www.maledatimes.com የማለዳ ወግ ! አይ የእኛ ነገር የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ ! አይ የእኛ ነገር የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው !

By   /   December 29, 2013  /   Comments Off on የማለዳ ወግ ! አይ የእኛ ነገር የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው !

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 43 Second

ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በፈረንጆች አመት በዋዜማ ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?

ባለሁበት የሳውዲ ምድር በአለም እንደ ጨው የተበተንን የዚያች ሃገር ዜጎችን ትኩረት ሳቢ ብቻም ሳይሆን አስጨናቂ ቀንን ተፋጦ ማወጫ ያጣ ወገን ጩኸት ደምቆ እንዳይሰማ የእኛ ነገር አልተመቸውም ! ሌላው ቀርቶ ጥቂት ያገባናል ያልን መረጃን በቀላሉ እየተለዋወጥን በምንገኝባቸው ማህበራዊ ገጾች ከአንድ ከአንድ አለም ጫፍ ወደ ሌላው የአለም ጫፍ በብርሃን ፍጥነት የሚሰራጨው የጥላቻ ፖለቲካ የመረጃ ቅብብል ሜዳችን እንዳያጨልምብን ሰጋሁ! ከሁሉም የሚያሳዝነው የምንወዳቸውና የምናከብራቸው የተማሩ የተመራመሩት ወገኖቻችን ሳይቀሩ በዝብሪቱ አዙሪት ተጠልፈው መግባታቸውን እየታዘብን ነው ። … በማህበራዊ ገጾች የተበተነውን የጥላቻ መረጃ ከስርጭቱ ባህር እየጨለፉ ይናኙት ይዘዋል ። እንዲህ እየሆነ …አንዱ ያሰራጨውን እነርሱም የታላቅነታቸው መገለጫ የሆነች አስተያየታቸውን ሞነጫጭረው አሳለፈው ይለጥፉ ይረጩት ይዘዋል! የማይጠቅም የማይበጀንን … የእኛ ነገር!

ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ሳውዲ ውስጥ ያለው ወገናቸው አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን የረሱት ይመስላል ። በጅዳ የሽሜሲ መጠለያ ፣ በጅዳ አየር መንገድ ፣ በጅዳና በጀዛን እና በሪያድ እስር ቤቶች በወህኒው እንግልት ድምጻቸውን የሚሰማ ያጡ ፣ በኮንትራት መጥተው በአረብ አሰሪዎቻቸው ወደ ሃገር እንዳይገቡም ሆነ የፈለጉትን እንዳያደርጉ እንደ ግዞት የተያዙ በርካታ የጨነቃቸው ወገኖች : የአረብ ቤት አጽድተው ባጠራቀሟት ገንዘብ ወደ ሃገር የላኩት እቃ በአንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ካርጎ ለበርካታ ወራት ከሳውዲ ግልጋሎት መስጠት መቋረጥ እዚህም እዚያም የወገን ጩኸት ተበራክቷል … ! ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ከባቢ ያለን ወገኖች ከአፍንጫችን ስር ያሉትን ወገኖቻችን በሰላም ወደ ሃገር የሚገቡበትን መንገድ ከማፈላለግ ባለፈ አነሰም በዛ በዚህ ክፉ ቀን በወገን ድጋፍ የተሰማሩ ወገኖችን ስም እያነሳን ከመደቆስ ፣ የክፋት ፣ የጥላቻ መርዛችን በመርጨት ብቻ ሳይወሰን በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን ስራ ባላስፈታው የጥላቻ ፖለቲካ ተጠልፈናል ። የዝብሪቱን መረጃ እየተቀባበልን የመረጃ መቀበያ ማህበራዊ ገጻችን ማጉደፍ ይዘናል ! አይ ! የእኛ ነገር …

የእኛ ነገር እንዲህ ቢሆንም ፣ እንዲህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ! ዛሬ ፋታ የማይሰጥ የወገን ጭንቀት ሊያስጨንቀን ፣ ህመሙ ሊያመን ፣ ቁስሉ ቁስላችን ፣ ሞቱ ሞታችን ሊሆን ይገባል ! ይህን ማድረግ ባይቻለንና በውን ያሰብነው ተሳክቶ ግፉኡን ወገን ልንታደገው ባይቻለን ጩኸቱ እንዳይሰማ ግርዶሽ የሚሆነንን የጥላቻ ፖለቲካ አንከተል ! የክፊዎች ጭራ አንሁን ! እየተረጨ ያለውን ሰሞነኛ ዝብሪቱን እኛም ተቀብለን ወግና እያሳመርን መርዙን መረጃ እያሽከረከርን የወገን ጩኸቱን አናፍነው! የወገን ጩኸቱን አንቀማው !

ሌላ ምን እላለሁ …

እስኪ እሱ ይታረቀን !

ነቢዩ ሲራክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 29, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 29, 2013 @ 2:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar