www.maledatimes.com ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው? (ክፍል አንድ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው? (ክፍል አንድ)

By   /   December 23, 2013  /   Comments Off on ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው? (ክፍል አንድ)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 54 Second
በስለሺ ሐጎስ
ዳኞቹ 1 ሰዓት አርፍደው 4፡00 ላይ ችሎቱ ተሰየመ፡፡ ወዲያውኑ ውሳኔው ማለቁንና ይሁን እንጂ በኮምፒውተር ተጽፎ ስላላለቀ ከሰዓት በኋላ እናርገው አሉ፡፡
በዚህ ጊዜ የእነውብሸት ጠበቃ አቶ ደርበው “ከሰዓት ሌላ ቀጠሮ ስላለኝ አልችልም” ብለው ከአራት ቀን በኋላ ለታሀሳስ 21 እንዲሆን አማራጭ አቀረቡ፡፡ ዳኛው ግን አልተቀበሉትም፡፡ “እነዚህ ሰወች ያሉት በማረሚያ ቤት ነው፤ ቀጠሮው ከሚራዘም 7 ሰዓት እንገናኝና እስከ 8፡00 እንጨርሳለን” የሚል አማራጭ አቅረቡና በዚሁ ተስማሙ፡፡
የዳኛው ንግግር የሆነ ጥሩ ነገር ሊኖር ይችላል የሚል ተስፋ ስላጫረብን ሁላችንም ከዚያው ሳንወጣ ሰዓቱ እስኪደርስ መንቆራጠጥ ያዝን፡፡…
አይደርስ የለ ሰዓቱ ደርሶ ችሎቱ በሚሰየምበት አዳራሽ ተኮለኮልን፡፡ ዳኞቹ ግን በሰዓቱ የሉም፡፡ ግማሽ ሰዓት አለፈ፤ አልመጡም 8 ሰዓት ሲሆን ሁላችንም ቀጠሮ አለኝ ያሉትን ጠበቃ ደርበውን እያየን መሳቀቅ ያዝን፤ ሰዓቱ እየነጎደ ነው፤ 9 ሰዓት ሆነ፡፡ ዳኞቹም አልመጡም ጠበቃ ደርበውም አልሄዱም፡፡ 9፡45 ላይ ዳኞቹ መጡ፡፡ አቶ ደርበው ግን ቀሩ፡፡
ዳኛው ስለማርፈዳቸው ምንም ሳይሉ አሁንም ጽሁፉ ስላልደረሰ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት አጀንዳቸውን ማገላበጥ ያዙ፡፡ “አራት ቀን ምን ሲደረግ ይራዘማል” ያሉት ዳኛ ከ23 ቀን በኋላ ለጥር 10 2006ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተው ዕለቱና ችሎቱ አበቃ፡፡ ተስፋችንም እንዲሁ፡፡24
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 23, 2013 @ 6:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar