www.maledatimes.com የኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚተረጉመውን ዲክሽነሪ የጻፉት አምሳሉ አክሊሉ አረፉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚተረጉመውን ዲክሽነሪ የጻፉት አምሳሉ አክሊሉ አረፉ

By   /   December 21, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚተረጉመውን ዲክሽነሪ የጻፉት አምሳሉ አክሊሉ አረፉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 12 Second

ለረጅም ዘመናት በህመም ሲሰቃዩ የቆዩት ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ በ83 አመታቸው ማረፋቸው ተገለጸ ።በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚተረጉመውን መጽሃፍ የተረጎሙት እኝህ ታላቅ ሰው ማረፋቸው ተሰምቶአል ። በህይወት ዘመናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት እና ምርምር ተቋም ውስጥ ለረጅም ዘመን ያገለገሉ ሲሆን መጸሃፋቸውም ለዘመናት ብዙ ተማሪዎችን እውቀት እንዲያፈሩበት ያስቻሉ ታላቅ ምሁር እንደነበሩ ይታወሳል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምሳሉ አክሊሉ ከጂፒ ሙስባክ ጋር ከጻፉት መጸሃፍ ሌላ በርካታ መጸሃፎችንም ቢጽፉም ለማሳተም የሚያስችል በቂ የሆነ የህትመት አጋዥ እቃዎች እና ሙያዊ ብቃት ያላቸው ሰዎች በአጠገባቸው ባለመኖራቸው ከእርሳቸው የእድሜ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ምንም ለማሳተም አለመቻላቸውን የቅርብ የስጋ ዝምድና ያላት አንድ ወገናቸው ለማለዳ ታይምስ ገልጻለች ።የቀብር ስነስራቱም እስከሚቀጥለው ቅዳሜ ድረስ ቆይቶ ከውጭ ያሉት ቤተሰቦቻቸው ከተሰባሰቡ በኋላ ሊፈጸም እንደሚችል ተገልጾአል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 21, 2013 @ 12:42 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar