www.maledatimes.com ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

By   /   December 16, 2013  /   Comments Off on ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 42 Second
ይህ የወርሃ ታህሣሥ ብዙም ያልተነገረ ትውስታ ነው፡፡

በዘመናዊው ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁሌም የሚታወስ ወር ነው፡- ታህሣሥ፡፡

“የታህሣስ ግርግር” ይሰኛል፡፡ መንግስቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱበትና በአፄው ሥርዓት ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት በታህሣሥ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፡- ከታህሣስ 5- 7 ቀን 1953 ነው መፈንቅለ መንግስት ሙከራው የተቃጣው፡፡

ከዛሬ 53 ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡- የእነመንግስቱ ንዋይ ያልተሳካው መፈንቅለ መንግስት የተካሄደው፡፡ በወቅቱ የአጼው ሥርአት መፈንቅለ መንግስቱን የመሩትን በሞት እንዲቀጡ ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ በዚሁ መፈንቅለ መንግስት የታሳተፉ በርካታ ሰዎችንም ወደ ወህኒ ወርውሮ እንደነበር የታሪክ መዝግብት ያወሳሉ፡፡
Photo: ==== ብዙም ያልተነገረ ታሪክ  ===== 

እናስ?

ዛሬ “ልዩ” ትውስታ ላወጋችሁ ነው፡፡ የማወጋችሁ “ልዩ” ትውስታ በ1953 ዓም መፈንቅለ መንግስት ጋር ግንኙነት ያለው ቢሆንም፤ እኔን እጅጉን ደንቆኛል፡፡

ታሪኩ ከ1953 ዓም ሙከራው ተሳታፊዎቹ የአንዱ ነው፡፡ ብዙም የተወሳለት አይመስለኝም፡፡ በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው  ወደ ወህኒ ከተወረወሩት አንዱ ነው ባለታሪኩ፡፡ እናም በወህኒ ቤት 2 ዓመታት ተከርችሞበታል፡፡ ከእስርቤት ወደፍ/ቤት እየተመላለሰ ክሱን ሲከታተል የቆየው ይህ ሰው ከሁለት ዓመት እስር በኋላ የሞት ፍርድ ሊፈረድበት እንደሚችል ጠረጠረ፡፡ ስለዚህም “ሞት የማይቀርልኝ ከሆነ” ብሎ ከእስርቤት ለማምለጥ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ያሰበውንም አደረገ፤ ከእስር ቤት አመለጠ፡፡

ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ ከሃገሩ አልወጣም፤ ኧረ እንዲያውም ከዚሁ ከአዲስአበባ አልራቀም፡፡ እዚሁ አ/አበባ የአጼው መንግስት አፍንጫ ስር ተደብቆ ኖረ፡፡  ተደብቆ የኖረው ለአጭር ቀናት ወይም ወራት አይደለም፡፡ ድፍን 10 ዓመት ነው ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የሚገኘው የቅርብ ወዳጆቹ ቤት ተደብቆ የኖረው፡፡ ድፍን 10 ዓመት!!

ይህ ሰው ማነው?
ይህ ሰው መቶ አለቃ በቀለ ሰጉ ይባላል፡፡

ዛሬ እንደዘበት “የዱሮ” መፅሔቶችን ሳነብ ይህ ሰው ድፍን አስር ዓመት ደብቀው ላኖሩት ሰዎች (ኮሎኔል አስፋው አንዳርጌና ለወ/ሮ ሸዋአነሰሽ ደገፉ) የፃፈላቸውን ጠልቅ የምስጋና ደብዳቤ አገኘሁ፡፡ አነበብኩት፡፡ ገረመኝ፡፡ ለእናንተም ቃል በቃል ላቋድሳችሁ አስቤ ነበር፡፡ ጊዜ አጠረኝ፡፡ ወደበኋላ ላይ ግን ደብዳቤውን አስነብባችኋላሁ፡፡

እስከዚያው ግን አንድመንግስት ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርጎ፤ በዚሁም ሰበብ ታስሮ፣ ከታሰረበት አምልጦ፤ 10 ዓመት ሙሉ እዚያው መንግስት አፍንጫስር ተደብቆ መኖርን እያሰባችሁ ቆዝሙ፡፡ ማንን ታደንቃላችሁ? የተደበቀውን ሰው ወይስ ደባቂዎቹን?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 16, 2013 @ 6:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar