www.maledatimes.com ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ

By   /   December 21, 2013  /   Comments Off on ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 17 Second

የአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበረው አቶ ተመስገን ጉላን በራሱና በወንድሙ ስም ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመገኘቱ ክስ የቀረበበት ሲሆን በፖሊስ ክትትል ስር የነበረው ወንድሙም ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለታል፡፡ ቀደም ሲል ተከሳሹ ሁለት ዶዘሮችን በ15ሚ.ብር መግዛቱን ደርሼበታለሁሲል አቃቤህግ መግለጫ መስጠቱ ይታወሣል፡፡
የ33 ዓመቱ የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ተመስጌን ጉላን ዓለሙ፣ በሌላ ስሙ ተመስገን ስዩም አሰፋ፤ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በግብረአበርነት በተያዙት የወልደሚካኤል ሃለፎም አጠቃላይ አስመጪና የፈሣሽ ትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት አቶ ወ/ሚካአል ሃለፎም፣ የታደለ ብርሃኑ አስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት አቶ ታደለ ብርሃኑ፣ ስራው ያልተገለፀውና እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ ሹመይ እንዲሁም የ24 አመቱ የ1ኛ ተከሣሽ ወንድም አቶ ካህሣይ ጉላን ዓለሙ ደግሞ በአንድ መዝገብ ተከሰዋል፡፡
በአቶ ተመስጌን ጉላን ላይ በተናጠል የቀረበው 1ኛው ክስ፤ ተከሣሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በተለያየ ሃላፊነት ላይ ተመድቦ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት ሲሠራ፣ አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ሲያገኘው ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን፣ በወንድሙ በካህሣይ ጉላን ስም በዳሽን ባንክ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ፤ በራሱ ስም ደግሞ በወጋገን ባንክ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በማስቀመጥ እና በማንቀሳቀሱ በአጠቃላይ በራሱና በወንድሙ ስም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ አስቀምጦ በመገኘቱ ተከሷል፡፡
ተከሣሹ በጓደኛው ብርሃኑ ዝናቡ ስም ስድስት ቦቴ መኪናዎችን ከነተሳቢያቸው፣ በአቶ ወ/ሚካኤል እና ታደለ ብርሃኑ አማካኝነት ከባንክ 10.5 ሚሊዮን ብር በመበደር ከራሱ 10.5 ሚሊየን ብር በመጨመር በድምሩ በ21 ሚሊዮን ብር ከሰኢድ ያሲን ኃላ.የተ.የግል ማህበር ገዝቶ መኪኖቹን በ2005 ዓ.ም ለተለያዩ ግለሰቦች በመሸጥ፣ በወንድሙ ስም ከቢዩ ኃ/የተ/የግ/ማህ ሁለት ዶዘሮችን በብር 15 ማሊዮን ብር መግዛቱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በወንድሙ ስም በቦሌ ክ/ከተማ 325 ሜ.ካ ቦታ ላይ የተሠራ መኖሪያ ቤት በማፍራቱ እና በ2.8 ሚሊየን ብር በመሸጡም ተከሷል፡፡
ቀሪዎቹ ተከሣሾች ደግሞ፣ አቶ ተመስገን ሙስና ፈፅሞ ያገኘው ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እያወቁ መኪኖቹ የሚገዙበትን ሁኔታ ሃሣብ በማፍለቅና በመርዳት፣ የባንክ ብድር እንዲገኝ በማመቻቸት እና በመበደር እንዲሁም በራሱ አስመጪና የትራንስፖርት ድርጅት ስር መኪኖቹ ተጠቃለው እንዲሠሩ በማድረግ አቶ ወ/ሚካኤል ሃለፎም ተጠያቂ ሲሆን አቶ ታደለ ደግሞ በሙስና ወንጀል የተገኘው ገንዘብና ንብረት እንዳይታወቅ ለማድረግ አቶ ብርሃኑ ዝናቡ እና ካህሣይ ጉባል የቀበሌ መታወቂያ እንዲያወጡ በማመቻቸት እና በቀበሌው መታወቂያ መነሻነት የተጠቀሡትን ወንጀሎች እንዲፈፅሙ በማድረጉ  በወንጀሉ በመሣተፉ መከሠሡ ተመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ፤ መኪኖቹ በስሙ እንዲገዙ፣ የባንክ ብድርም በስሙ እንዲበደር በማድረጉ ክስ የቀረበበት ሲሆን ወጣት ካህሣይ ደግሞ ለወንድሙ ውክልና ሠጥቶ በስሙ ገንዘብ እንዲያስቀምጥና እንዲያንቀሣቅስ እንዲሁም መኖሪያ ቤት እንዲገዛ በማድረጉ ተከሷል፡፡
ቀደም ብሎ በነበሩት ሁለት ቀጠሮዎች አቶ ተመስገን፣ አቶ ወ/ሚካኤል እና አቶ ታደሰ፤ ክሡ ተነቦላቸው መቃወሚያቸውን አቅርበው፣ አቃቤ ህግም ለመቃወሚያው መልስ የሠጠ ሲሆን ካህሣይ ጉላል ለመጀመሪያ ጊዜ ከትናንት በስቲያ ቀርቦ ክሡ ከተነበበለት በኋላ፣ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ከሌሎች ተከሳሾች ጋር አብሮ እያየው ነው፡፡
አቃቤ ህግ በተከሣሾቹ ላይ 14 የሠውና 14 የሠነድ ማስረጃዎችን ከክሡ ጋር አያይዞ አቅርቧል፡፡
ከትናንት በስቲያ የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛው ችሎት፤ በመዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ያስተላለፈ ሲሆን በእለቱ የቀረበው 5ኛ ተከሣሽ፤ የዋስትና መብቱ ተከልክሎ በቀጣይ ቀጠሮ ከጠበቃ ጋር እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት፣ መዝገቡን ለጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ -ምንጭ አዲስ አድማስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 21, 2013 @ 12:52 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar