www.maledatimes.com ሰንበት ት/ቤት ወይንስ ያዛውንቶች ክበብ (ከዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰንበት ት/ቤት ወይንስ ያዛውንቶች ክበብ (ከዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ)

By   /   December 11, 2013  /   Comments Off on ሰንበት ት/ቤት ወይንስ ያዛውንቶች ክበብ (ከዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ)

    Print       Email
0 0
Read Time:21 Minute, 43 Second

የሻኪሶ ቅድስተ ማርያም ሰንበት ት/ቤት የተመሰረተው በ1976 ዓ/ም ሲሆን የተመሰረበትን 29ኛ ዓመት በቅርቡ አክብሯል:: ነገር ግን ይህ ሰንበት ት/ቤት እንደ ማቱሳላ የዕድሜ ታሪክ ብቻ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም ሰንበት ት/ቤቱ የማቅ ጥገኛ በመሆኑ ነው ማቅ ለኔ አካሄድ ይመቹኛል ያላቸውን ካስቀመጣቸው 10 ዓመታት አልፏቸዋል፡፡ በቃለ አዋዲው መሰረት እድሜያቸው 30 ዓመት በታች የሆኑትን ወጣቶች በሰበካ ጉባኤ አማካኝነት ያስመርጣል፡፡ በሻኪሶ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ከማህበረ ቅዱሳን በሚተላለፍላቸው ቀጭን ትዕዛዝ የማቅ ቅጥረኞት ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ስልጣንን በሞኖፖል ይዘው ወጣቶችን በመጫን ከኪነ ጥበብና ከማርታ መዝሙር ውጪ ቢዘምሩ ይባረራሉ፡፡ 

 

ይህ የአዛውንቶች ስብስብ መመሪያ የሚወጣውና የሚረቀው በተመረጡ በከተማ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ነው፡፡ ለአብነት ያህል በአቶ ልንገረው መኮንን/መፃጉ/ ቤት በአቶ ዘላለም እርቅይሁን በአቶ አዳነ ኪሮስ በአቶ አዳነ ኤዴዬ በመገኘት በማቅ በበላይ ጠባቂ በሆኑት በመርጌታ ሰለሞን ባራኪነት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዝማሬን ይቃወማሉ ወንጌል እንዳይሰበክ የወንጌል ተባዮች ናቸው ቤታቸው ውስጥ ግን የሚመለከቱት የዝሙት ፊልም የሚያዳምጡት የአስቴር እና የጥላሁንን ዘፈን ነው፡፡ በአንድ ወቅት የሰንበት ት/ቤቱ ሊቀ መንበር የማቅ ስመ ፅድቅ ጋዜጣ ሪፖርተር ኃብተ ገብረኤል ታደሰ/ቃንጫን/  ቃለ መጠየቅ አድርጎለት ኃብተ ገብርኤልም ሲመልስ ይህ ሰንበት ት/ቤት ጠንካራ ነው ጥንካሬውም ተሀድሶዎችን አናስገባም ብሎ ወጥሮ የያዘ ነው፡፡ እኛ ሳንሱር ሳናደርግ  ማንኛውም ዝማሬ አይዘመርም፡፡ ማቅ ከአዋሳ ማዕከል ከላከልን ዝማሬ ውጪ አናዘምርም፡፡ ለመሆኑ ዝማሬን መቃወም ጥንካሬውን ይገልጣል እንዴ? ወጣቶችን ከቤቱ በማሳደዳቸው ነው ጥንካሬው? ዕድሜቸው ከ45 ዓመት በላይ ስለሆነ ነው እንዴ ጥንካሬያችሁ? ከአንድም ስድስት እህቶች አርግዘው ሲወጡ የት ነበራችሁ? ሱሪ አደረገች ጥፍር ቀለም ተቀባች ብላችሁ ከቤቱ በማስወጣታችሁ ነው እንዴ ጥንካሬው? የናንተን የስጋ ፍቃድ ስላልፈፀሙ ከቤቱ የተባረሩት ቤት ይቁጠራቸው ወላጅ እኮ ልጁን ቤተ ክርስቲያን የሚልከው በወንጌል ቃል በዝተው በዝማሬ ረክተው እንዲመለሱ እንጂ በዲቃላ በዝተው በዝሙት ረክተው እንዲመለሱ እኮ አይደለም!! እናንተ ራሳችሁን ሊቃውንት አድርጋችሁ የተቀመጣችሁ የልምድ አዋላጆች ዝናብ የማይታይባችሁ ደመናዎች ምንጭ የሌላቸው የውኃ ጉድጓዶች እስቲ ጎረቤታችሁን ክ/መንግስትን ተመልከቱ ከ20 በላይ የወንጌል መምህራንን ያፈራ በዓመት ከ4 ጊዜ በላይ ታላላቅ ጉባኤያትን በማድረግ በየሰንበት ት/ቤቱ ኮርስ በመስጠት እኮ ነው የወንጌል አብዮት የፈጠራቸው እንጂ ሐመርና ስመአ ፅድቅ ጋዜጣ የተገኘ ፍሬ አይደለም፡፡

 

ከእናንተ ፍሬ ይገኛል ብሎ ከማሰብ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ነው፡፡ እስቲ አስተውሉ ማህበራችሁ ውስጥ ያሉት በርካቶች የሚልኮል እጣ ፈንታ ገጥሟቸዋል እስቲ ንገሩን ባለሃብቱ ደረጃውን የጠበቀ መንበር ቢገዛ ከማቅ ካልተገዛ ብላችሁ ተሃድሶ ናቸው፡፡ ጉባኤን በራሳቸው ወጪ ቢያዘጋጁ ተሃድሶ ናቸው፡፡ አላችሁ በህንፃው ምርቃት ላይ እኮ 160,000 ብር/መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ለምረቃው የመጡትን የብፁህ አቡነ ዮናስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልኡካል ሙሉ ወጪን የሸፈኑት ተሃድሶ ያላችኃቸው ናቸው፡፡ ማቅ እንኳን ሌላ የአንድ ብር ጧፍ እናኳ አልሰጠም፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ እንደ ጧፍ ሲያቀልጥ ግን ተወዳዳሪ የለውም፡፡

እናንተ በህንፃው ምርቃት ላይ እንኳን መዘምራን አልባሳት እንዳይለብሱ የቤተ ክርስቲያኑን ፖስተር እንዳይሸጡ ከለከላችሁ ታዲያ ይህ ኦርቶዶክሳዊነት ነው? ወጣቱን ከቤቱ በማሳደድ የእርኩሰትን ስራ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በመስራት ነው ኦርቶዶክሳዊነት? የቤተ ክርስቲያኑን ሙዳይ ምፅዋት መገልበጥ ነው ኦርቶዶክሳዊነት?

እስቲ የማኅበሩን ሰዎች እንመልከታቸው 1ኛ. ኢሳያስ ገ/ስላሴ /ፈርጉሰን/ የሰንበት ት/ቤቱ ሂሳብ ሹም ገንዘብ ያዥ እና ቁጥጥር የማቅ የጀርባ አጥንት የ49 ዓመት ሽማግሌ እና የሶስት ልጆች አባት ነው፡፡ ወጣቶችን ከቤቱ እንደ ካሮት እየነቀለ የሚጥል፣ በተክሊል አግብቶ ከሚስቱ እህት ሲማግጥ የተያዘ፣ ፈርጉሰን ስንል የአያቱ ስም እንዳይመስላችሁ የማችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ በቲቪ መስኮት ሲታዩ ካፋቸው ማስቲካ አይጠፋም ማስቲካ ሲበሉ ሁሌ ይታያሉ ኢሳያስም የማቅ ዶክተሮች ሳያዙለት አይቀርም መሰለኝ ቀሚስ የለበሰች ሁሉ አትለፈኝ የሚል ሰው ስለሆነ ነው ፈርጉሰን የተባለው ከፈርጉሰን አፍ ማስቲካ ከኢሳያስ ፊት ደግሞ ዝሙት አይጠፋም ለማለት፡፡ በ2003 ዓ/ም ሰንበት ት/ቤቱ 28ኛ ዓመቱን ሲያከብር ከተምቦላ ሽያጭ 18,000/አስራ ስምንት ሺህ ብር/ ከቲሸርት ሺያጭ 10,000 /አስር ሺህ ብር/በድምሩ 28,000 /ሃያ ስምንት ሺህ ብር/ቤት ሰብስቦ ቤት ጀምሬ መጨረሻ አጣሁ ቀስ እያልኩኝ እከፍላለው በማለት የውሀ ሽታ አድርጎታል፡፡  በ1999 ዓ/ም ሰንብት ት/ቤቱ ለኮምፒተር መግዣ ከየ መስሪያ ቤቱ በቅፅ የተሰበሰበ 11,000 /አስራ አንድ ሺህ ብር/ የውሃ ሽታ አድርጎታል፡፡ ሰንበት ት/ቤቱ ለገና፤ለትንሳኤ፤ለዘመን መለወጫ፤ ለነድያንና ለህግ ታራሚዎችን ፆም ያስፈታሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ዝግጅት የሚሆን ከየመስሪያ ቤቱ ገንዘብ ይሰበሰባል ነገር ግን በከተማው ውስጥ ያሉ ወርቅ ነጋዴዎች በየ በአላቱ ሁለት ፍየሎችን በመግዛት ያስረከባሉ ባለ ሱቆችም ከጨው እስከ ቂቤ ያለውን ወጪ በነፃ ይሸፍናሉ የተሰበሰበው ገንዘብስ ብትሉኝ? በገንዘብ ያዡ ኢሳያስ ገቢ ይደረግና በሂሳብ ሹሙ ኢሳያስ ወጪ ይደረጋል በራሱ ቁጥጥር ይደረግበታል፡፡ እንዲህ ነው ጨዋታ!!

ዲያቆን ቁምላቸው የሰንበት ት/ቤቱ ፀሐፊ ድራማና ስነ ፁሁፍ ተጠሪ የማቅ ስራ አስፈፃሚ ህፃናትን መቃብር ሰብስቦ ተነሱ ለአድማ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ተነሱ ለፀሎት አአውደ ምህረት ላይ ቋንቋዬ ነሽ ብሎ የሚዘምር ጭፈራ ቤት ገብቶ ሀኪሜ ነሽ ብሎ የሚዘፍን አንድ ጎልና አንድ ሚስት አስተማማኝ አይደለም በሚል አባባሉ የሚታወቅ እና ሁለት ሚስት ያለው፡፡ የሁለት ህፃናትን ክብረ ንፅህና የደፈረ ዳግማዊ ሄሮዶስ በዕለተ ሰንበት 4 ዣንጥላዎችን በማዞር ሁለቱን ገቢ ሲያስደርግ ሁለቱን ጥላ ለማርቆስ እናት ቤት ይላል የማርቆስ እናት ቤት ስል ሐዋርያት እንዳይመስላችሁ የማቅ ቤተ መቅደስ በመባል በምትታወቀው ለመሌ ግሮሰሪ ለቢራና ለጥብስ እንጂ!!

2004 ዓ/ም ለህንፃው ምረቃ ለመዘምራን አልባሳት መግዣ አልባሳት 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ወጪ ተደርጎ ኢሳያስ አዲስ አበባ ይሄድና ሊገዛ ሲል ቀድሞ ሻኪሶ የነበረ ፍቅረ ማርያም የተባለ ወንድም የተባለውን አልባሳት በራሱ ወጪ ይገዛል ነገር ግን 15,000/አስራ አምስት ብር ኢሳያስና ቁሜ እንደ አባታቸው ማሳ ተካፍለውታል፡፡ መሪጌታ ሰለሞን ሀይሌ /ቀያፋ/ የማቅ የበላይ ጠባቂ የግንቦት ባራኪና ቀዳሽ የሰንበት ት/ቤቱ ሳንባ የሻኪሶ ቅ/ማርያም ስ/ወ/ሀ/ የነበረ በህዝብ ተቃውሞ በአቡነ ሳዊሮስ ትዕዛዝ ወደ ቦሬ ማቲ ተቀይሮ አሻፈረኝ በማለት ጠቅላይ ቤተክህነት ያገደው ፖለቲካና ዘረኝነትን አጣምሮ በመያዝ ያለ ጎንደሬ መቀደስ የለበትም የሚልና ክርስቶስ ከጎንደሬ ነው የተወለደው ለማለት ትንሽ የቀረው የሃይማኖትን የፖለቲካንና የጥንቁልናን ካባ የደረበ ሰው ነው፡፡

የቅ/ማርያሙ አስተዳዳሪ ጎንደሬ ባለመሆናቸው ብቻ ቤተ መቅደሱን አረከሱት እያለ ህዝቡን ሲያነሳሳ የነበረ ይህ ግለሰብ ሻኪሶ ሲመጣ የቀን ስራ የሚሰራ በአዝመራ ጊዜ ጤፍና ስንዴ አጫጅ አሁን በሲያምር ተዋናይነት በጠቅላይ ቤተ ክህንት የታገደውን መልሶ የቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ አድርጎታል ይህ ቀድሞ ጤፍና ስንዴ አጫጅ አሁን ወጣቱን ከቤተ  ክርስቲያን አጫድ ሆኗል፡፡ ይህ ሞራ ገላጭ ጠንቋይ ግለሰብ በወረዳው ስር በምትገኘው ቦሬ ሸጥ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እያለ የደብሩን ቄሰ ገበዝን በመተት ሊገድል ሲል ተነቅቶበት ተጋልጦ የተባረረ በወቅቱ የወረዳው ፀሐፊ በነበረው በዲያቆን ቁምላቸው እጅ የሰበካው የክሱ ደብዳቤ ይገኛል፡፡ በ2001 ዓ/ም የአጎቱ ልጅ የሆነው ዲያቆን ጥበቡ መቃብር ቤት አብረው በመሆን አጋንት  ሲስቡ ስህተት በመፈጸማቸው የዲያቆኑን ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ ይህንን ጉድ የዲያቆኑ ባለቤት ትመሰክራለች፡፡

እንዲሁም ይህ ግለሰብ ማቅ ላይ ለተለጠፉ ኪራይ ሰብሳቢዎ ነጋዴዎች ይጠነቁላል ልንገረው መኮንን/መፃጉ/ ይህ ግለሰብ ቀድሞ ጎጃም በረሃ ላይ መኪና አስቁሞ የሚዘርፍ የደርግ ወታደር ነበር፡፡ በቅርቡ ደግሞ ከመንግስት ከኪራይ ሰብሳቢ አባል ከሆነው የኢሀአዴግ የአባልነት መታወቂያ በአስመሳነቱ በማውጣት እንደ ጓደኛው ወርቅነህ ተክለ ሚካኤል ለግንቦት 7 አጥቂ መስመር ላይ የሚጫወት ወር በገባ በ21 ቦቃ በግ በመግዛት አርዶ ደሙን እራቁቱ ሆኖ ይቀባል ዘንቢል ሙሉ ንፍሮ ይበትናል፡፡ አለም ሁሉ የዳነው በአማናዊው በግ በክርስቶስ እንጂ በእንሰሳ ደም አይደለም ይህንን ምስጥር ያወጣችው የቀድሞ ባለቤቱ ነች፡፡ ይህ ሰው ከባለ ሰባት ስልጣኑ ኪዳኔ ጋር በመሆን በማሪያም ገንዘብ ኤልክትሮኒክስ በመነገድ ትርፍ ለጋራ በመጠቀም ከትርፉ ከመቶ አስር በማውጣት ለማቅ ይሰጣሉ፡፡ አስራት በክርስቶስ ደም ለተመሰረች ቤተ ክርስቲያን ወይንስ በሰው ደም ብላቴ ለተመሰረተ ማህበር? የቃኤል መስዋዕት ይሉታል ይህ ነው፡፡

መ/ር አዳነ ኪሮስ የቀድሞ የቀይ ሽብር ረሻኝ የኢሰፓ አባል አንዳች ስነ ምግባር የሌለው የማቅ ፍርፋሪ ለቃሚ የሶንዳና የፈጥኖ ደራሽን ዕድር ቆርጥሞ የበላ ካሃዲ ክብሩን በሆሊደይ ሆቴል በግማሽ ኪሎ ስጋና በሁለት ቢራ የሸጠ የግንቦት ሰባት ተከላካይ መስመር ላይ የሚጫወት የአንድ ምስኪን ሴት ልጅ በኢለመንተሪ ት/ቤት ደም ስሯን ብሎ የገደለ ታስሮ በሙስና የተፈታ ያገር ሽማግሌ ተብዬው ጋር  ከቀድሞ ሰበካ ጉባኤ አቶ ሁንዴ ዱላ ጋር በመሆን ከባለ ሰባት ስልጣኑ ኪዳኔ ጋር ሆነው ማርያም ቅጥር ግቢ ከብት አደልበው በመሸጥ ትርፍ ለጋራ የሚጠቀሙ የቤተ ክርስቲያንን ክላሽ በቤቱ ደብቆ በአጣሪዎች ተጋልጦ ያስረከበ ከሰበካው ሲወርድ እርጅና የተጫጫነው አሁንም ለመመረጥ የሚሮጥ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች እያሉ ሰንበት ት/ቤቱ እንዴት ያድጋል? ይህ እንደ ማቱሳላ የዕድሜ ታሪክ ብቻ ሆኖ የቀረው ሰንበት ት/ቤት እንደ ጉንዳን ወረው እንደ ጊንጥ የሚነድፉ አይናቸው የጊያዝ አይን የተሰጣቸው ወጣቱን እየገደለ ብቻውን የሚኖር የተኩላ ማህበር እስካልተላቀቀ ድረስ ፍሬ ማፍራት አይችልም፡፡ ሰንበት ት/ቤቱ ከነፍጠኛው ስርዓት ተላቆ በቃል አዋዲ መሰረት ለወጣቶች ሲለቀቅ ብቻ ነው፡፡ ጌታ ወንበዴዎችን እና ቀማኞችን ከቤተ መቅደስ ገርፎ እንዳስወጣ የብላቴውን ዉልደ አሪዮስን ገርፎ ያስወጣልን፡፡

ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን

ከዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ

myemaus@gmail.com

ሻኪሶ

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 11, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 11, 2013 @ 9:46 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar