www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የሽብርተኝነት ጥቃት (በወሰን ሰገድ ገብረ ኪዳን ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የሽብርተኝነት ጥቃት (በወሰን ሰገድ ገብረ ኪዳን )

By   /   December 19, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የሽብርተኝነት ጥቃት (በወሰን ሰገድ ገብረ ኪዳን )

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 27 Second

ኢቲቪ ከምሸቱ 2 ሰዓት ዜና በኋላ ጥቂምት 3 ቀን 2003 ዓም የዋልያዎቹንና የናይጀሪያን ቡድን ጨዋታ በሚካሄድበት አ/አበባ ስታዲየም የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ አሸባሪዎች በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያትት ዶክመንተሪ አሳየን፡፡

በዶክመንተሪው እንዳሳየን አሸባሪዎቹ በሙሉ (ዜግነታቸው) ሱማሌያውያን ናቸው፡፡ የሸብር ተግባር ለመፈፀም ስልጠና የወሰዱት በአልሻባብ ነው፡፡ በዶክመንተሪው ውስጥ ቃላቸውን ሲሰጡ የሚታዩት አሸባሪዎች እንደሚናገሩት ወደኢትዮጵያ ቀድመው ገብተው ጥቃት የሚፈፅሙበትን ቦታ ሲያጠኑ ከርመዋል፡፡

– ደንበል ሲቲ ሴንተር፤ ፍሬንድሺፕ፤ ሸራተንን ….ወዘተ ሲያጠኑ አጥንተዋል፡፡

– ይህም ይሁን እንጂ አሸባሪዎቹ ወደኢትዮጵያ የገቡበት ዋናኛ ዓላማ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሚከበርበት ዕለት (ሕዳር 29 ቀን) ጥቃት ለመፈፀም እንደነበር ዶክመንተሪው ያወሳል፡፡ ዕቅዳቸው ተለውጦ ነው በአ/አበባ ስታዲየም ላይ ዒላማቸውን ያደረጉት፡፡ ወዘተ ወዘተ

– የእቅዱም ለውጥ እንደማይሳካ ሲያውቁ ወደተከራዩበት ቤት (ቦሌ አካባቢ) ተመለሱ፡፡ የታጠቁት ፈንጂ ሁለቱን አጋያቸው፡፡ የተቀሩት ተሰወሩ፡፡
– በጥቅሉ ዶክመንተሪው የሚያበስረን የተሰወሩትም በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው፡፡

መልካም ነው፡፡ ፖሊስና ደህንነት ወንጀለኞቹን መያዙና ሕዝብን መታደጉ መልካም ነው፡፡ ሆኖም ግን ጥያቄ አለኝ፡፡ የጥያቄዬ ምንጭ በራሱ በዶክመንተሪው የተጠቀሰው አባባል ነው፡፡

“ሁሉም አሸባሪዎች የኢትዮጵያ ፖስፖርትና መታወቂያ ይዘው ነበር” ይላል ዶክመንተሪው፡፡

እንደዛ ከሆነ ደህንነትም ሆነ ፖሊስ የሚጠበቅበትን አልሰራም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ማነው ፓስፓርት የሚሰጠው ወይም የሰጠው? ማነው መታወቂያ የሰጠው ? ለምን አልተያዙም? ወይስ አሰጣጡ እንደወንጀል አይቆጠርም?

እንደ እኔ እንደኔ ከመታኝ ይልቅ ያስመታኝ ነው አሸባሪ መባል ያለበት፡፡ ከደበደበኝ ይልቅ ዱላ ሰጥቶ ያስደበደበኝ ነው ወንጀለኛ፡፡ እና የዛሬው ዶክመንተሪ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ያላለው ለምንድነው? ነው የኔ ጥያቄ፡!

ወይ መብራትኃይል እዚህ ጥያቄ ላይ ድርግም አደረገው፡፡ ለምንድነው?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 19, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 19, 2013 @ 3:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar