www.maledatimes.com የህወሃት ጥበበኞች እና የአምልኮ እይታቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህወሃት ጥበበኞች እና የአምልኮ እይታቸው

By   /   December 26, 2013  /   Comments Off on የህወሃት ጥበበኞች እና የአምልኮ እይታቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 37 Second

ሰሞኑን በደማቅ ሁኔታ የአለምን ህዝብ አይን እና ጆሮን የሳበው የአፓርታይድን ስርአት ገርስሠው ለህዝባቸው እና ለሃገራቸው እንዲሁም ለተቀሩት አለማት የህዝብ ኩራት የነበሩት የኔልሰን ማንዴላ ህልፈተ ህይወት እንደነበር ማንም የሚረሳው አይደለም ። ይህ ዕርሳቸው ህልፈተ ህይወት የመላው አለምን መንግስታት እና የአለምን ህዝብ ከመሳቡም በላይ እድሜ የሚጨመር ቢሆን ሊጨምርላቸው የሚችል ህዝብ እንደሆነ በፍቅራቸው አሳይተዋል ። ማንዴላ እና ስራዎቻቸውን ስናስብ በአፓርታይድ ስርአት ውስጥ በነበሩት የአፍሪካ ሃገሮች ላይ ይደርስባቸው የነበረውን የዘረኝነት ጭቆና ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ያደረጉት የህይወት መሰዋእትነት ክፍያ አሌ የማይባል የትየለሌ እንደሆነ የትግሉን መራራነት ያለፉት ወገኖች ብቻ ያውቁታል ።

ታዲያ አፍሪካ አገራቶች ለደረሰባቸው ጭቆና የትግል ስልታቸው በማንዴላ የሰላም አካሂያድ ባይፈታ ኖሮ ዛሬ ደቡብ አፍሪካ የደረሰችበት ደረጃ ባልደረሰች ነበር ለማለት ያስችላል ምክንያቱም የሰላማዊ ድርድሩ የቂም በቀል መልስ ሳይኖረው ፣ዘር ከዘሩ ሳይለይ ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ተከብሮ የሚኖርባት አንዲት ደቡብ አፍሪካዊት አገር ለመፍጠር የተደረገ መሰዋእትነት እንደሆነ የአለም ምሳሌ የሆኑት ኔልሰን ማንዴላ የሰላም አርማ የሆናቸውን እጃቸውን ከፍ አድርገው ሰላም ሲሉ ዘምረውለታል ፣ታዲያ እንዲህ እንዲህ እያለን ስለ ማንዴላ እና የትግል ህይወታቸው እናንሳ ብለን ካልን ብዙ ጊዜያቶች ሊያስፈልጉን እንደሚችሉ እና ጊዜውም ላይበቃን ይችልም ይሆናል ።ነገር ግን ለዚህ ርእስ መነሻ ወደ ሆነው ጉዳይ ስናመራ የወያኔ ቆንጮ የነበረው እና ከአመት በፊት የእልፈተ ህይወቱ የተነገረለት መለስ ዜናዊን አስመልክቶ በአይጋ ፎረም ላይ የተለጠፈው እና አንድ የፌስቡክ ወዳጄ ያጋራኝን ምስል እና ጽሁፍ ሳይ እኔም የበኩሌን ሃሳብ እንድሰነዝር አስገደደኝ ፣ማገናዘብ የተሳነን ዜጎች ነን ማለት ነው ብዬ ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ በኋላ መልሼ ለምን እንዲህ ከማለት ልዩነቶቹን በጥቂቱ ብሰነዝረው ሊረዱኝ ይችላሉ እና ሃሳቤን ላስቀምጠው ብዬ የእጄን ብእር ከወረቀት አወዳጀሁ።
ይሄውም “መለስ ህግ ሳይሆን ሀዋሪያ ነው ምን አልባትም በ2000 አመት ውስጥ አንዴ ሊደገም የሚችል መሪ” ይላል ሃሳቡ ፣በጣም ያስቃል ግን አንዳንድ ጊዜ ልንፈርድ የማንችለው ነገር ላይ እንደርሳለን ፣ለምንድ እንደሆነ ባላውቅም መለስን ከሃዋርያቶች አንዱ አድርገው ያለሙበት ምክንያት ባይገባኝም ልክ እንደ ጣኦት ስለሚያመልኩት ብቻ እንደሆነ  ግልጽ ሃሳብ ይሰጣል ። ሃዋርያቶች ወደዚህ ምድር ከመጡ ረጂም ዘመናትን አስቆጥረዋል ፣የመጸሃፍ ቅዱስ ህግጋትን ለህብ ካስተማሩ በኋላ ማናቸውም ሃዋርያቶች ይህችን ምድር እስከ ዘለአለሙ ተሰናብተዋል ከዚህም በኋላ የሚመጡትም  ሃዋርያቶች ሳይሆኑ ተከታዩቻቸው  እንጂ ሃዋርያቶች ሊሆኑም አይችሉም ፣ታዲያ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ማለቱን ስናይ እውነትም ጊዜው ደርሶአል ያሰኛል ፤  “ልጄ ሆይ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ ፣ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ ፣እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና ደምም ለማፍሰስ ይፈጥናሉና መርበብ በወፎች አይን ፊት ከንቱ ትተከላለችና እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ ።
      እንዲሁ ይህ መንገድ ትርፍን ለማግኘት የሚሳሳ ሁሉ ነው የባለቤቱን ነፍስ ይነጥቃል ጥበብ በጎዳና ትጮአለች በአደባባይ ድምጿን ከፍ ታደርጋለች  በአደባባይ ትጣራለች በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች  እናንተ አላዋቂዎች እስከመቼ አላዋቂነትን ትወድዳላችሁ ?ፌዘኞች ፌዝን ይፈቅዳሉ ?ሰነፎችም እውቀትን ይጠላሉን?” ይላል በመጸሃፈ ምሳሌ        እውነት ስለ መለስ ስንናገር የምናውቀውን እና ለህዝብ ያደረገውን እያገናዘብን እና መልካም ስራውን ከመጥፎው ጋር እያወዳደርን የገለጽንበት ወቅት አለን ? ካለስ የትኛው ይጎላል? እውነት አለማወቃችን ይሆን እንዲህ የሃዋርያትን ቦታ ልንሰጠው የቻልነው ወይስ እኛም የጣኦቱ አምላኪዎቹ ሆነን እርሱ የሚመለክበት ግኡዙ ጣኦታን ነው ? 
ማንዴላ እና መለስ ከአንድነታቸው ልዩነታቸው ይሰፋል እና ልዩነቶቻቸውን ላስቀምጥ በመጀመሪያ   ማንዴላ ለአፍሪካውያኖች በሙሉ በአፓርታይድ ስርአት ለተጨቆኑ ዜጎች የታገሉ ታላቅ ሰው ሲሆኑ መለስ ዜናዊ  ትግል ሃርነት ትግራይ በሚል ለአንድ ብሄር የታገለ  ነው  ማንዴላ 27 አመታት በእስር ሲማቅቁ  መለስ በባንክ ዘረፋ ላይ ተሰማርቶ ግዳጁን ሳይወጣ ፈርጥቶ የሮጠ ደካማ ታጋይ ነበር ፣ ማንዴላ ከበላዮቻቸው የነበሩትን የነጭ ባለስልጣናትን  ብበሰላማዊ መንገድ ሰላም ለመፍጠር ድርድር ሲያደርጉ መለስ ዜናዊ በጅምላ እንዲገደሉ ያዘዘ መንግስት ነበር  ማንዴላ ለአንድ ተርም ብቻ  በመንግስት አስተዳደርነት ቆይተው ከአሁን በኋላ በቃኝ ብለው ሲወርዱ መለስ ለሃያ ሁለት አመታት ገዝቶ በሞት ተሸንፎ ከስልጣን የወረደ መሪ ነበር ፣ ማንዴላ የሃገራቸው ህዝብ ጥቁር ነጭ ብሎ እንዳይለይ የዘር መከፋፈል እንዳይኖር በአስቸኳይ አዋጅ ሲያውጁ መለስ ዘሮችን የከፋፈለ ሃገር የከፋፈለ ፣እና የሰዎችን ሰላም የነሳ መንግስት ነበር የማንዴላ መንግስት በነበሩበት ወቅት የነጮችን ታሪክ ለልጅ ልጅ እንዲቀር ማንም እንዳይነካው ሲያውጁ መለስ የኢትዮጵያን ታሪክ ያፋለሰ እና ያበላሸ መንግስት ነበር  ታዲያ አንድነታቸው ከማንዴላ ጋር ሲተያይ ሁለቱም የአፍሪካ አገር መሪዎች ሲሆኑ በመካከላቸው ያለው ሰፊው ልዩነት ፣ከህዝብ ክብር ለማንዴላ ሲያስገኝ ለመለስ ደግሞ በስራው ጥላቻን አስገኝቶአል ፣በመለስ ቀብር ስነስርአት ህዝብ በገንዘብ እና በግዳጅ ቀብር እንዲወጣ ሲታዘዝ ለማንዴላ ቀብር  ግን ከታላላቅ ባለስልጣኖች  ውጭ የአለም ታዋቂ ሰዎች ባለሃብቶች የፊልም ባለሙያዎች የሙዚቃ ባለሙያዎች የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢዎች ለቀብራቸው በክብር በመገኘት ስንብት አድርገዋል ፣ለመለስ ይህ በአለም አቀፍ ህዝቦች ታውሶአል እንዴ ትብሎ ቢጠየቅ አረ እሱ ማነው ? የሚል ጥያቄ ያመጣል ታዲያ ሃዋርያነቱ ለማን ይሆን ? እኔም ነገር አላብዛ ስለዚህ ወዳጄ ሰሚር አያይዞ ከለጠፈልኝ ጽሁፍ ጋር እኔም እሰናበታችኋለሁ መልካም ቆይታ  የሰሚርን ጽሁፍ ከዚህ በታች ያዩታል እና  ያንብቡት ።

 “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሙዋሽሽምም ” is killing አረ አይተ አይጋ ፎረም ሼም እወቁ ምን አልባት ሼምየለሽ ከማል ይሆን እንዴ እቺን ፅሁፍ የፃፉት?

,,,,,,,,መለስ ህግ ሳይሆን ሀዋሪያ ነው ምን አልባትም በ2000 አመት ውስጥ አንዴ ሊደገም የሚችል መሪ ,,,,,,,,,እያለ ታዋቂ የመንግስት ጋዳፊ እንደሆነ ይቅርታ ደጋፊ እንደሆነ የሚነገርለት አይጋ ፎረም ድህረገፅ ስለ ሀዋሪያው መለስ ፅሁፉን ይቀጥላል,,,,
እኛም ይህንን አንብበን የአይጥ ፎረም ብለነዋል,,,,,

A Humorous picture of Zenawi’s resurrection

‹‹መለስ ዛሬ የለም፡፡ አዲስ ጊዜ ነው፡፡ ደስ ብሎኛል፤ ቪዛዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተሰጥቶኛል፡፡››…ማዳም አና ጎሜዥ <<ለመንግስታችን ዮዲት ጉዲት ለተቃዋሚው ደግሞ ሀና ጎበዜ >> የነበረችው ወ/ሮ ናት እንግዲህ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዲህ ያለችው።

እኛም በተራችን የአና ጎሜዝን ልብ በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይደበዝዝም እንበል እንዴ ?

ያላቻ ጋብቻ

ጉዳዩ በህወሀት ደጋፊዎች እና በOromofirst ግሩፖች መካከል የተፈፅመውን ያላቻ ጋብቻ ይመለከታል።
ምን አልባትም political prostitution (the carpet crossing in pursuit of ambitions – hate monger) ሊባል ይችል ይሆናል።
እንግዲህ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ብሂል polarized የሆኑ ቡድኖች አሸሼ ገዳሜ እያሉ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ለነገሩ እነዚህን ባላንጣዎች አንድ በማድረግ አፄ ሚኒሊክ ከመቶ አመት በሁዋላም ታሪክ ሰርተዋል። viva Minilik viva Teady Afro ብለን እንቀውጠው እንዴ ? ማነህ እንትና አንድ አባዱላውን በደሌ እስቲ አምጣ አሉ ጋሽ ወርቁ። አንድ ጊዜ በዌብሳይቱ ላይ ያሉትን ማስታወቂያዎችን ይጫኑ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 26, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 26, 2013 @ 1:35 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar