላነወሩ
ሳይኖርን ኖርን ለሚሉ – እያዩ ግን ለማያዩ
ለነዚህ ለነዚያም ሁሉ – የብርሃን ሞገስ ሆነሃል
ለዕድሜ ሙሉ ትጋትህ – የክብር ዘውድ ይገባሃል፡፡

ኦ! ማዲባ ይገባሃል – የክብር አክሊል መድፋት
ተፈትኗል በመከራ – የዕውነትህ የእምነትህ ፅናት፤
ብትሞትም – የክብር አክሊል – የፍቅር ዘውድ ተቀዳጅተህ
ሽበት ውበት በቸረው- ብርማ ፀጉርህ ላይ ደፍተህ
መቼም የፍቅር ነገር – እያደር ለሚመራቸው
“ስለፍቅር ነው መፅደቄ – ህይወቴም ፍቅር” በላቸው
አንተ ነህ መምህራቸው፡፡

አዎ ማዲባ እውነትን – ያለመታከት ሰብከሃል
የሰብዓዊነት ዝማሬህ – እስከአርያም ድረስ ናኝቷል
ዓይነ በሲሩን ህሊና – ጨለማውን ሁሉ ገልጧል
የፍቅርን መስቀል ታቅፈህ – ሮቢን ደሴት ወርደሃል
ደክምህ፣ ዝለህ፣ ቀልጠህ ነደህ – ቤዛ ሆነህ ተገኝተሃል
በምድር ላይ የማይከስም – ህያው ታሪክ አኑረሃል፡፡

ማንዴላ የእውነት አባት – ዛሬ በአካል ብትለይም
ታሪክህ ለአፅናፈ ዓለም – ከቶም በምድር አይከስምም፡፡
ሕያው ነህ ለዘላለሙ – ኖርክ እንጂ ሞትክ አይባልም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 6, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 6, 2013 @ 9:35 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar