www.maledatimes.com የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ባለሥልጣን በመርካቶ የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር ድክመት እንደነበረበት አመነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ባለሥልጣን በመርካቶ የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር ድክመት እንደነበረበት አመነ

By   /   December 24, 2013  /   Comments Off on የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ባለሥልጣን በመርካቶ የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር ድክመት እንደነበረበት አመነ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 26 Second

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ባለሥልጣን በመርካቶ የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር ድክመት እንደነበረበት አመነ

-ፖሊስ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለሥልጣን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ከደረሱ

አደጋዎች ውስጥ ከፍተኛና ትልቁ የተባለውን የመርካቶ እሳት አደጋን ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት ደካማና የቅንጅት ችግር እንደነበረበት አመነ፡፡ በአደጋው አምስት የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ጨምሮ 25 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በባለሥልጣኑ ማረጋገጫ የተሰጠባቸው 45 ሱቆችና አምስት መጋዘኖች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡

ባለሥልጣኑ እንዳመነው ከሆነ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር መመርያ ይሰጡ የነበሩ አመራሮች መናበብ ተስኗቸው በአግባቡ ሊሠሩ አልቻሉም፡፡ ይህ በመሆኑ አደጋው ተቋሙን የፈተነው እንደነበር ኮማንደር አለነ ገልጸዋል፡፡ ተቋሙ በሰው ኃይልና በማቴሪያል ያለው አቅም ውሱን መሆኑም አደጋውን ለመቆጣጠር እንዳስቸገረው ጠቁመዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮማንደር አለነ ገብሩ ባለፈው ረቡዕ በማዘጋጃ ቤት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በአደስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ ጆንያ ተራ (ቦምብ ተራ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ኅዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡15 ሰዓት ላይ 8፡30 ሰዓት እሳቱ እንደተነሳ መረጃዎች ይጠቁማሉ) የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ውድመት አስከትሎ አልፏል፡፡

ባለሥልጣኑ የአደጋው ጥሪ ለባለሥልጣኑ የደረሰው 9፡15 ሰዓት ደርሶ፣ በሦስት ደቂቃ ውስጥ በቦታው ተገኝቶ አደጋውን ለመቆጣጠር እንደሞከረ ኮማንደር አለነ አስታውቀዋል፡፡ አሥር የእሳት አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎች ቢሰማሩም፣ እሳቱ እየጠፋና መልሶ እያገረሸ እስከ ኅዳር 27 ቀን 2006 ዓ.ም. መታየቱ የሚታወስ ነው፡፡

የተፈጠረውን የእሳት አደጋ ለመከላከል አስቸጋሪ ከነበሩት ምክንያቶች ውስጥ የውኃ መስመሮች ባዶ ሆነው መገኘት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮች ከሚቃጠሉት ቤቶች አካባቢ አለመቋረጥ፣ የመንገድ መዘጋጋትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መቆራረጥ በዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ የተጠቀሱት ናቸው፡፡

ይህም ሆኖ ጥሪ በደረሳቸው በሦስት ደቂቃ ውስጥ ደርሰዋል የተባሉት የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ዳተኛ ሆነው መታየታቸውና ትዕዛዝ አልተሰጠንም ማለታቸውን የአደጋው ተጎጂዎች ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በከፋ ሁኔታ ጉቦ ሲጠይቁና ሲደራደሩ የነበሩ ሠራተኞች መታየታቸውንም የእሳት አደጋው ሰለባዎች ለከንቲባ ድሪባ ኩማ ጭምር አስታውቀዋል፡፡

ይህንን በማስመልከት ኮማንደር አለነ ምንም የተጨበጠ ነገር ሊገኝ አለመቻሉን ተናገረዋል፡፡ ማስረጃም አልቀረበም ብለዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዪን እየመረመረው መሆኑን ሪፖርተር ከአዲስ ከተማ ፖሊስ መምርያ ያገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡ በተለይ በገንዘብ ሲደራደሩ ነበሩ ያላቸውንና በቦታው ቶሎ ደርሰው መመርያ አልተሰጠንም ያሉትን በማስመልከት ማስረጃ ማሰባሰቡን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነና የአደጋውን መንስዔ ገና እያጣራሁ ነው ያለው ፖሊስ፣ የንግድ ሱቃቸውን ሲያስበይዱ በነበሩ ሰዎች ምክንያት እሳቱ ተነስቷል ከሚለው መረጃ በመነሳት ሁለት እህትማማቾችና አንድ ወንድማቸው በቁጥጥር ሥር አውሎ ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡ በአያታቸው ቤት ውስጥ ይነግዱ የነበሩት ሦስቱ የቤተሰብ አባላት እያንዳንዳቸው የአምስት ሺሕ ብር ዋስ እንዲጠሩ የታዘዙ መሆናቸውንና የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኮማንደር አለነ ከክረምቱ ወራት ጀምሮ እንደ አዲስ የተደራጀው የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን፣ ከሲቪል አደረጃጀት ወደ ፓራሚሊታሪ መዋቅር እንዲሸጋገር መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ይህም የሆነው የሲቪል ሠራተኞች ግዳጅ ለመወጣት የሚያሳዩት ዲስፕሊን ደካማ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ መጠነ ሰፊ አደጋ ቢያጋጥማትና በአንድ ጊዜ በርካታ አደጋዎች ቢከሰቱባት በቀላሉ መቆጣጠርና መከላከል የምትችልበት አቅም እንደሌላት የመርካቶ አደጋ አመላካች መሆናቸውን ብዙዎች እንደ ሥጋት ያዩታል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 24, 2013 @ 2:53 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar