www.maledatimes.com የቴዲ ምላሽ አሳማኝ ነውን? =~=~=~=~=~=~ሬገን ሰሎሞን in Hurdal, Norway - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቴዲ ምላሽ አሳማኝ ነውን? =~=~=~=~=~=~ሬገን ሰሎሞን in Hurdal, Norway

By   /   December 30, 2013  /   Comments Off on የቴዲ ምላሽ አሳማኝ ነውን? =~=~=~=~=~=~ሬገን ሰሎሞን in Hurdal, Norway

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 30 Second

እንደገና ይታኘክ ልመልሰው እስቲ:: የሆላንዱ ቴሌግራፍ ጆሮ የገባው የ#ቦይኮት#በደሌ ዜና ሄይንከን ቴዲ አፍሮ ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሚል የለቀቀውን መግለጫ እንዲሰጥ እንዳስገደደው እገምታለሁ::

የቴዲ ምላሽ ከዚህ በፊት ፈረመ ተብሎ ለቀረበበት ስሞታ የሰጠውን ምላሽ የሚመስል ቃና አለው::”ከዚህ ዉጪ እኔ በማላዉቀዉ ሁኔታ መፅሔቱ በሰራዉ ስህተት ፎቶዬን በሌላ አነጋገር አጅቦ ያወጣዉ ከኔ እምነትም ሆን ጉዞ ጋር የሚራመድ ጉዳይ አይደለም::… ጉዞዬ የፍቅር የአንድነት እና የይቅር ባይነት ነዉና ይህንንም ጉዳይ በዚሁ ስሜት ውስጥ እናስተናግደዋለን።” ይላል::ሁለት ቡጥቡጥ ላንሳና ልሞግት::

አንደኛው ይህንን መግለጫ ለመስጠት ለምን ተዘገየ ነው::ይህን በጊዜ ቢያደርጉ ሁለቱም አካላት ብዙ ጉዳት በቀነሱ::ይህ የፕሮሞሽን ስራዎቻቸውን የያዙ ሰዎቻቸውን ይመለከታል:: በርግጥ ፌስቡክ ላይ የተደረገው ዘመቻ መሬት ስለመውረዱ እርግጠኛ አይደለንም ሊባል ይችላል:: ያም ሆኖ ትልቅ አደጋ አስተናግዶ አልፏል ባይ ነኝ::

ሁለተኛው መጽሔቱ ስህተት ሰርቷል የሚለውን ምላሽ እንዳለ ተቀብለን ስህተት ሰርቷል ተብሎ ዝም ነው የሚባለው? ወይስ መጽሔቱ የወሰደው እርምጃ ምንድነው ብሎ መጠየቅ ይኖርብን ይሆን? በመጀመሪያ ‘ለኔ ቅዱስ ነው’ የሚለውና ‘አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል::’ የሚሉት ሁለት ሀረጎች የተለያየ ትርጉምና እርስ በርሱ በምንም መልክ ተቀራራቢነት ያላቸው ሀሳቦች አይደሉም::

ይህ የሚያስማማን ከሆነ ደግሞ ይህ እንዲመስልና የተባለውን ተደርጎ እንዲወሰድ የሰራ ሰው መኖር አለበት:: ያላለውን ብሏል ብሎ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ አስቀምጦ ከጻፈ ይህ ሰው በርግጥም ከሙያው ስነ ምግባር የማይጠበቅ ተግባር ፈጽሟል:: ይህንን ተግባሩንም አቅዶና አስቦበት ላለማድረጉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም:: ስለዚህ ከትርጉማቸው አለመቀራረብና በተለይም ከጉዳዩ ክብደት አንጻር ይህንን ተራ ስህተት ብሎ ማለፍ አይቻልም ባይ ነኝ::

ይህን ስህተት ለማለትም ይከብደኛል:: ስም ማጥፋት እንዳይሆን የሚከለክለውም ምን እንደሚሆን አይገባኝም:: በኢትዮጵያ የፕሬስ ህግ የስም ማጥፋት ባለቤቱ ቢተወው እንኳ መንግስት ስም አጥፊውን ተከታትሎ ይቀጣል ወይም የቅጣት ውሳኔ እንዲሰጥ ያደርጋል:: ጥያቄው በርግጥ ቴዲ ያላለውን የእንቁ ‘ሌይ አውት’ ሰዎችና ያጠናከረው ጋዜጠኛ በዚህ መልክ አቀረቡትን? እኔን አላሳመነኝም!

በተጨማሪ እንዲህ አይነት ቃለመጠይቆች ቢያንስ በመቅረጸ ድምጽና ሌሎች ዘመናዊ የዲጅታል መሳሪያዎች የሚደገፉ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ:: ብቻ የማይታመን ነገር ለሚስትህ አትንገር ነው ተረቱ:: ቴዲ ከ13 ዓመት በፊት የሰጠውን ምላሽ እየገረብሁ ነበር ድንገት ተመሳሳይ ቅርጽ(ፓተርን) ይከተል እንደሆን በሚል:: መልካም ሳምንት!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 30, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 30, 2013 @ 8:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar