www.maledatimes.com የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው ገብሬሉ ተስፋዬ ከ ኖርዌ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው ገብሬሉ ተስፋዬ ከ ኖርዌ

By   /   December 16, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው ገብሬሉ ተስፋዬ ከ ኖርዌ

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 18 Second

የሚያኮራ የሚያስደስት ኢትዮጲያዊ አንድነት ሰሞኑን በተደረጉት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ አይተናል ::
በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ ላሉት እህትና ወንድምቻችን ሀይማኖትና ዘርን ሳንለይ ያሳየነው የአንድነትና የቁጣ መንፈስ በጣም
የሚያስደስት ነው :: ይሄ ያሳየነው አንድነት እና ቆራጥነት መቀጠል ሊኖርበት ይገባል :: ካልሆነ ግን የችግራችንን ሥር መንቀል
አስችጋሪ ነው :: ሳውዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ሲገደሉ፣ሲደበደቡ እና ሲደፈሩ በኢትዮጲያዊነታችው መሆኑን
መገንዘብ ያስፈልጋል :: ይሄ አይነቱ ኢሰብሐዊ ጥቃቶች በሰፊው እየደረሰ ያለ ሲሆን አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ፊት
ካልተጓዝን በተለያየ ቦታና ሀገር ኢትዮጲያዊነት ሊደፈር ይችላል ::
በመጀመሪያ መግለፅ የምፈልገው የኢትዮጲያን ክብር እና ማንነት ያጠፋው ወያኔና አመራሩ ናችው :: ስለዚህ ሁል ጊዜ
ለሚፈጠሩት ችግሮች ሆይ ብለን መነሳት ብቻ በቂ መፍቴ አይሆንም ዋናው የችግሩን መንሴ ወያኔን ማስወገድ ነው :: ወያኔ
ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እህትና ወንድሞቻችን ተሰደዋል፣ተገድለዋል፣ተደፍረዋል ይሄ አዲስ ነገር
አይደለም ሁላችንም ቢሆን እየሰማን እያየን የቆየነው ነገር ነው :: በአሁኑ ሰሀት በሳውዲ አረቢያ እየተደረገ ያለው ግፍ በዛ
እንጂ በፊትም የነበረ ነው ::የወያኔ አገዛዝ በሀገር ፍቅር ወይም በአንድነት ላይ የተመሰረተ አይደለም :: ይሄን በደንብ አድርጎ
ለብዙ አመታት አሳይቶናል :: የእናትና የአባቶቻችንን መሬት ለበአድ ሀገር ተወላጆች በመሸጥ፣መሀበረሰቡን በዘር እና
በሀይማኖት በመከፋፈል፣እህትና ወንድሞቻችንን ለበአድ ሀገር አሳልፎ በመስጠት እና በመሳሰሉት ማየት ይቻላል ::
የአንድነታችን መላላት መንሴወች እና መፍቴያችው ያልኩዋችውን ላብራራ
አንደኛው እንደ ሰው እናም እንደ ኢትዮጲያዊ ለሚደርሱብን ኢሰብሀዊ ድርጊቶች አይሆንም፣አይደረግም የሚል ቆራጥ
መንፈስ በውስጣችን መመንመኑ :: ይሄ ወደ ምን ያመራል ብንል ለገንዘብ እና ላአንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞች አገርን አሳልፎ ወደ
መሸጥ:: ሰው እንደመሆናችን መጠን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል የወያኔ መንግስት የህዝብ ጥርቅም መሆኑን :: ህዝብ ደግሞ
የእያንዳንዱ ሰው ስብስብ ነው :: ስለዚህ እንደ ሰው ወያኔ ለሚያደርስብን ጥቃቶች አይሆንም ካልን ወያኔ የሚቀጥልበት
ምንም ምክንያት አይኖርም :: ህዝብ የመረጠው መንግስት ደግሞ ለህዝቡ አንድነት የቆመ ነው ::
ሁለተኛው የወያኔ የአገዛዝ ስልት ነው :: በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት (ወያኔ) ስልጣን ላይ ለመቆየት የተለያዩ ጫናዊ
የአገዛዝ ስልቶችን ይጠቀማል :: ከሁሉም የሚከፋው ዘርን ከዘር እና ሀይምኖትን ከሀይማኖት በማጣላት የህዝቡን አንድነት
የሚበታትኑት ነው :: ለዚህም ምስክሩ ኢትዮጲያን ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያላችው ብቻ
አይደሉም ጥሩ የትምህርት ደረጃ እና ክፍያ ያላችውም ናችው ::ይህ የሚያሳየው የደንነት እና የአንድነት ስሜታ በመሀበረሰቡ
መመንመኑን ነው ::መፍቴው ህዝብ የመረጠውን መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን አስተዋፆ ማድረግ :: ለምናደርጋችው
ማንኛውም እንቅስቃሴወች ከማስተዋል ጋር ሊሆን ይገባዋል :: ሌላው እንደ አሜሪካ ካሉ ያደጉት ሀገራት በዘርም በቀለምም
በሀይማኖት የማይገናኙ ህዝቦች እንዴት ለአንድ አላማ እንደቆሙ ትምህርት ከነርሱ በመውሰድ ::
ሦስተኛው የኛ የሆኑ ችግሮችን ሌላ ሀገሮች መተው ችግራችንን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅ :: ይሄ እምነታችን ያመጣብን
የራሱ የሆኑ ችግሮች አሉት፥ ከችግሮቹም አንዱ ያሀገራችንን ታሪክና ሚስጥራት አሳልፈን መስጥት :: ይሄ ደግሞ የተለያዩ
የምእራብአዊ ሀገሮች በኢትዮጲያ ፖለቲካ እንደፈለጉት እጃችውን እንዲያስገቡና እንዲያሶጡ መንገድ ከፍቶላችዋል :: ይሄም
ለአንድነታችን መላላት ትልቅ አስተዋጾ አለው ::ለምሳሌ የጫካ ውስጥ ጎሾችን ብንወስድ በተናጠል ሳር በሚግጡበት ጊዜ በቀላሉ አውሬ ያጠቃችዋል ግን ሶስትም አራትም ሆነው ሲግጡ እራሳችውን በሁሉም አቅጣጫ ከአውሬ መከላከል ይችላሉ ::
ስለዚህ መፍቴው ምንልያይበትን ነገር ከማየት አንድ የሚያደርገንን ነገር በማየት ችግራችን እርስ በእራስ በመወያየት መፍታት
ነው::
አራተኛው ከታሪክ አለመማራችን ነው :: ኢትዮጲያ ባለ ብዙ ታሪክ ሀገር ስትሆን የሚያስደስት ታሪክ እንዳላት
ሁሉ የሚያስከፋም ታሪክ አላት :: ታሪካችንን በአግባቡ መርምረን አጥንተን ምንጓዝ ብንሆን ኖሮ አንዳይነት ችግሮች
በተደጋጋሚ ባልመጡብን ነበር ::መፍቴው የሰው አገርን ታሪክ ቀድሞ ከማወቅ ይልቅ የሀገራችንን ታሪክ አምብበን ተረድተን
ተገንዝበን ለችግራችን ቀድመን መፍቴ ፈልገን መገኘት ይኖርብናል ::
በኔ እምነት ከላይ የጠቀስኩዋችው አራት ነጥቦች ለአንድነታችን መላላት ቁልፍ ከሆኑ መሰረታዊ ችግሮች
አንዳንዶቹ ናችው :: በአሁኑ ሰሀት ኢትዮጲያ እየሄደች ያለችበት ጎዳና አስከፊ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው :: ስለዚህ እኛ
ኢትዮጲያውያን ከምን ጊዜ በበለጠ ለአንድነታችን እናም ለሀገራችን ሰላም የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ያለብን ሰሀት አሁን
ነው::
ፍቅር ለኢትዮጲያ እዝብ !

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 16, 2013 @ 5:40 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar