www.maledatimes.com ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የዲሴምበር 2013 ዕትም ወጥቷል። እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ ዲሴምበር 28 5ኛ ዓመቷን ትደፍናለች – እንኳን አደረሰን። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የዲሴምበር 2013 ዕትም ወጥቷል። እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ ዲሴምበር 28 5ኛ ዓመቷን ትደፍናለች – እንኳን አደረሰን።

By   /   December 19, 2013  /   Comments Off on ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የዲሴምበር 2013 ዕትም ወጥቷል። እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ ዲሴምበር 28 5ኛ ዓመቷን ትደፍናለች – እንኳን አደረሰን።

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 23 Second
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የዲሴምበር 2013 ዕትም ወጥቷል። እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ ዲሴምበር 28 5ኛ ዓመቷን ትደፍናለች – እንኳን አደረሰን።የወሩን እትም ማየት ይፈልጋሉን እንግዲያውስ እኛም ለእርስዎ ብለን አቅርበንልዎታል እና ይህንን ይጫኑ የዘሃበሻን አምስተኛ አመት ለማክበር ይቻለን ዘንድ የእርስዎን እርዳታን እንሻለን እና እባክዎትን በዘሃበሻ ዌብ ሳይት የፔይ ፓል ፎርም ላይ የሚቻልዎትን ይለግሱን ።እኛም ለእርስዎ እንቆማለን እርስዎም ለእኛ ይቁሙ !
በዚህ በ2013 የመጨረሻው ዕትማችን ላይ የያዝናቸውን ቁምነገሮች እናስቃኛችሁ እና በPDF ፎርማት ሙሉውን ጋዜጣ ፕሪንት አድርጋችሁ ማንበቡን፤ ወይም በዲስክ ቶፕ ላይ ሴቭ አድርጋችሁ መኮምኮሙን ለናንተ ትተናል። በሚኒሶታ እና አጎራባች ስቴቶች ያላችሁ ጋዜጣዋን በነፃ በኢትዮጵያውያን ንግድ ቤቶች ማግኘት ትችላላችሁ።
– $44,000 ይላል አብይ ርዕሳችን። በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲን ሕንፃ ለመግዛት በተደረገ የገቢ ማሰባሰብ ምሽት በአንድ ቀን 44,000 ዶላር ተሰብስቧል። በዚህ ዙሪያ ሰፊ ዘገባ አለን። ኢትዮጵያዊነት በሚኒሶታ ከፍ ያለውን ቦታ እየያዘ ነው።
– የአትላንታው የዘ-ሐበሻ ወኪል ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ ኢሕአዴግ በኦጋዴን ስላከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በተመለከተ ያሰናዳው ጥልቅ ዘገባ በዓብይ ርዕሳችን ይዘነዋል።
– “በየወሩ መልዕክቴን በዘ-ሐበሻ በኩል የማስተላልፈው ራዕይ ታይቶኝ ነው” ትላለች ፓስተር ደስታዬ። ይህን ለምን እንዳለች ያንብቧት።
– የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን በማሰጠትና ለዜጎች ሞት የሚጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን ለቀቁ
– ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!!ተጨማሪ ማስታወሻዎችና ከኢትዮጵያ የወሰዱት ሽጉጥ መጨረሻ በጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ – አዳዲስ መረጃዎችን ስለ ማንዴላ ያቀብላችኋል።
– ዘ-ሐበሻ ሁሌም በምትወደስበት የጤና አምዷ
* የተወሰኑ የነቀርሳ ዓይነቶችን በኤችፒቪ ክትባት አማካይነት ይከላከሉ (MDH እና zehabesha በመተባበር ያቀረቡት ትምህርታዊ ዘገባ)
* በተለይ በበረዷማ ከተማዎች ውስጥ ለምትኖሩ የቫይታሚን ዲ ምስጢሮች /The Secret to Boosting Vitamin D Levels All Winter (ሊያነቡት ይገባል)
* ቦርጭን ማጥፊያ የምግብ ዓይነቶች
* የሐሞት ጠጠር ጉዳይ! ተተንትነዋል።
በሴቶች ጤና አምዳችን ደግሞ፦
* የሊሊ ሞገስን የማረጥ ዕድሜ ለውጦችሽን የምታስተናግጂባቸው 19 ምርጥ ጥበቦች (Menopause (Perimenopause) Symptoms,Treatments, Diet …)
* የ’ፍንዳታው’ አንጎል (በንዮሳይንስ መጽሔት ላይ የቀረበውን የባለሙያ ትንታኔ ተርጉመን ይዘነዋል)
በሃኪምዎን ያማክሩ (እንመካከር አምድ) ለ4 ጉዳዮች ምላሽ አግኝተናል
* “ባለቤቴ እንደምትወደኝ አውቃለሁ፤ የወሲብ ፍላጎት ግን የላትም፤ በዚህ የተነሳ ትዳሬ አደጋ ላይ ነው” – ምላሽ ይዘናል
* ለጨጓራ መላጥ (አልሰር) በሽታ መፍትሄው ምንድን ነው?
* እግሬ ላይ ጋንግሪን ሊወጣ ነው ወይ?
* ነጭ ጓደኛ ይዤ ፍቅር መስራት ጀመርን። ወዲያውኑ ብልቴ አካባቢ ያሳክከኝ ጀመር፤ ቢጫ ሽንት አየሁ” – ለዚህም የባለሙያ ምላሽ አለን።
በወንጀል ነክ ዜናዎቻችን፦
* በአሪሲ የ11 ወሩን ሕጻን ብልት የቆረጠች እናት 10 ዓመት ተፈረደባት
* የ3 ዓመት ሕፃን በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው 6 ዓመት ተፈረደበት
በስፖርት አምዳችን 3 ጉዳዮችን ይዘናል፦
* 4-1-3-1-1 ወይም 3-2-3-2 ወይም 3-3-3-1 1-1-3-1-1 ወይም 1-4-3-2 የማንችስተር ዩናይትድ ታክቲካዊ አማራጮች
* “ኢትዮጵያን አሸንፈን ለዓለም ዋንጫ በማለፋችን የቼልሲ ተጨዋቾች ደስታቸውን ገልፀውልኛል›› – ኬኔት ኦሜሮ (Kenneth Omeruo)
* የአርሰናሉ ሮዚስኪ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? ያንብቧቸው።
– በሳይኮሎጂ አምዳችን ላይ ለደስተኛ ሕይወት 25 ምርጥ ምክሮች አሉን ይማሩባቸዋል ብለን እናስባለን።
በጥበብ አምዳችን፦
* “ትወና መምሰል ብቻ ሳይሆን መሆንም ጭምር ነው” መሐመድ ሚፍታህ (ፋርማሲስት፣ ተዋናይ፣ የማስታወቂያ ባለሙያና የፊልም ፕሮዲዩሰር) ቃለ ምልልስ ይዘናል።
* ስለ አስቴር አወቀ ወደ ሚኒሶታ መምጣትም ዘገባ አለን።
ምን ይሄ ብቻ፡ ግጥሞች፣ አዝናኝ ጽሁፎች፣ ስለ አሜሪካ ኑሮ፣ ማስታወቂያዎች፣ የተለያዩ መረጃዎች የቁጥር 58 አካል ናቸው።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 19, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 19, 2013 @ 4:11 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar