www.maledatimes.com ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች

By   /   December 16, 2013  /   Comments Off on ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 46 Second

ታሕሳስ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከግንቦት ሰባት ዲሞክራቲክ የተላከ መግለጫ ኤርትራ የሚፈፀም ወንጀል1 ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዋናውን ገጽ እዚህ ያንብቡት
የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት ሲጣስ የትም ይሁን የት፣ በማንም ይሁን በማን ሊወገዝ፣ ፈጻሚው ሊጠየቅ
ይገባዋል። ኢትዮጵያውያን በተለይም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የህግ ባለሙያዎችም ሁኔታውን
አጣርተው ለወገኖቻችን ሰቆቃ ጥብቅና ሊቆሙ ይገባል።

የኢትዮጵያውያን መከራ አገርቤት ባለው መንግስት በሚደረግ የመብት ጥሰት የሚጀመር ነው። ይህን ቅጥ ያጣ
ፖለቲካዊ አፈና፣ የዘር መድልዎ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግር በመሸሽ፣ የተሻለ ነጻነት ወይም የስራ ዕድል
ይገኝበታል ተብሎ ወደ ሚታሰብበት የዓለም ክፍል ተሰዶ የናፈቀውን ፍትህና ነጻነት የማያገኝበት፣ በፍርሀትና
በእፍረት ተሸብቦ ያሰለፈባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ተከስተዋል።

በቅርቡ በሳውዲ ዓረቢያ የተመለከትነው አሰቃቂ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር ሃብት ንብረትን መዝረፍ እንደ
አንድ ማመላከቻ ሊጠቀስ ይችላል። በውጭ ሃገር የሚፈጸም የወገኖቻችን ስቃይና መከራ በባእዳን ብቻ
የሚፈጸም አይደለም። አንዳንድ ድርጅቶች ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም ለነጻነት እንታገላለን በሚል ሽፋን
ነጻነት ናፋቂ ወገኖቻችንን በቃላት በማታለል፣ ለነጻነት በሚደረገው ትግል ተሳታፊ ሁኑ በሚል ሰበብ ወደ
ኤርትራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው። በነጻነት ትግል ስም የሚፈጸም ግፍና በደል እንዲያውም ሰው
በተሰበሰበበት የሚደረግ አረመኔያዊ ግድያ ሲፈጽም ነጻነት መሆኑ ቀርቶ ባርነት ይሆናል። ሰው ሲገደል
ለመቀጣጫ አገዳደሉን ቆሞ እንዲመለከት የተደረገውን ወገንም ሰብዓዊነት የሚፈታተን አረመኔያዊ ድርጊት
ነው።

ይህ እንግዲህ ኤርትራ ውስጥ በተደራጁ የወያኔ/ኢሕአዲግን መንግስት እንቃወማለን ለዚህም በትጥቅ ትግል
ከስልጣን እናስወግደዋለን በሚሉ አንዳንድ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚፈጸም ድርጊት ነው። እነዚህ ድርጅቶች
ኤርትራ ውስጥ የራሳቸው የማሰቃያ እስርቤቶች ያላቸው ሲሆን እጅግ በጣም በርካታ ወገኖቻችን በእነዚሁ
እስርቤቶች በደረሰባቸው ስቃይ ህይወታቸው አልፏል ሌሎቹም አካለ ጎደሎ ሆነዋል። እዚህ ላይ ኤርትራ
ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ሰዎችን እንዳሻቸው የሚገድሉ፤ የሚያስሩና የሚያሰቃዩት ብቻቸውን ሳይሆን፣
በኤርትራ መንግስት ካድሬዎችና ወታደራዊ መኮንኖች አይዞህ ባይነትና ሲያስፈልግም በቀጥታ ተባባሪነት ነው።

በኤርትራ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል ግንቦት 7 በዋናነት የሚጠቀስ ነው። ይህ ድርጅት
የወያኔ/ኢሕአዲግን መንግስት በሁለገብ ትግል አስወግዳለሁ፣ ለዚህም ከሰይጣንም ቢሆን እርዳታ ከመጣ
መቀበል ችግር የለውም ብሎ የሚከራከር ድርጅት ነው። ድርጅቱ የተደራጀ ታጣቂ እንዳለው በማስመሰል
የብዙውን ሰው ቀልብ በሚስብ ቋንቋ በማማለል ቅን እና የዋህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኤርትራ ምድር
እንዲገቡ በማድረግ ስቃይና መከራ እያደረሰባቸው ይገኛል። ለዚህ ማስረጃ በቦታው ደርሰው ድርጅቱ
የሚያወራውና ሄደው በቦታው ያዩት የማይገናኝ መሆኑን ሲገነዘቡ አንዳንዶች በድፍረት ታጣቂ ሀይል አለ
በሚል ዋሽታችሁ አምጥታችሁናልና ወደ መጣንበት መልሱን የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የአካልና የስነልቦና
ስቃይና መከራ የደረሰባቸው ነው። ሌሎች ደግሞ ድርጅቱ ነጻነታቸውን በመግፈፍ የቁም እስረኛ አድርጓቸው
ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ ገሚሶቹ በመከራ ከኤርትራ ምድር የወጡ ሲሆን እነዚህ ወገኖች
እንደሚያስረዱት በርካታ ሰብዓዊ ጥሰቶች በኤርትራ በረሃዎች እየተፈጸመ ይገኛል። አሁንም ቀሪዎቹ
መውጣት እየፈለጉ በቁም እስረኝነት በኤርትራ በረሃ የምድር ላይ ሲኦል ውስጥ ይገኛሉ።

ለእማኝነት መጀመሪያ ዙር ለስልጠና ከወሰዷቸውና በብዙ ውጣ ውረድና እንግልት ስልጠና ተብየውን
ጨርሰው የለም ይህ ጊዜ ያለፈበት የትግል ስልት ነው በሚል ከተበተኑት አንዱ አቶ አንተነህ ጌትነት የሰጡትን
እማኝነት የሚከተለውን በመጫን ያዳምጡ።
http://ginbot7d.org/audio/Anteneh%20Interview%20Part%201.wma
http://ginbot7d.org/audio/Anteneh%20Interview%20Part%202.wma

2
ባለፈው ዓመት በውሽት ደልለው ከወሰዷቸው መካክል በለስ ቀንቶ ያመለጠው ቴዎድሮስ የሰጠውን
ምስክርነት እዚህ በመጫን ያዳምጡ።http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderPartf1.m3u
http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderFromPartf2.m3u

አሁን በቅርቡ ደግሞ ድርጅቱ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ውሸት ከሚችለው በላይ ሆኖበት
ድርጅቱን በመልቀቅ የድርጅቱን ውሸት እንዲሁም የሚያደርሰውን አፈና እና ስቃይ በማስመልከት ዳንኤል
የተናገረውን እዚህ ያዳምጡ።
http://ginbot7d.org/audio/YegedeyaMukera.mp3

በተለይ ቴዎድሮስን “ይህ ሰው አደገኛ ነው ይፈለጋል” የሚል ማስታወቂያ በከረንት አፌርስ የመወያያ
መድረክና ድረ-ገፅ ላይ አውጥተው እንደነበር የሚታወስ ነው። ይህ የሚያሳየው ሰውን የማሳደድ ተግባር ላይ
እንደተሰማሩም ጭምር ነው። ዳንኤልንም ይሳካላቸውም አይሳካላቸውም እያሳደዱት እንደሆነ የሚያሳዩ
መረጃዎች አሉ። ይህ የሚፈጸመው ኑሯቸውን አውሮፓና አሜሪካ ባደረጉና ፊደል በቆጠሩ ግለሰቦች መሆኑ
ደግሞ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። የመግደል ሙከራ ሊያደርግ ነበር በሚል የወንጀሉትን ሙሉቀን መስፍንን
በሚመለከት የሚያቀርቡት መረጃ እርስ በርሱ የተምታታ ከመሆኑም በላይ ወጣቱ በወያኔ የደረሰበት ግፍና
መከራ አንሶ የግንቦት 7 መሪዎች ለርካሽ ፕሮፖጋንዳ ሲባል እንዲህ አይነት ራስን ትዝብት ላይ የሚጥል ርካሽ፣
ዝቃጭና መናኛ የተለመደ አሉባልታ ከመንዛታቸው በተጨማሪ ለሻዕቢያ አሳልፈው በመስጠት በስቃይ ላይ
እንዳለ መረዳት ተችሏል። የዚህ ልጅ ደህንነት እንደ ኢትዮጵያዊ ሁላችንም የሚያሳስበን ሲሆን ለሚደርሰብት
ግፍና በደል ግንቦት 7 እና ኢሳት እንደ ድርጅት ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ ለወታደራዊ ስልጠና ከወሰዳቸው መካከል አንዳንዶቹን ጉድጓድ እያስቆፈረ፣
በቆፈሩት ጉድጓድ እንዲታሰሩ ማድረጉን ስንሰማና ገሚሶቹ ደግሞ ትግል በሌለበት እዚህ የሰው አገር ማሽላ
ቆራጭ እና መንገድ ሰሪ መሆን አንፈልግም ወደመጣንበት መልሱን ሲሉ የሚሰጣቸውን መልስና ድብደባ
ስንሰማ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከፍ ያደርገዋል። በመሆኑም ይህ በወገኖቻችን ላይ የሚደርስ አሰቃቂ የሰብዓዊ
መብት ጥሰት እንዲቆም፤ ያለፍላጎታቸው የታገቱ ወንድሞቻችንም በነጻነት መሄድ ወደሚችሉበት አገር
እንዲሄዱና ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ድርጅቶች በተለይም የድርጅት መሪዎች ሁኔታው ተጣርቶ
ለገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች
ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የኢትዮጵያ አንድነት በልጆቿ ፀንቶ ይኖራል!!!

ግንቦት 7 ዲሞክራቲክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 16, 2013 @ 5:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar