www.maledatimes.com ወደ ፍቅር ጉዞ ወይስ ወደ ውሸት ጉዞ ፣የቴዲ አፍሮ ስራአስኪያጅ ውሸት እንዴት ይታያል ?በአንድ እራስ ሁለት ምላስ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወደ ፍቅር ጉዞ ወይስ ወደ ውሸት ጉዞ ፣የቴዲ አፍሮ ስራአስኪያጅ ውሸት እንዴት ይታያል ?በአንድ እራስ ሁለት ምላስ

By   /   December 21, 2013  /   Comments Off on ወደ ፍቅር ጉዞ ወይስ ወደ ውሸት ጉዞ ፣የቴዲ አፍሮ ስራአስኪያጅ ውሸት እንዴት ይታያል ?በአንድ እራስ ሁለት ምላስ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 27 Second

ወደ ፍቅር ጉዞ (The journey of love ) የተሰኘውን የሙዚቃ ዝግጅት ከበዴሌ ቢራ ጋር እንደሚሰራ ተደርጎ የተዋዋለበትን የፕረስ ሪሊዝ የተቀቀው በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ እንደሆነ ይታወሳል ሆኖም ግን ፣አላዋቂ ሳሚ አይነት ነገሮች በቴዲ አፍሮ እና በማናጀሩ በኩል ሲታዩ ምን ሊባል እንደሚቻል ለማወቅ ያስቸግራል ፤ይሄውም በኬኤምኤፍ የፕሮሞሽን ፕሮዳክሽን ጋር ባደረገው እሰጣ ገባ ክስ መመስረቱን ባሳለፍነው ወር መጀመሪያ ላይ የፕሮሞሽኑን ማናጀር አቶ ሞሃመድን የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል አነጋግሮ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ፣በዚህ ጉዳይ ላይ ከኤኮን ጋር  በዋሽንግተን ዲሲ ይደረጋል ተብሎ ለታሰበለት ኮንሰርት ዝግጅት አልፈልግም ብሎ ኮንሰርቱን መሰረዙን አያይዘን ገልጸናል ::ሆኖም ግን ከዚያም አልፎ ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ ከአዲካ ጋር ላለው ጉዳይ ሲጠየቅ እና ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ በሰጠው ምላሽ ከማንኛውም ሰው ጋር ያለውን ሁኔታ በሰላም እንደጨረሱ ተናግረዋል ።

ከጋዜጠኞች በኬ ኤም ኤፍ ጋር ባደረገው ጉዳይ ላይ አንስተው ጥያቄ ባይጠይቁትም ነገር ግን የቴዲ እና የኬኤምኤፍ ፕሮዳክሽን ክስ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ባሳለፍነው ሁለት ሳምንት መስማታችን የሚታወስ ሲሆን ይህንን አድበስብሰው ለማለፍ ሞክረዋል ::ክሱ ግን አሁንም በፍርድ ቤት እንደተያዘ ሲሆን ቴዲ ግን በሰዎች ሽምግልና ይሁንልኝ እያለ ልመና ላይ እንደነበር ይታወቃል ፣በዚህ አይነት የረጅም ጉዞዎችን የተጓዘው ቴዲ አፍሮ አሁንም ሌሎች ስህተቶችን በመድገም ሽምግልናን ሳያስከትል አይቀርም  ።

በሌላም በኩል በክፍያው ላይ አስመልክቶ በኢትዮጵያን አርቲስቶች እና ሙዚቀኞች እንዲሁም የተለያዩ የኪነጥበብ    ባለሙያዎች ለስራቸው የተከፈላቸውን ሲደብቁ ይታያሉ ይሄውም የሃገሪቱን የታክስ ስራ ለማጭበርበር እንዲያመቻቸው እና መክፈል ስለማይፈልጉ ፣በአጭር እና በቀልጣፋ ሁኔታ ሃብትን ማጋበስ ብቻ የሚሹ የጥበብ ሰዎች ስለሆኑ ብቻ ነው ፣ለዚህ ደግሞ በመንግስት አፋጣኝ የሆነ የተገለጸ የአሰራር ዘዴ ይዘው እንዲወጡ ማድረግ አለበት ፣ይህ  አይነቱ ስራ  የድብቅ ስራ የሌሎቹንም የኪነጥበብ ሰዎችን እና ሙያተኞችንም ሊጎዳ ይችላል ፣ በቴዲ አፍሮ በኩል ሊመለሱ የሚገባቸውን ስራዎችንም ለማናጀሩ አሳልፎ ሲሰጥ ታይቶአል ሆኖም ግን የአሰራሩ ዘዴ ስራ አስኪያጁ ካለ ባለቤቱ የመናጋር ሁኔታው እጅግ የጠበበ ሲሆን በእርሱ ጉዳይ ያሉትን ነገሮች የመምራትም ሆነ የመፈራረም ሃላነት ያለው በስራ አስኪያጁ ብቻ ነው ::

በሌላም በኩል ከሜታ ቢራ ጋር ባደረገው ውል ጥቁር ሰው በተሰኘው አልበም ላይ በተለጠፈው የሜታ ቢራ ማስታወቂያ ከፍተኛ ጭቅጭቅ የተነሳ እንደነበር እና ቀድሞ ማናጀር የነበረውንም አቶ አዲስ ገሰሰንም እስከ ማባረር የደረሰበት ተጭበርብሬአለሁ በሚል እና ለሜታ ቢራ ማስታወቂያ የማልፈርመው ዘፈኖቼን የሚሰሙት ብዙሃኑ እድሜአቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ናቸው ሲል ተደምጦ ነበር ዛሬ ግን ምን ነካው የሄኛው የለስላሳ መጠጥ አከፋፋይ ነውን ? በአንድ እራስ ሁለት ምላስ የሆነ አመለካከት እንዴት ሊታይ ይችላል ?አላዋቂ ሳሚ ማለት ይህ አይደለምን ?የበለጠ በረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ »http://www.diretube.com/diretube/teddy-afro-journey-of-love-concert-media-release-video_95c7b9f24.html#.UrX26PRDvO0

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 21, 2013 @ 2:58 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar