www.maledatimes.com ብኣዴን – የሕወሓት አሽከሮች እና ለውጥ ፈላጊዎች ተፋጠዋል:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ብኣዴን – የሕወሓት አሽከሮች እና ለውጥ ፈላጊዎች ተፋጠዋል::

By   /   December 26, 2013  /   Comments Off on ብኣዴን – የሕወሓት አሽከሮች እና ለውጥ ፈላጊዎች ተፋጠዋል::

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 49 Second

by ‎Miniliksalsawi‬  በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዬ ሲጠራ የደፈረሰው ይጠራል ተብሎ ይጠበቃል::‪
የጄነራል አበባው ስልክ መጠለፍ አሁንም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ሽኩቻ እና ዘረኝነት ያመለክታል::

ምንሊክ ሳልሳዊ :- የሟቹን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሕወሓት እና በብኣዴን መካከል ልዩነቶች የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ተከስተው አሁንም በስፋት ቀጥለው ይገኛሉ::የተለያዩ የብኣዴን ሰዎችን በሰብብ አስባብ የሚያንጠባጥበው ሕወሓት አሁንም አሽከሮቹን አሰማርቶ ለውጥ ፈላጊዎችን ወደ ገደል ለመግፋት አየተሯሯጠ ነው:: የብኣዴን ካድሬዎች የለውጥ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ተከትሎ ከሕወሓት አሽከር ከሆኑት ጋር በስብሰባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስብሰባው እንደተበተነ ታውቋል::
FDRE States flags
በዚህ ሳምንት ውስጥ ሁለት ግዜ የካድሬዎች ስብሰባ ተጠርቶ የመጀመሪያው በሕወሓት አሽከሮች እና በለውጥ ጠያቂዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ስብሰባው ሲበተን …ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው ስብሰባ በከፊል ካድሬዎቹ ስላልመጡ ለሚመጣው ሳምንት የተላለፈ መሆኑን ታውቋል::በሕወሓት አሽከሮች እና በብኣዴን ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል::
አዲስ በወጣው እቅድ መሰረት በአማራው ክልል በድጋሚ አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ እንደሚደርግ እና በዚህ መካከል አስቸጋሪ እና አድመኞች የጸረ ሰላም እና የጸረ ሕዝብ ሃይሎችን የመደምሰስ እንዲሁም በአዲሱ የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አስፈላጊው ጥቅማጥቅሞችን ለአዳዲስ አባላት መስጠት የሚል ይገኝበታል::ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱ ችግር በፓርቲው ላይ የሚፈጥሩ ካድሬዎችን በማስወገድ በአዳዲስ መተካት የሚሉ እቅዶች ተይዘዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት የጦር መኮንኖች የአማራ እና በኦሮሞ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ዘረኝነት እያራመዱ መሆኑ ታውቋል:: የተለያዩ ማእረጎች የስልጣን እርከኖች እና ወታደራዊ ጥቅማጥቅም የሚሰጠው ትግሪኛ ተናጋሪ ለሆኑ ብቻ ነው ሌሎቹ ምንም የሚወረወር ፍርፋሪ የላቸውም::በሰራዊቱ ውስጥ ዘረኝነት መንሰራፋቱ እንዲሁም አደርባዮች መስፋፋታቸው አስፈላጊውን ለውጥ እንዳይመጣ ያደረገው መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና ጄኔራል አበባውን ጨምሮ የቀድሞ የብኣዴን ታጋዮች እና የዛሬ የጦር ሰራዊቱ መኮንኖች ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ሊፈጥሩ ይሽላሉ በሚል ስልካቸው ተጠልፎ እንደነበር ታውቋል:: የከፍተኛ መኮንኖቹ ስልክ መጠለፉ እንደታወቀ እሰጥ አገባዎች የተደረጉ ሲሆን ስብሰባ ይጠራል ያሉት የሕወሓት ጄኔራሎች አስካሁን ዝምታን መርጠዋል:; ይህ በሰራዊቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሽኩቻ እና ዘረኝነት ተስፋፍቶ መቀተሉን ያመለክታል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል:: በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሰፋ ያለ ዘገባ ይቀርብበታል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 26, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 26, 2013 @ 5:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar