www.maledatimes.com ዱርዬ መልክ የለውም ( ሪያድ ኢብራሂም) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዱርዬ መልክ የለውም ( ሪያድ ኢብራሂም)

By   /   December 10, 2013  /   Comments Off on ዱርዬ መልክ የለውም ( ሪያድ ኢብራሂም)

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 55 Second

የየትኛውም ሀገር መንግስት ሀገሩን የሚመራበት ኢኮኖሚያዊ ዘዴ አለው ከነዚህ ዘዴዎች ውስጥም አብዛኛው ሀገራት የሚጠቀሙበት ማርኬት ኢኮኖሚ ኮማንድ ኢኮኖሚ ትራዲሽናልኢኮኖሚ እናም ሚክስድ ሲሆኑ የኛሀገር የምትከተለው ደግሞዱርዬአዊ ይባላል። ምክንያቱም የወያኔ አደረጃጀት ከላይ እስከታች በዝምድና በዘር በማንአለብኝነት የተዋቀረስለሆነነው። ምክንያቱም የወያኔ መንግስት አንድ ዱርዬ ግለሰብ ያለውን ባህሪ ሙሉ በሙሉ ያሟላ በመሆኑነው። ልብ ብዬ መንግስታችንን ሳስበው አንዳንድ በአካል የማውቃቸውን ዱርዬዎችን ያስታውሰኛል። ዱርዬ አላማ የለውም፣ይዘርፋል፣ ሰውይገድላል፣ገድሎም ቤተሰብ ይበትናል፣የሀገር ጉዳይ አያሳስበውም፣ ለራሱና ለመሰሎቹ ከማሰብ ሌላ የሚደንቀውም የሚጨንቀውም ነገር የለም። ለዚህ ሁሉ ጥፋቱም አንድም ጊዜ እራሱን የሚወቅስበት ህሊና የለውም።የተጠያቂነት ስሜትም የለውም።ታዲያ ይሄ የዱርዬ ባህሪያት መንግስታችን       አያሟላም ትላላችሁ?

ከወያኔኣዊ ባህሪያት አንደኛው፦ ከዘሮቹ አልፎ ለተቀሩት ዜጎች አልፎ የሚያስብበት ጊዜ እንደሌለው በተደጋጋሚ አሳይቶናል። ስንት ወንድምና እህቶቻችን ናቸው ለፍተውና ተግተው ተምረው ከወያኔ ባለመወለዳቸው ስራ አጥ የሆኑት። ከዚህ በተቃራኒው ብዙም ሳይለፉ መጠነኛ ኮርስ ብቻ ወስደው ከወያኔ በመወለዳቸው ብቻ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የተቀመጡት። ከሁሉ የሚያሳዝነውም ለተቀመጡበት የስልጣን እርከን ሙያዊ ብቃት ስለሌላቸው የሚያደርሱት ሀገራዊ ጥፋትም ጭምር ነው።

ሁለተኛው፦በግድ የለሽነትና በማን አለብኝነት ጥንት አባቶቻችን አጥንቶቻቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው እንደ ሀገር ያቆሟትን ሀገር ያለማመንታት መሬታችንን ቆርሰው ለጎረቤት ሃገራት  ሰጥተዋል።

ሶስተኛው፦ ማንኛውንም ተቀናቃኝ በሃይል እያሳደዱ ከእነደብዛ ማጥፋት መለያቸው ከሆነ ከርሟል። ግርም የሚለው ተቃዋሚዎቻቸውን አጥፍተው ሲያበቁ ባገኙት አጋጣሚ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ብለው መደስኮራቸው ነው ።በመሳሪያ ከሆነ አዎ የለም በጠርጴዛ ዙሪያ ከሆነ ግን በእጥፍ የሚያስከነዳ ሞልቷል እላለሁ ።

አራተኛው፦ውሸት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ስለሆነ ከጠዋት እስከማታ ሚድያቸውን(ኢቲቪ) በመጠቀም ነፍስ ያላወቁ ህጻናትን ውሸት ያስተምራሉ።ነፍስ ያወቀውማ ምን ሲደረግ የእነሱን በሬ ወለደ ይሰማል። ታዲያ ትውልድን ውሸት ከማስተማር የበለጠ ምን ጥፋት    ይኖራል!

  አምስተኛው፦አድርባዮቻቸውን ውሻዊ ባህሪ ማላበስ የዱርዬዎች መለያ ባህሪ ነው። ዋናው ዱርዬ ከበታቹ ያሉትን ሲሻው እንደ ውሻ ሲያዝ እነሱም በበኩላቸው  ሲታዘዙ ን

ጹሃን ዜጎችን ንከሱም ሲላቸው ያለማመንታት ሲነክሱ ይኖሩና እርሱም ማዘዝ የሰለቸው እለት እራሳቸውን ነክሶ ይጥላል። ለዚህም ምስክር ይሆነን ዘንድ በርካታ አድርባዮችን መጥቀስ ይቻላል።ለጊዜው ግን እነ ጁነዲን ሳዶ፣ መላኩ ፋንታ ማየት በቂ ምስክር ነው። የቀን ጉዳይ ነው እንጂ እነ ኩማ ደመቅሳ፣አባዱላገመዳ፣ደመቀ መኮንን እና ሌሎችም መሰል ተግባራት ላይ ያሉ ተራቸውን የሚጠብቁ አድርባዮች መሆናቸው ግልጽ ነው።

 

በዘረፋ ከተባለም በርትተው ሀገሪቷን በራቁት ለማስቀረት ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ። ገደብ ያጣ ዝርፊያቸውን ያስረዳ ዘንድ በዋናነት ለሀገሪቱ የገቢ ምንጭ የሆኑትን ከቡና፣ ከተለያዩ ማዕድናት፣ ከቆዳ፣ ከአበባ፣ በዕርዳታ ስም ወደ ሀገር ቤት የሚገባው ገንዘብ የት እንደሚገባ መጠየቅ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳሉት ቀዩዋን መስመር እንደ ማለፍ ይቆጠራል። ተቆጥሮም አይቀር ሽብርተኛ ያሰኛል። ግድ የለም ሂሳቡን የሀገሪቱ ቁልፍ ህዝብ  እጅ ሲገባ በጋራ የምናወራርደው ይሆናል።ሀዘኔ ግን በየጊዜው በወያኔ ክንድ እየተደቆሱ ለመሬት ግብአት ለዋሉት ወገኖቻችን ነው።የተነጠቀን ህይወት ማስመለስ አይቻልምና።

ምክንያቱም ይህ የሽፍታ ቡድን ሀገሪቱን ወደ እድገት ጎዳና የመምራት ቅንጣትታህል ፍላጎት እንደሌለው በተለያዩ አጋጣሚዎች አሳይቶናል። እስከሚገባኝ ድረስ የዜጎችእድገት ማለትየ ሀገር እድገት ማለትነው። ለወያኔ ግን ይሄ የገባው አይመስለኝም ምክንያቱም የዜጎች ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ህዝቦችዋ በረሀብ እና በጥማት በሚኖሩባት ሀገር ባለበት ወቅት ወያኔ ግን ኢኮኖሚያችን ፩፩ ዲጂት አድጓል ሲል ቅንጣት ታህል አያፍርም።ለነገሩ ሽፍታ ወንበዴ እኮ አያፍርም።ሀገር እኮ ማለት ሕዝብ ነው ። ሕዝብ ደግሞ ከተራበ ሀገሪቱዋ አደጋ ላይ ናት ማለት ነው።  ወንበዴ አላማየለውም፣ ከዘላቂ ነገር ይልቅ ለጊዘያዊ ፍላጎቱ ሙሉ ጊዜውን ይሰዋል፣የገዛ ድርጊቱ እንኩዋን ለሰው ለራሱ ግልጽ አይደለም፣ ጉዞ ሲጀምር የሚያደርሰውን ቦታ አያውቅም፣ ተስፋን አያውቅም፣ መረጋጋትን አልፈጠረበትም፣ ህሊና የለውም፣ ሁሉን በእጁ ማድረግ ይሻል፣ ሁሉን በሃይል ማዘዝ ይቀናዋል፣ የሰውን ሃሳብ ማድመጥ ለሱ ሽንፈት ነው፣ የንጹሃን ደም ለሱ ቧልት ነው ፣መዝረፍ ለሱ ተራ ነገር ነው፣የሻውን ነገር ለታይታ ወይም ለመመፃደቅ ብቻ ያለ እቅድ እና ፍላጎት ጊዜና ገንዘቡን ያፈሳል። የሰው ልጅ ከነዚህ ባህሪያቶች ውስጥ አንዱ ወይም ሁለቱ ሊኖረው ይችላል ወንበዴ ግን ይህን ሁሉ ባህርያት በጅምላ ይይዛል። ለዚህም ነው ዱርዬ መልክ የለውም ያልኩት። ዱርዬውን መንግስታችንን ልብ ብላችሁ ከታዘባችሁት የሚሰራው ነገር ለራሱም  ግልጽ አይደለም፣እየሄደበት ያለው መንገድ የት እንደሚያደርሰው አያውቅም፣ሀገሪቱዋ የህዝብ በመሆን ፈንታ ሁሉን ነገር ያለ ገደብ በእጃቸው ሲያደርጉት አይተናል፣ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ እና ትኩረታቸው ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ የምዕራብ ሀገራትን ልብ ለመግዛት አገልግሎት የሚውል ሀሰተኛ ዲሞክራሲ ማካሄድ ላይ ብቻ ነው።ታድያ ይሄ ዱርዬ መንግስትአይደለም ትላላችሁ ? በስተመጨረሻም ወያኔን ሊገባው ከቻለ አንድ ምክር እመክራለው ህዝብን ሁልጊዜ ማታለል ማዋከብበ ሀይል መያዝ አይቻልም። ስለዚህም ከወዲሁ እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ የትም አያደርሳችሁምና ቆም ብላችሁ በጥሞና ብታስቡበት መልካም ይመስለኛል። ህዝብ በቃኝ ያለ ዕለት ማንም እንደማያቆመው ከተለያዩ በአምባገነን ሲተዳደሩ ከቆዩ ሀገራት ተመክሮ መውሰድ ብልህነትነው። በእነኚህ ሀገራት የተከሰተው አይነት አሰቃቂ የዕርስ በዕርስ ጦርነት ያየነውን በሀገራችን እንዳላይ ነው ጸሎቴ።መንግስት የያዘውን መንገድ የሙጥኝ ካለ ግን ውጤቱን መገመት አያዳግትም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 10, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 10, 2013 @ 3:13 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar