www.maledatimes.com በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ?

By   /   December 12, 2013  /   Comments Off on በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ?

    Print       Email
0 0
Read Time:38 Minute, 45 Second

ራሳችንን ማዬት የምንጀምረው መቸ ይሆን? yqobadishegala@gmail.com አስተያየት
ካላችሁ ብትጽፉልኝ በደስታ እቀበላለሁ።
“ ሰው ሆይ የምታስበውን ግፈኛ ምኞት ሁሉ እፈጽማለሁ ብለህ ከመንጠራወትህ በፊት ባላሰብከው ጊዜ
የምትፈርስ እርጥብ ሸክላ መሆንህን አስብ!!!” ለእውነት እና ለፍትህ ሲሟገት የሞተው ጋዜጤኛ አቤ
ጉበኛው።
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍ የፈጸሙ ሁሉ በፈጣሪ ኃይል በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደሚቀጡ ያለፉትን ሁለት ሥራዓት
በማስታወስ መምህር ፅጌ ደስታ ወ/ኪዳን በ1999 ዓ.ም ከቃሊቲ ወህኒ በአንድ ወንበር ተቀምጠን ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ሁለተኛ ችሎት( ድንጋዮት ችሎት ወደሚያስችሉበት) እየሄድን ባለንበት ወቅት ያሉኝ ከልቤ አይጠፋም።ያሉትም
“የኢትዮጵያን ህዝብ የበደሉ ሁሉ ከኢትዮጵያ ሳይወጡ ቅጣታቸውን እግዚአብሔር በምድሯ ይሰጣቸዋል!!!” ለምሳሌ
በቀዳማዊ ንጉሰነገስት ኃይለስላሴ ዘመን የነበሩ በህዝብ ላይ ግፍ የፈጸሙ የተቀጡት ከኢትዮጵያ ሳይወጡ ነው። ደርግ
ሳይለይ በንጽሃንም ጭምር ማድረጉ ዘግናኝ ቢሆንም። የደርግ ባለስልጣናትም በቃልቲ ወህኒ ምን ያህል እንደበሰበሱ
ሁላችንም የምናውቀው ነው።መንግስቱ ኃይለማሪያምም ቢሆን ቃሊቲ ከታሰሩት በላይ እራሱን በባእድ ምድር አስሮ
ተቀምጧል። የወያኔውም አለቃ ለገሰ ዜናዊም ቢሆን አንድ ቀን ሰላም ሳያገኝ በእግዚአብሔር ፈቃድ በልጇ በአበበ ገላው
አማካኝነት አዋርዳና አሸማቃ በብስጭት ተቃጥሎ እንዲሞት ፍርዷን ሰጥታለች።ይህ የሚያስተምረን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ
ግፍ የሚሰራ ሁሉ ሰላም ሳያገኝ እንደሚኖር እና በመጨረሻም ቅጣቱን እንደሚያገኝ ነው።ከተቃዋሚሆችም ቢሆኑ የኦነግ
መሪዎች ያሰቡት ሳይሳካ በሰው ሀገር ሲንከራተቱ ያለፉትን ማስታወሥ በቂ ነው።በቅርብም አንድ የኦነግ መሪ ባለቤታቸው
ጥገኝነት ለማግኘት ስሯሯጡ በኖርዌይ ህይወታቸው ማለፉን ማስታወስ ትልቅ ትምህርት የምሰጥ ነው።”የአህዛቡ ወያኔ
ባለስልጣናትም ከኢትዮጵያ ሳይወጡ ፍርዳቸውን እንደሚያገኙ ጥርጥር የለኝም!!!”
የዛሬ የጽሁፌ መነሻ የግንቦት7 መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወያኔዎች ለድርድር ጠየቁን ብለው አዋጅ ማስነገራቸውና እሳቸውም ሰ
ትርጉም የሌላው ንግግር ማድረጋቸው ምን ይሉታል? የዶክተሩ ንግግር አፄ ምኒሊክ ገጠሙት የተባለውን ግጥም
እንዳስታውስ አድርጎኛል።
ደጉ ሳያልቅብኝ ክፉ ተናግሬ፣
የጨዋ ልጅ ሳለ ከባሪያ መክሬ፣
ጠበሱት መሰለኝ ሸተተኝ ሀገሬ።ግንቦት7 እውነት ቅንና ሀገሩን አፍቃሬ ኢትዮጵያዊ ሞልቶ እያለ
ከጣሊያን ባሪያ ከሆኑት አቶ ኢሳያስ እና አሽከሮቻቸው ጋር እየመከሩ የሚሰጡን አጀንዳ በህዝብ ከመተፋት ውጭም ምንም
ትርፍ እንደሌለው መረዳት ለምን እንደተሳናቸው አልገባ ብሎኛል።
አህዛቡ ወያኔ ሁል ጊዜ መደራደር የሚፈልገው ከቢጤዎቹ ጋር ነው።ለምሳሌ ከኦነግ፣ኦብነግ፣ሻቢያ እና ሌሎች
ኢትዮጵያን የመበታተን አዝማሚያ ካለቸው እና አሰብ የኢትዮጵያ አካል መሆኗን ከማይቀበሉ እና አሰብ የኤርትራ መሆኗን
በሙሉ ልብ አምነው ከዚህ በፊት ከተቀበሉት ጋር እንጂ ከልባቸው ድርድር ቢፈልጉ ኖሮ ድርድሩ የሚጀምረው ቃሊት
ታስረው ከሚገኙት ከእስክንድር ነጋ፣አንዱዓለም አራጌ ርዕዮት ዓለሙና ሌሎች ቅን ኢትዮጵያዊያን ጋር በሆነ ነበር።
እንዲሁም ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ካላቸው እንደሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ ጋር በሆነ ነበር።ነገርግን አምስት ሰዎች
ካሉት ድርጅት ጋር ድርድር መጠየቅ ፌዝ ከመሆን አይዘልም።አምስት ሰዎች ስል ዶ/ር ብርሃኑ፣አቶ አንዳርጋቸው፣አቶ
ኤፍሬም ማንዴቦ( የመጀመሪያ ልጀን ከኤርትራዊ መወለዱ እጅግ ደስ ያሰኘኛል የሚሉን)፣ታማኝ፣አቶ ወልደሚካኤል እና
ጋዜጤኛ ተብዬው ፋሲል።በእውነቱ ወያኔ ውጭ ተቃውሚ ነን ከሚሉት ሀገር ውስጥ የሚቃወማቸውን አንድ ጋዜጤኛን ምን ያህል እንደሚፈሩት እና እንቅልፍ እንደሚያሳጣቸው ለማንም የተሰወረ አይደለም።ግንቦት7 ታዲያ በምኑ ተፈርቶ ነው
ለድርድር የተጠየቀ።ምንም አዲስ ነገር የለውም ወያኔን ከልባቸው የሚቃወሙ ባለመሆናቸ ብቻ ነው።
በዚህ ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግንቦት7 የተለያዩ አጀንዳዎችን እያመጣ ህዝብን
ማደናገር አስፈለገው? እንዲሁም ሰሞኑን ደግሞ ወያኔ ለድርድር እንደጠራው ለማጮህ
የፈለገበት ምክንያት ምን ይሆን? ብለን ብንመረምር የተለያዩ አጀንዳዎች እያመጣ
የኢትዮጵያን ህዝብን ትኩሳት ለማቀዝቀዝ እና ሃሳቡን ወደሌላ አቅጣጫ ለማስለወጥ
በግንቦት7 የተተለመለት አጃንዳ ማስለወጥ እንደሆነ ለማንንም የተሰወረ አይደለም።እስኪ
ይህንን ለማብራራት የሚከተሉትን ነጥቦች አጢኑ፦
፩/ ሰማያዊ ፓርቲ በሀገር ቤትም ይሁን በውጭ ሀገር የህዝብን ቀልብ መሰባ ሲጀምር አቶ አንዳርጋቸው ከሻቢያ ተልኮ
ስለግንቦት7 ጦርና በኢሳያስ ዓይን ሞገስ ስለማግኘቱ በተሌቪዥን ጣቢያቸው እና ሌላው አጋፋሬያቸው በሆነው የአሜሪካ
ድምጽ ሬዲዮ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ተሰራለት ( ውጤቱ ክስረት) አጀንዳ አንድ
፪/ ግንቦት7 ለአራተኛ ዙር ( ይገርማል አንድ ዙር እንኳን አላሰለጠኑም) ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ለማሰመረቅ ወደምረቃው
ለመጓዝ በሚዘጋጁበት ጊዜ በአቶ አንዳርጋቸው እና በሌሎች ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ የስልክ ውይይት ሲያደርጉ
የተጠለፈውን ያሰሙን ደግሞ( ያውም ኤርትር ውስጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ የማይቻል ነው) አጀንዳ ሁለት
፫/ ሰሞኑን ደግሞ በሳዑዲዎች በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ በታሪካችን እጅግ ዘግናኝ እና አስከፊ በደል ኢትዮጵያንን
ዳር እስከዳር ባንቀሳቀስበት እና በወያኔ ላይ ከምንጊዜውም በላይ ጥርስ በስነከሰበት ወቅት ግንቦት7 ይህንን የህዝቡን ቁጭት
ውኃ ለመቸለስ ያደረገው ሙከራ እውን ከጤነኛ ተቃዋሚ የሚጠበቅ ነው??? ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሰማያዊ ፓርቲ በሳዑዲ
በህዝባችን ላይ የደረሰው በደል እጅግ ስላስቆጣው የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅቶ ለተቃውሞ በተዘጋጀበት ሰዓት የአህዛቡ
ወያኔ ፖሊሶች ( በድን ፍጡሮች) ዕድሜያቸው በገፉ እና በልጆቻቸው ሃዘን በተቆራመዱ ወላጆች ላይ ያድረሰው ድብደባ
ህዝቡን እጅግ ያሰቆጣ እና የወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጣት ታህል ስሜት የሌለው አውሬ መሆኑ ከመንጊዜውም
በላይ የተረዳበት ወቅት መሆኑ እየታወቀ ግንቦት7 ወያኔ ለድርድር ጠየቀን ማለቱ እውን የግንቦት7 መሪዎች ይህን ህዝብ ነፃ
ለማውጣት የሚታገሉ ናቸው ማለት ይቻላል??? አጀንዳ ሦስት
፬/ ይህ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ለማድረግ ጀርመን
በገቡበት ወቅት ግንቦት7 ወያኔ ለድርድር ጠራኝ ማለቱ ጥርጣርዬ እጅግ ያጎላው ሆኗል። አጀንዳ አራት
እንግዲህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሳጤን ግንቦት7 ከወያኔ በምን
ይለያል የሚልው ሐሳብ በአዕምሮዬ ላይ መጣ። ጎበዝ እነዚህን
የማናሳቸውን ነጥቦች አስተውሉ
 ግንቦት7 በአብዛኛው መሪዎቹ የወያኔ አባል እና ደጋፊ በሆኑ ሰዎች የተመሰረተ ነው።ለምሳሌ አቶ
አንዳርጋቸው፣ዶ/ር ብርሃኑ እንዲሁም የኢሳት አስተባባሪ የስቪል ሰርቪስ ምሩቅ ዳኛ ወልደሚካኤል፣በሻቢያ
ፍቅር አዕምሮውን የሳተው ኤፍሬም ማንዴቦ
 ወያኔ አማራን አምርሮ ይጠላል ግንቦት7ም እንደዚሁ( ለምሰሌ ኤፍሬም ማንዴቦን መጠቀስ በቂ ነው)
 ወያኔ ቅንጅትን ሲያፈርስ ትልቁን ሚና የተጫወተው የግንቦት7 መሪ ናቸው።  ወያኔ ኢ.ህ.አ.ፓን ይጠላል ግንቦት7ም እንደዚሁ( ዶ/ር ብርሃኑ ቃሊቲ የጻፈው መጽሃፍ ማንበብ በቂ ምስክር
ነው)
 ወያኔ የህብሬብሄር ድርጅቶችን ይጠላል ግንቦት7ም እንደዚሁ
 ወያኔ የጎጠኛ ድርጅቶችን ይወዳል ግንቦት7ም እንደዚሁ( ለምሳሌ ከኦነግ፣ኦብነግ እና ኤርትራ ውስጥ
ከደህሚት ጋር ያለው ቁርኝት በቂ ምስክር ነው)
 የግንቦት7ን ኤርትራ ውስጥ መወሸቅ ወያኔ ይወደዋል የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በጥርጣሬ ይመለከተዋል
 ወያኔ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና የሐይማኖት መሪዎችን ለግሉ መጠቀሚያ አድርጓቸውል ግንቦት7ም
እንደዚሁ ለማድረግ እየሳራው ያለው በግልፅ የሚታይ ነው
 ወያኔ አክቲቪስቶችን በገንዘቡ እየገዛ ያሰማራል ግንቦት7ም አክቲቪስቶችን በጥቅም እየገዛ ለግሉ ገንዘብ
አሰባሳቢ ያደርጋቸዋል
 ወያኔ የተሌቪዥን እና ሬዲዮ ጣቢያዎችን፣ድህረገጾችን እና ፓልቶኮችን ለግሉ መገልገያ ያደርጋቸዋል
ግንቦት7ም እንደዚሁ። ለምሳሌ የኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣እንደ ኢትዮሚዲያ፣ዘ-ሐበሻ፣ኢካድፎረም፣
ኢትዮፖለቲክስ፣ኢትዮፍሪደም፣ቋጠሮ፣አባይሚዲያ ሲሆኑ ከፓልቶኮች ደግሞ እንደ ከረንት አፍየርስ
የመሳሰሉት በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሱ ናቸው። የኢትዮሚዲያ ባለቤት በደርግም ሆነ በወያኔ ጊዜ የሄራልድ
ጋዜጣ አዘጋጅ በነበረበት ጊዜም አሁንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለግሉ ከርስ የቆመ ግለሰብ ነው።
 ወያኔ የሚቃወሙትን ውድ ኢትዮጵያዊያንን አሸባሪ በማለት ለማሸማቀቅ ይሞክራል ግንቦት7 ደግሞ አካሄዱን
እንዲያስተካክል ፊት ለፊት የሚጋፈጡትን ወያኔ የሚል ታርጋ ይለጥፍባቸውል።ማን ይሙት ዶ/ር ብርሃኑ እና
አቶ አንዳርጋቸው የሚቃወማቸውን ወያኔ ለማለት የሞራል ብቃቱ አላችው?
 ወያኔ ሰዎችን ተጠቅሞባቸው ሲያበቃ እንደሚወረውራቸው ግንቦት7ም እንደዚሁ።ለምሳሌ ከግንቦት7 ጋር
ግንኙነት በማድረግ መፈንቅለመንግስት ያደረጉ የወያኔ ጀነራሎች እና ታዋቂ ሲቪሎችን ወያኔ አስሮ
እያሰቃያቸው ባለበት ጊዜ ዶ/ር ብርሃኑ ከግንቦት7 ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ጥቂት
የአማራ ጀነራሎች ያደረጉትየመፈንንቅለ መንግስት ሙከራ እንደሆነና ግንቦት7 ምንም እጁ እንደሌለበት አንቋሾ
መናገሩ እጅግ ያሳዝናል።ቢሳካ ኖሮ ዘራፍ የሚለው ግንቦት7 ነበር። መፈንቅለመንግስቱን አቀናብረዋል
ከተባሉት ውስጥ ኮሌኔል አለበል አመራ እና አቶ ያረጋል እንዴት አምልጠው ኤርትራ ገቡ? ይህን በተመለከተ
ጥብቅ ሚስጥር ያለ ሲሆን የዚህም ሚስጢር አቀናባሪ አቶ አንዳርጋቸው ሲሆን እነዚህ ሁለቱ ግለሰቦች ውጭ
ከወጡም በኋል ሚስጥሩን ለማውጣት አለመፈለጋቸው በጋራ የሰሩት ሸር እናዳለ አመልካች ነው።
 ዶ/ር ብርሃኑ ቃሊቲ ታስሮ በነበረበት ወቅት ከዞን አንድ ለምን ወደ ዞን አምስትሊቀየሩ ቻሉ? መጽሃፋቸውንስ
እንዴት አድረገው ጻፉ።ለምን ለመፈታት ብለው ኢንጂነር ኃይሉን እና ወ/ሮ ብርቱካንን አግባቡ? የሚሉት
እስከአሁን ግልጽ ሊሆኑልኝ ያልቻሉ ሚስጢሮች ናቸው።ከዚህ ሁሉ በኋል ደግሞ አሜሪካ ሄደው
መቅረታቸው ነገሩ እንቆቅልሽ እንደሆነ የሚሰጠን ፍንጭ አለ።
ፀጋዬ ገብረመድህን “ ለወግ የወለዱት ትውልድ የአባቱን መቃብር ይንዳል” ሆናና የግንቦት7 መሪዎችም ለወግ
ይሆኑልናል ስንል እንዲህ ሆነው ቀሩ። ግንቦት7 አሁን የያዘው ሥራ ያላወቁብኝን ላታላቸው ያወቁብኝ ደግሞ
ምን አባታቸው ያመጣሉ ነው። በተለይ ወጣቱ የሀገር ተረካቢ ትውልድ መሆኑን አውቆ በትግሉ ላይ ንቁ
ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል አለበለዚያ “ግድ የሌለው ወጣት የፀፀት ዘመን ያሳልፋል!!!”
በማለት ፍራንኪሊን ጨርሶታል። ግንቦት7 ከበታኞች ጋር መሰለፉን በግዴለሽነት የምናልፈው ከሆነ
“ ለማጥፋት ከሚፈልገው ጋር እሲኪያጠፋው ድረስ በወዳጅነት የሚቀመጥ እንስሳ ቢኖር ሰው ብቻ ነው!!!”
የተባለው በኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ የተረጋገጠ ሆነ ማለት ነው። “ ጭብጨባና ምስጋና ለታላላቅ ጭንቅላቶች
እንደ እርካብ ያገለግላል ለደካሞች ግን እንደግብ ይቆጠራል።” የሚለው አባባል የኢሳት አክቲቪስቶችን
እንዳስታውስ ያደርገኛል። የግንቦት7 መሪዎች ከእኛ በላይ የሚያስብልህ ስሌለ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አርፈህ ተቀመጥ እያሉን ስለመሆናቸው ከነሱ የተለየ ሐሳብ ይዞ የተገኘን ሰው ወያኔ በማለት ማሸማቀቃቸው ሙሁሩ
ምን አግባኝ ብሎ እንዲቀመጥ ሚዲያዎቻቸው የሚጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው።
እንግዲህ ተግተን ነፃ የምንወጣበትን መንገድ አስተካክለን ለመያዝ ካልተነሳን ቮልተር “ ጅሎችን
ከሚወዱት የባርነት ሰንሰለት ማላቀቅ እጅግ ከባድ ነው!!!” እንዳለው መሆናችን ነው።በዚህ በኩል
ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተጽዕኖ ነፃ የሆኑ ጋዜጤኞች የሚጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው።ነፃ የሆኑ ጋዜጤኞች
አጎብዳጅ ጋዜጤኞችን እና በኢትዮጵያ የህዝብ የነፃነት ትግል የሚያሾፉትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን
ለህዝብ እየነቀሱ እያወጡ ማሳየት የሚገባቸው መሆኑን ተረድተው ለትግሉ ትልቅ እገዛ ማድረግ ይገባቸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ድፎ ዳቦ እየሆነ ነው። በአንድ በኩል አህዛቡ ወያኔ መከራውን ሲያበላው በሌላ በኩል
ደግሞ ነጻ ያወጡኛል ያላቸው ድርጅቶች ሲክዱት ምን እንደሚሰማው ተመልከቱት። ቃሊቲ ወህኒ ቤት ታስሬ
በነበረበት ወቅት የቅንጅት መሪዎች ሲፈቱ ትተውን የወጡት ሳያንሳቸው ከወጡ በኋላ ደግሞ የጀመሩትን
ንትርክ ስሰማ የተሰማኝ ስሜት “ በሁለት ጎን የተጎዳውንና ያዘነውን ልቤን ብትቀምሱት እሬት
እሬት ይላል!!!” ነበር።
በሳዑዲት በኢትዮጵያን ላይ የደረሰው ስቃይ እጅግ አድርጎ አንጀታችንን ሲያቃጥለው ወያኔ ደግሞ በሀገራችን
ላይ የተጎዱ ቤተሰቦችን እንደ እባብ መቀጥቀጡ ምን ያህል አሳፋሪ እና ሰቅጣጭ እንደነበረ ቅን ሀገር ወዳድ
ሁሉ እጅግ ያሳዘነው እና ያስቆጣው ነበር። ይህን አህዛብ እና ዘረኛ ወያኔን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ቆሽቴ
አሮ እያለ ግንቦት7 ደግሞ ወያኔ ለድርድር ጠየቀኝ ማለቱን ስሰማ የባሰውን አንጀቴን አረረ።ይህ ለኔ እንደገባኝ
በወያኔ ላይ ቂም እንዳትይዙ ይሄው ማረሻሻ ብለው እንዳላገጡብን ነው የተሰማኝ። አሁንም እንደ ቃሊቲው
ሰዓት ልቤን እሬት እሬት ነው ያለው።
 በመጨርሻ ውጭ ሀገር ሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ እንታገልለታልን የሚሉ ቡድኞች ማለትም ኦነግ፣ኦብነግ ለ22
ዓመታት፣ ግንቦት7 ወደ አምስት ዓመታት ገደማ ለወያኔ ርዕስ ፈጥሮ እንድንደበደብ፣ እንድንታስረ፣
እንድንገደል አመቻችተው ሰጡን እንጂ ለእኛ የፈየዱልን ነገር ምንድን ነው? ለምሳሌ የኦሮሞን ተወላጅ ኦነግ
እያለ፣የሱማሌን ተወላጅ ኦብነግ እያለ፣ሌላው በኢትዮጵያዊነቱ ለመብቱ የሚታገለውን ግንቦት7 የላከው አሸባሪ
እያለ ታርጋ እንዲለጥፍባቸው እና ለሲቃይ እንዲዳሩጉ ከማድረግ ውጭ እነዚህ ቡድኖች ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ
መውጣት ያደረጉት ምን ነገር አለ??? ማን ወክሏቸው ነው በየአደባባዩ ደረታቸውን ነፍተው
የሚጮሁብን?ጭራሽ በሰሩት አሳፋሪ ሥራ መሸማቀቅ ሲገባቸው እኛኑ መልሰው ሲያሸማቅቁን አሜን ብለን
መቀበላችን በፍቃዳችን ባርነትን ከመቀበል የሚለየው ምንድን ነው? ሌላው ቢቀር ማን ነው የወከላችሁ ብለን
ባገኘነው ሁሉ አጋጣሚ ብንነግራቸው ልካችውን ያወቁት ነበር።ነገርግን ለነዚህ ሂሊናቢሶች
ስናጨበጭብላቸው እንገኛለን።
 ውጭ ያሉ የህዝብ ውክልና የሌላቸውን ቡድኖችን የውጭ ትግል ከ30ዓመታት በላይ ተሞክሮ ውጤት
ስላላመጣ ኃይላችንን ሁሉ ወደሀገር ቤት ማድረግ አለብን ብለን ለምን አናስገድዳቸውም። በውጭ የሚገኙ
አብዛኞችን ጋዜጤኞችን የህዝብ ወገን እንጂ የአንድ ቡድን አሽከሮች መሆናችሁን አቁም ብለን በግልጽ ለምን
አንነግራቸውም።አለበለዚያ ነፃነት ስሙን ብቻ እንዳወቅን ወደከርሰመቃብር እንወርዳለን።
 የጎጠኞች ድርጅቶች ከማንዴል ታሪክ ሰሞኑን መማር ካልቻሉ “ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ……።” ማለት
ይገባናል።
 በአጠቃልይ ራሳችን መመርመር እና በራሳችን ላይ መሰለፍ እንዳለብ የሳዑዲ ውርደታችን ትምህርት ሊሆንን
ይገባል።አንድ ጠንካራ ድርጅት ቢኖረን ኖሮ ይህ ጊዜ ወያኔን ለማስጭነቅም ሆነ ለማስገደድ አመቺ ጊዜ
ይሆንልን ነበር። ያለመታደል ሆኖ ይህንን አሳፋሪ ውርደት እየመረረንም ቢሆን ተቀብለናል።የሚታደገው ያጣና
ነፍሱ ተንጠልጥላ ያለችው የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ውርደትን አሜን ብሎ ተቀበለ።እጅግ
ማፈሪያ ትውልድ!!!
ወገኖቸ ሆይ እንደዛሬው የማንም ማላገጫ ሳንሆን ብርቅዬ የአፍሪቃ የነፃነት
ታጋይና መሪ የነበሩ ስለኢትዮጵያ እንዲህ ነበር ያሉ፦ “ እንግሊዝም፣አሜሪካም፣ፈረንሳይም የትም ከምጎበኝ ወደ አንዲት ኢትዮጵያ በመሄድ
ከጥንታዊ ጀግኖች አባቶች መንፈስ ጋር በሀሳብ መገኘት የበለጠ ያረካኛል!!!” ማንዴላ
(ነፈሳቸውን በገነት ያኑርልን) ወያኔ፣ሻቢያ፣ ኦነግ፣ኦብነገን ይህን መንፈስ ምን ብለው
እንደሚያብጠለጥሉት ዘወትር የምንሰማው ነው።
“ የጥቁር ኢትዮጵያዊ አባት ድል ባይመሰክርልን ኖሮ በአምሳሉ የተፈጠረው የልጅዬው የማኦ
ማኦ ጦርነት ብቻውን ነፃነታችንን አያስገኝም ነበር!!!” ጆሞ ኬንያታ
“ ኢትዮጵያ ብቻዋን የጥቁር ህዝብ አለኝታ ናት!!!” ክዋሚ ንኩሩማ
“ አንቺ ኢትዮጵያ የመላው ጥቁር ዓለም ኮኮብ ነሽ!!!” ሊዎፖል ሴዳር ሴንጎር።
 ከላይ ማንዴላ የጥንታዊ ጀግኖች አባቶች መንፈስ ያሉት አንድ ኢትዮጵያና አንድ ባንዲራ ነበር።ዛሬ ግን የማንም ቀረፎ
ተነስቶ የመሰለውን ጨርቅ እየሰፋም ሆነ እያሰፋ እያንጠለጠለ ሀገር እገነጥላለሁ ሲል እንደራደር፣እንነጋገር ዘመኑ
ተለውጧል ዛሬ የዲሞክራሲ ዘመን ነው ማለቱ ባሌጌዎችን እንዲተብቱ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም።ደግሞም ግራኝ
መሃመድ ነፃ አውጭ ነበረ የሚል የእስላም መሪ ከሳዑዲት እና ከአረብ የተላከ ቅጥረኛ በመሆኑ ስለሱ መጨንቅና
መጠበብ የለብንንም። እውነተኛውን የኢትዮጵያ ታሪክ የማይቀበል ሁሉ በየትኛውም መለኪያ ኢትዮጵያዊ ሊሆን
አይችልም።ስለዚህ እሱ የፈጠረውን ታሪክ ይዞ የሚፈልገው ሀገር መኖር እንጂ ይህ መብቴ ነው ብሎ ለሀጩን
እንዲያዝረከርክብን እድል አንስጠው። ላሃጩ የሚያዝረከረክበት ሀገር ኤርትራ ሄዶ መቀመጥ መብቱ ነው። በቅርብ
ሳዑዲት በኢትዮጵያዊያን ላይ ያን አሰቃቂ በደል ብትፈጽምም እንኳን ባንዲራውን ቀና ብሎ ማየት አስፈሪ መሆኑን
እንደተነገረን ሁላችንም ሰምተናል። የኛ በንዲራ ደረግ አንበሳውን ነቀለው ወያኔ ደግሞ ምናምንቴ አምጥቶ ለጠፈበት።
 ጎበዝ የኮሪያ ዘማቾችን ስናስብ ክቡር ሂይወታቸውን የገበሩላት ለየተኛዋ ባንዲራ ነው?እሷ ዝቅ ከምትል እኛ ብንሞት
ይሻለናል ብሎ የሞቱላት ባንዲራ አንበሳ ያለችባት ነች እንጂ ደረግና ወያኔ የሰጡን አይደለችም።የጥንት አያቶቻችን
የሞቱላት እና ያወረሱን ባላአንበሳውን እንጂ አሁን የምናየውን አይደለም።ታዲያ ኦነግና ኦብነግን ፈርተን የጥንቷን
ባንዲራ ያነሳ ጥቁር ዉሻ ይውለድ እንደተባለ ስለሷ ለማንሳት የምንፈራው ለምን ይሆን?ከአረብ እየተላከ የሚመጣውን
ሁሉ እየፈራን የምንኖር ከሆነ መቸውንም ነፃ አንውጣም። ኢትዮጵያ ያለ ሞአ አንበሳ ባንዲራ ኢትዮጵያ
ብሎ መጥራት አፅም ወቃሽ እንደሚያደርገን ሁላችንም ማወቅ አለብን።ማንም ቢንጫጫ
መብቱ ከኢትዮጵያዊነት እና ከታላቋ ባንዲራችን በኋል መሆኑ እንዲረዳ እቅጩን እንንገረው።በደም የተገኘች እንጂ
ደርግና ወያኔ የፈጠሯት አይደላችም።አክራሪዎች ለምን ቢሉን ቀድመው ሳዑዲት እና አረብ ሀገር ያለውን ባንዲራ
ያስቀይሩና ከዚያ በኋል እኛን ይጠይቁን።ኢትዮጵያ ጥንታዊት ሀገር እንጂ ዛሬ እንደተፈጠረች ሀገር ማንም ያለንን ሀሳብ
ይዘን የምናራምድ ከሆነ ከመበታተን አንድንም።አልረፈደም አቁሙ አቁሙ አቁሙ እንበላቸው።
ጎበዝ አሁን ውዳቂዎች መሆናችን ምን ያህል ያሸማቅቀናል?ምን ያህል ብናቀረቅር ውርደታችንን እንሸፍነው
ይሆን?ወዴት ብንደበቅ የጀግኖች አያቶቻችንን መንፈስ እናመልጠው
ይሆንን?????????????ውርደታችንን ምን ቃል ይገልጽልን ይሆን?
ጨረስኩ
አምላኬ ሆይ ያችን የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን ሳታሳይ አትግደለኝ!!!
የሶማው ነኝ ( ከባዳ ሀገር)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 12, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 12, 2013 @ 3:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar