www.maledatimes.com “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” (በወሰን ሰገድ ገብረኪዳን) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“በሕግ አምላክ መልሱልኝ” (በወሰን ሰገድ ገብረኪዳን)

By   /   December 10, 2013  /   Comments Off on “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” (በወሰን ሰገድ ገብረኪዳን)

Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 45 Second
በ1950ዎቹ አጋማሽ በኋላ በብዕራቸው ሃያልነት የተነሳ በሕዝብ ዘንድ (በተለይም በተማረው ወገን ዘንድ) አድናቆትን ያተረፉ፤ በአንፃሩ ደግሞ በወቅቱ መንግስት አሣራቸውን ሲጨምቁ ከነበሩ የሥነፅሁፍ ሰዎች መሃል አንዱ ነው፡፡ ይህ ሰው በፅሁፎቹ ትንታግነት የተነሳ በተለያየ ወቅት ከዩኒቨርስቲ ትምህርቱ እንዲታገድ ተደርጓል፡፡ በተለያየ ወቅት ወደ እስር ቤት ተግዟል፡፡ ተደብድቧል፡፡ መኖሪያ ቤቱ ተበርብሮ በርካታ የሥነፅሁፍ ሥራዎቹ ተወስደውበታል፡፡ “ዘለፋና ማነሳሳት” የሚል ክስ ተመስርቶበት ፍ/ቤት እንዲገተር ተደርጓል፡፡ ወዘተ፡፡ይህም አልበቃ ብሏቸው፤ የመንግስት ልሣን በሆኑት መገናኛ ብዙሃን (አዲስ ዘመንና ኢትዮጵያ ሄራልድ) “መርዘኛው ፀሐፊ” የሚል ቅፅል ሥም ተሰጥቶት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሄዶበታል፡፡
“His poisen-pen letters and anti-social activities were the work of a mischief and mis-guided individual …. His surreptitious vilifications were quite haphazard and generally misanthropic…….” ተብሎ ተፅፎበታል፡- በ1960 ዓም፡፡

“መርዘኛ” የተባለው ደራሲ “ገሞራው” በተሰኘው የብዕር ሥሙ ገናን ዝና ያተረፈው ባለቅኔ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ ነው፡፡ እናም በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተባለውን እንዲህ ሲል ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሶት ነበር፡-
“…. የሚፅፈው በተንኮል መርዝ የተሞላ ፅሁፍ በጠቅላላ ግብረ-ሰብን የሚቃወም ነው፡፡ …የሚፅፋቸው መርዛማ ፅሁፎቹ በጠቅላላ የሚያስረዱት ማንኛውንም ሰው የሚመለከተው በጥላቻ መንፈስ ብቻ መሆኑን የሚገልፁ ናቸው፡፡…..”

አሁን ቃል በቃል ልከትበው ባልችልም በዚያው “መርዘኛ” በተባለበት ወቅት “መርዝ” የተሰኘ ግጥም ፅፎ እንደነበር ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ከዚህ ግጥሙ ሁሌም ትውስ የሚለኝ ሁለት መስመር (ስንኝ)አለ፡፡
“…..መርዝን በመርዝነት – ስለመርዝ መመረዝ
የመርዙን በመርዙ – መልሶ ማስመረዝ፡፡…..”

የሆነ ሆኖ ዛሬ የማወራው ስለ ግጥሞቹ ምጡቅነትና ጠልቀት አይደለም፡፡ ስለደራሲው ሙግት አይታክቴነት እና “አስደናቂ” ድፍረት እንጂ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ በወቅቱ የነበረው መንግስት (ሥርዓት) የማይጠበቅ “ትሁትነት” ጭምር ነው የደነቀኝ፡፡

እርግጥ ነው፤ በወቅቱ የነበረው ስርዓት አምባገነንነት የሚያነጋግር አይደለም፡፡ በታሪክ የተመዘገበ ነውና፡፡ ሆኖም በወቅቱ “ነውጠኛ” ብሎ የፈረጀው ባለቅኔ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) የተደጋጋሚ በመንግስት ኃይሎች ቤቱ ተበርብሮ የተወሰዱበት በርካታ የሥነፅሁፍ ስራዎች እንዲመለስለት የጠየቀበት “ በሕግ አምላክ መልሱልኝ” በሚል ርዕስ የፃፈው ደብዳቤ በ“አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ነው የገረመኝ፡፡

ይህም ብቻ አይደለም የደነቀኝ፡፡ በወቅቱ “የሕዝብ ጸጥታ ጥበቃ መ/ቤት” ይባል የነበረው የአምባገነኑ ሥርዓት ተቋም ደራሲው ገሞራው ላቀረበው ጥያቄ በሣምንቱ በወጣው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ የፅሁፍ ምላሽ መስጠቱ ጭምር ነው የደነቀኝ፡፡ እኔ እንደገባኝ ወይም እንደተረዳሁት “የሕዝብ ፀጥታና ጥበቃ መ/ቤት” ማለት በአሁን ዘመን “የደህንነት መ/ቤት” ማለት መሰለኝ፡- ካልተሳሳትኩ፡፡

የደህንነት መ/ቤት ለአንድ ደራሲ፤ ለዚያውም እንደ በግ ደጋግሞ እያሰረ ለፈታው “ነውጠኛ” ብዕረኛ፤ ሥራዬ ብሎ የፅሁፍ ምላሽ መስጠቱ፤ ምላሹም በአዲስዘመን ታትሞ እንዲወጣ ማድረጉ ነው “ሥርዓቱ እንዲህ ትሁት ነበር እንዴ?” ብዬ እንድጠይቅ ያስገደደኝ፡፡ ለማንኛውም ደራሲው ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” ሲል ያቀረበውን አቤቱታ እንዳለ ላስነብባችሁ፡፡

“በሕግ አምላክ መልሱልኝ”
ክፍት ደብዳቤ፡፡

ሀ/ ለሕዝብ ጸጥታ ሚኒስቴር ባለሥልጣኖች፤ (መስፍን ሐረር መንገድ)
ለ/ ለካቢኔ መ/ቤት ባለሥልጣኖች፤ (ካዛፖፖላሬ ሠፈር)
ሐ/ ለፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባለሥልጣኖች (አ/አ)፤

ከዚህ በላይ የተጠቀሳችሁት ክፍሎች እንደምታስታውሱትና ከሞላ ጎደልም ብዙ ሰዎች እንደምታውቁት ሁሉ ባለፉት አስር አመታቶች ውስጥ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በየጊዜው በወንጀለኝነት በመከሰስ በኢትዮጵያዊነቴ የማልጠብቀው ከፍተኛ በደልና ታላቅ መንገላታት ደርሶብኛል፡፡ “ማንኛውንም ሰው በጥላቻ የሚመለከት የሰው ልጆች ጠላት ነው” እስከመባል ድረስ ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነቴን ጭምር የሚነኩና የሚያዳቅቁ ድርጊቶች ሲፈጸሙብኝ መኖራቸውን የሚያውቁ ወገኖች ሁሉ ይመሰክሩልኛል፡፡

አንድ ሦስት ጊዜ ያህል (ጥቃቅኑን ሳልቆጥር) አለአግባብ በታሰርኩበት ወቅት ከደረሱብኝ በደሎች ዋና ዋናዎቹ በሞራሌ ላይ የደረሰብኝ የማይጠገን ሥብራትና በአካላዊ የጤንነት ይዞታዬ ላይ ያስከተለብኝ የማይሽር ደዌ ይገኙበታል፡፡ በማምንባቸው እውነቶቼ መንስዔነት የደረሱብኝ የሚያሰቅቁ አደጋዎች በመሆናቸው፤ ምንም እንኳ በሕግ ያልተደገፉ ድርጊቶች እንደሆኑ ባውቅም ካሣ አልጠይቅባቸውም፡፡ እስከዛሬ ድረስ በፀጋ የተቀበልኳቸውን ያህል ወደፊትም ለመቀጠል አልሰለችም፡፡ ዘመኑ ያለፈበት የከረከሰ መሣርያ መርምሮ የሚያስገኘውን የከረከሰ ውጤት (ቢፈቀድልኝ እፅፍበታለሁ) ድጋፍ በማድረግ በሳይንስ ያልተደገፈ ከዱላ አንስቶ እስከስቅላት ድረስ ባለው ልዩ ቅጣት “ወንጀለኝነትህን እመን” ብሎ ማሰቃየትና ማስጨነቅ በኢትዮጵያዊነቴ ቀርቶ በሰብአዊነቴ የማልጠብቀው ነበር፡፡ በዚህ ረገድ የገጠመኝን ልዩ ትዝታ ከሞቴም በኋላ ግዑዝ አጥንቴም ሲያስታውሰው እንደሚኖር ምንጊዜም ይሰማኛል፡፡ በትምህርቴ እንኳ የደረሰብኝን በደል ሁሉ ዕድሜ ይኑር እንጂ በእርጅናዬም ዘመን ቢሆን በመማር እንደምወጣው አምናለሁ፡፡

ምንም እንኳ በአሁኑም ጊዜ “ዘለፋና ማነሳሳት” በሚል ወንጀል ተከስሼ በዝግ ችሎት ስንቃቃና ስንከራተት ሁለተኛ ዓመቴን በማገባደድ ላይ ያለሁ ብሆንም፣ በይበልጥ እየቆጨኝና እየቆጠቆጠኝ የሔደው በየጊዜው ሕገወጥ በሆነ መንገድ የተወረስኳቸው የሥነፅሁፍ ክምችት ቅርሶቼ ናቸው፡፡ ለኢንተርናሽናል የሥነፅሁፍ ደረጃ ብቃት ይኖራቸዋል ብዬ የማምንባቸው እንደ “ሚጋክራሲ” ያሉ ኖቭሎቼ፣ እንደ “የስሜት ዓለም” ያሉ ቲአትሮቼ፣ እንደ “የበሰለው ያራል” ያሉ ቁጥር የለሽ ግጥሞቼና የመሳሰሉት ሥነፅሁፋዊ ቅርሶቼ በየጊዜው ተወስደውብኛል፡፡ (ሦስት ጊዜ ከመኖሪያ ቤቴ በብዙ ሰዎች በሸክም ለመወሰዱ ምስክሮች አሉኝ) በመሠረቱ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 43 እና 61 ዘረፋው አግባብ አልነበረም፡፡ ለሦስት ጊዜ ያህል ከሕግ ውጪ በሆነ መንገድ የተወረስኩት የጽሁፍ ክምችት በገንዘብ ቢተመን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስገኝ አልጠራጠርበትም፡፡ እነዚህ ሁሉ ጽሁፎቼ ከመወረሳቸው በፊት ለሁለተኛ ሰው ተላልፈው ያልተሰጡ በመሆናቸውና የሐሳብ ነፃነት (ፍሪደም ኦፍ ዘ ማይንድ) በመኖሩ እንደ ፅንሰ-ሐሳብ በመቆጠራቸውም፣ በአብዛኞቹ አልተከሰስኩባቸውም፡፡

አሁንም ከላይ የጠቀስኳቸውን የጽሁፍ ቅርስ አስገዳጅ ወራሾቼን የምጠይቀው ብዙ ንትርክ ውስጥ ሳንገባ የወሰዱብኝን የሥነ ጽሁፍ ከምችት እንደመልሱልኝ ነው፡፡ ለእውነት፣ ለፍትሕና ለነፃነት አቤቱታዬን አቅርቤ ከምፋረዳችሁ በፊት በልመና መልክ “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” ብሎ መጠየቁ ኢትዮጵያዊ አቀራረብ መሰሎ ስለታየኝ በዚች ክፍት ደብዳቤ በታላቅ አክብሮትና በከፍተኛ ትህትና እንድትመልሱልኝ እጠይቃለሁ፡፡

ይህ የገሞራው (ኃይሉ ገ/ዮሐንስ) አቤቱታ ግንቦት 27 ቀን 1966 ዓ.ም በታተመው መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ላይ ለንባብ የበቃ ነው፡፡ ለዚህ የደራሲው አቤቱታ በወቅቱ “የሕዝብ ጸጥታና ጥበቃ መ/ቤት” የተባለው ተቋም የሰጠው ምላሽ ሰኔ 8 ቀን 1966 ዓም ለንባብ በበቃው አዲስዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል፡፡ የደህንነት ተቋሙ የሰጠውን ምላሽ ደግሞ ሌላ ጊዜ አቋድሳችኋለሁ፡፡

እስከዚያው “ብዙ ንትርክ ውስጥ ሳንገባ” ምናምን በሚሉት የገሞራው ደፋር አገላለፆች ተደመሙ፡፡

==== “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” =====

በ1950ዎቹ አጋማሽ በኋላ በብዕራቸው ሃያልነት የተነሳ በሕዝብ ዘንድ (በተለይም በተማረው ወገን ዘንድ) አድናቆትን ያተረፉ፤ በአንፃሩ ደግሞ በወቅቱ መንግስት አሣራቸውን ሲጨምቁ ከነበሩ የሥነፅሁፍ ሰዎች መሃል አንዱ ነው፡፡ ይህ ሰው በፅሁፎቹ ትንታግነት የተነሳ በተለያየ ወቅት ከዩኒቨርስቲ ትምህርቱ እንዲታገድ ተደርጓል፡፡ በተለያየ ወቅት ወደ እስር ቤት ተግዟል፡፡ ተደብድቧል፡፡ መኖሪያ ቤቱ ተበርብሮ በርካታ የሥነፅሁፍ ሥራዎቹ ተወስደውበታል፡፡  “ዘለፋና ማነሳሳት” የሚል ክስ ተመስርቶበት ፍ/ቤት እንዲገተር ተደርጓል፡፡ ወዘተ፡፡

ይህም አልበቃ ብሏቸው፤ የመንግስት ልሣን በሆኑት መገናኛ ብዙሃን (አዲስ ዘመንና ኢትዮጵያ ሄራልድ) “መርዘኛው ፀሐፊ” የሚል ቅፅል ሥም ተሰጥቶት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሄዶበታል፡፡

“His poisen-pen letters and anti-social activities were the work of a mischief and mis-guided individual …. His surreptitious vilifications were quite haphazard and generally misanthropic…….”  ተብሎ ተፅፎበታል፡- በ1960 ዓም፡፡

“መርዘኛ” የተባለው ደራሲ “ገሞራው” በተሰኘው የብዕር ሥሙ ገናን ዝና ያተረፈው ባለቅኔ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ ነው፡፡ እናም በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተባለውን እንዲህ ሲል ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሶት ነበር፡-

“…. የሚፅፈው በተንኮል መርዝ የተሞላ ፅሁፍ በጠቅላላ ግብረ-ሰብን የሚቃወም ነው፡፡ …የሚፅፋቸው መርዛማ ፅሁፎቹ በጠቅላላ የሚያስረዱት  ማንኛውንም ሰው የሚመለከተው በጥላቻ መንፈስ ብቻ መሆኑን የሚገልፁ ናቸው፡፡…..”

አሁን ቃል በቃል ልከትበው ባልችልም በዚያው “መርዘኛ” በተባለበት ወቅት “መርዝ” የተሰኘ ግጥም ፅፎ እንደነበር ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡  ከዚህ ግጥሙ ሁሌም ትውስ የሚለኝ ሁለት መስመር (ስንኝ)አለ፡፡

“…..መርዝን በመርዝነት -  ስለመርዝ መመረዝ

የመርዙን በመርዙ - መልሶ ማስመረዝ፡፡…..”

የሆነ ሆኖ ዛሬ የማወራው ስለ ግጥሞቹ ምጡቅነትና ጠልቀት አይደለም፡፡  ስለደራሲው ሙግት አይታክቴነት እና “አስደናቂ” ድፍረት እንጂ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ በወቅቱ የነበረው መንግስት (ሥርዓት) የማይጠበቅ “ትሁትነት” ጭምር ነው የደነቀኝ፡፡

እርግጥ ነው፤ በወቅቱ የነበረው ስርዓት አምባገነንነት የሚያነጋግር አይደለም፡፡ በታሪክ የተመዘገበ ነውና፡፡ ሆኖም በወቅቱ “ነውጠኛ” ብሎ የፈረጀው ባለቅኔ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) የተደጋጋሚ በመንግስት ኃይሎች ቤቱ ተበርብሮ የተወሰዱበት በርካታ የሥነፅሁፍ ስራዎች እንዲመለስለት የጠየቀበት “ በሕግ አምላክ መልሱልኝ” በሚል ርዕስ የፃፈው ደብዳቤ በ“አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ነው የገረመኝ፡፡

ይህም ብቻ አይደለም የደነቀኝ፡፡ በወቅቱ “የሕዝብ ጸጥታ ጥበቃ መ/ቤት” ይባል የነበረው የአምባገነኑ ሥርዓት ተቋም ደራሲው ገሞራው ላቀረበው ጥያቄ በሣምንቱ በወጣው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ የፅሁፍ ምላሽ መስጠቱ ጭምር ነው የደነቀኝ፡፡ እኔ እንደገባኝ ወይም እንደተረዳሁት “የሕዝብ ፀጥታና ጥበቃ መ/ቤት” ማለት በአሁን ዘመን “የደህንነት መ/ቤት” ማለት መሰለኝ፡- ካልተሳሳትኩ፡፡

የደህንነት መ/ቤት ለአንድ ደራሲ፤ ለዚያውም እንደ በግ ደጋግሞ እያሰረ ለፈታው “ነውጠኛ” ብዕረኛ፤ ሥራዬ ብሎ የፅሁፍ ምላሽ መስጠቱ፤ ምላሹም በአዲስዘመን ታትሞ እንዲወጣ ማድረጉ ነው “ሥርዓቱ እንዲህ ትሁት ነበር እንዴ?” ብዬ እንድጠይቅ ያስገደደኝ፡፡ ለማንኛውም ደራሲው ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” ሲል ያቀረበውን አቤቱታ እንዳለ ላስነብባችሁ፡፡

“በሕግ አምላክ መልሱልኝ”

ክፍት ደብዳቤ፡፡

ሀ/ ለሕዝብ ጸጥታ ሚኒስቴር ባለሥልጣኖች፤ (መስፍን ሐረር መንገድ)

ለ/ ለካቢኔ መ/ቤት ባለሥልጣኖች፤ (ካዛፖፖላሬ ሠፈር)

ሐ/ ለፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባለሥልጣኖች (አ/አ)፤

ከዚህ በላይ የተጠቀሳችሁት ክፍሎች እንደምታስታውሱትና ከሞላ ጎደልም ብዙ ሰዎች እንደምታውቁት ሁሉ ባለፉት አስር አመታቶች ውስጥ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በየጊዜው በወንጀለኝነት በመከሰስ በኢትዮጵያዊነቴ የማልጠብቀው ከፍተኛ በደልና ታላቅ መንገላታት ደርሶብኛል፡፡ “ማንኛውንም ሰው በጥላቻ የሚመለከት የሰው ልጆች ጠላት ነው” እስከመባል ድረስ ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነቴን ጭምር የሚነኩና የሚያዳቅቁ ድርጊቶች ሲፈጸሙብኝ መኖራቸውን የሚያውቁ ወገኖች ሁሉ ይመሰክሩልኛል፡፡

አንድ ሦስት ጊዜ ያህል (ጥቃቅኑን ሳልቆጥር) አለአግባብ በታሰርኩበት ወቅት ከደረሱብኝ በደሎች ዋና ዋናዎቹ በሞራሌ ላይ የደረሰብኝ የማይጠገን ሥብራትና በአካላዊ የጤንነት ይዞታዬ ላይ ያስከተለብኝ የማይሽር ደዌ ይገኙበታል፡፡ በማምንባቸው እውነቶቼ መንስዔነት የደረሱብኝ የሚያሰቅቁ አደጋዎች በመሆናቸው፤ ምንም እንኳ በሕግ ያልተደገፉ ድርጊቶች እንደሆኑ ባውቅም ካሣ አልጠይቅባቸውም፡፡ እስከዛሬ ድረስ በፀጋ የተቀበልኳቸውን ያህል ወደፊትም ለመቀጠል አልሰለችም፡፡ ዘመኑ ያለፈበት የከረከሰ መሣርያ መርምሮ የሚያስገኘውን የከረከሰ ውጤት (ቢፈቀድልኝ እፅፍበታለሁ) ድጋፍ በማድረግ በሳይንስ ያልተደገፈ ከዱላ አንስቶ እስከስቅላት ድረስ ባለው ልዩ ቅጣት “ወንጀለኝነትህን እመን” ብሎ ማሰቃየትና ማስጨነቅ በኢትዮጵያዊነቴ ቀርቶ በሰብአዊነቴ የማልጠብቀው ነበር፡፡ በዚህ ረገድ የገጠመኝን ልዩ ትዝታ ከሞቴም በኋላ ግዑዝ አጥንቴም ሲያስታውሰው እንደሚኖር ምንጊዜም ይሰማኛል፡፡ በትምህርቴ እንኳ የደረሰብኝን በደል ሁሉ ዕድሜ ይኑር እንጂ በእርጅናዬም ዘመን ቢሆን በመማር እንደምወጣው አምናለሁ፡፡

ምንም እንኳ በአሁኑም ጊዜ “ዘለፋና ማነሳሳት” በሚል ወንጀል ተከስሼ በዝግ ችሎት ስንቃቃና ስንከራተት ሁለተኛ ዓመቴን በማገባደድ ላይ ያለሁ ብሆንም፣ በይበልጥ እየቆጨኝና እየቆጠቆጠኝ የሔደው በየጊዜው ሕገወጥ በሆነ መንገድ የተወረስኳቸው የሥነፅሁፍ ክምችት ቅርሶቼ ናቸው፡፡ ለኢንተርናሽናል የሥነፅሁፍ ደረጃ ብቃት ይኖራቸዋል ብዬ የማምንባቸው እንደ “ሚጋክራሲ” ያሉ ኖቭሎቼ፣ እንደ “የስሜት ዓለም” ያሉ ቲአትሮቼ፣ እንደ “የበሰለው ያራል” ያሉ ቁጥር የለሽ ግጥሞቼና የመሳሰሉት ሥነፅሁፋዊ ቅርሶቼ በየጊዜው ተወስደውብኛል፡፡ (ሦስት ጊዜ ከመኖሪያ ቤቴ በብዙ ሰዎች በሸክም ለመወሰዱ ምስክሮች አሉኝ) በመሠረቱ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 43 እና 61 ዘረፋው አግባብ አልነበረም፡፡ ለሦስት ጊዜ ያህል ከሕግ ውጪ በሆነ መንገድ የተወረስኩት የጽሁፍ ክምችት በገንዘብ ቢተመን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስገኝ አልጠራጠርበትም፡፡ እነዚህ ሁሉ ጽሁፎቼ ከመወረሳቸው በፊት ለሁለተኛ ሰው ተላልፈው ያልተሰጡ በመሆናቸውና የሐሳብ ነፃነት (ፍሪደም ኦፍ ዘ ማይንድ) በመኖሩ እንደ ፅንሰ-ሐሳብ በመቆጠራቸውም፣ በአብዛኞቹ አልተከሰስኩባቸውም፡፡

አሁንም ከላይ የጠቀስኳቸውን የጽሁፍ ቅርስ አስገዳጅ ወራሾቼን የምጠይቀው ብዙ ንትርክ ውስጥ ሳንገባ የወሰዱብኝን የሥነ ጽሁፍ ከምችት እንደመልሱልኝ ነው፡፡ ለእውነት፣ ለፍትሕና ለነፃነት አቤቱታዬን አቅርቤ ከምፋረዳችሁ በፊት በልመና መልክ “በሕግ አምላክ መልሱልኝ” ብሎ መጠየቁ ኢትዮጵያዊ አቀራረብ መሰሎ ስለታየኝ በዚች ክፍት ደብዳቤ በታላቅ አክብሮትና በከፍተኛ ትህትና እንድትመልሱልኝ  እጠይቃለሁ፡፡

ይህ የገሞራው (ኃይሉ ገ/ዮሐንስ) አቤቱታ ግንቦት 27 ቀን 1966 ዓ.ም  በታተመው መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ላይ  ለንባብ የበቃ ነው፡፡ ለዚህ የደራሲው አቤቱታ በወቅቱ “የሕዝብ ጸጥታና ጥበቃ መ/ቤት” የተባለው ተቋም የሰጠው ምላሽ ሰኔ 8 ቀን 1966 ዓም ለንባብ በበቃው አዲስዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል፡፡ የደህንነት ተቋሙ የሰጠውን ምላሽ ደግሞ ሌላ ጊዜ አቋድሳችኋለሁ፡፡

እስከዚያው “ብዙ ንትርክ ውስጥ ሳንገባ” ምናምን በሚሉት የገሞራው ደፋር አገላለፆች ተደመሙ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
Print       Email
• Published: 11 years ago on December 10, 2013
• By:
• Last Modified: December 10, 2013 @ 3:30 pm
• Filed Under: Ethiopia
• Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar