www.maledatimes.com የ5 ዓመት ህፃን ከት/ቤት ፎቅ ወድቃ ሞተች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የ5 ዓመት ህፃን ከት/ቤት ፎቅ ወድቃ ሞተች

By   /   December 31, 2013  /   Comments Off on የ5 ዓመት ህፃን ከት/ቤት ፎቅ ወድቃ ሞተች

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 51 Second

አራት የት/ቤቱ ሰራተኞች ከስራ ታግደዋል

የምሥራቅ ጮራ መዋለ ህፃናትና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የመዋዕለ ህፃናት ተማሪ የነበረችው የ5 ዓመቷ ህፃን ሳባህ አማን ከት/ቤቱ 3ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ በአራተኛ ቀኗ ባለፈው እሁድ ህይወቷ አልፏል፡፡ ጉሊት በመነገድ ከሚተዳደሩ አክስቷና ከ12ኛ ክፍል ተማሪ እህቷ ጋር ትኖር የነበረችው ሕፃን በአሁኑ ዓመት ነበር ትምህርት ቤት የገባችው፡፡ ለብቻው ከተከለለው መዋዕለ ህፃናት እንዴት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታ፣ ከፎቅ ላይ እንደወደቀች እንደማያውቁ የተናገሩት ቤተሰቦች፤ ህፃኗን ስትወድቅ ማንም እንዳልነበረና የትምህርት ቤቱ የካፍቴሪያ ሰራተኛ መሬት ላይ ወድቃ እንዳገኛት ጠቁመዋል፡፡ ልጅቷ ስትወድቅ እንዴት አስተማሪዎች ወይም ሞግዚቶች እንዳላዩ ት/ቤቱን መጠየቃቸውን የገለፁት ቤተሰቦች፤ ከት/ቤቱ “ስብስባ ላይ ነበርን” የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ የምስራቅ ጮራ ት/ቤት ርእሰ መምሕር አቶ ስንታየሁ አንሺሱ ስለ አደጋው ሲናገሩ፤ “ሳምንታዊ ስብሰባ የምናደርግበት ቀን ስለነበር አጠቃላይ የት/ቤቱ መምህራንና ሰራተኞች ተሰብስበን ሳለ ከቀኑ 9፡40 ላይ አንዲት ተማሪ ከፎቅ ወድቃለች ተባልን።

ወዲያው ህፃኗን አንስተን ወደ ምግባረ ሰናይ ሆስፒታል ወሰድናትና ወደ ጥቁር አንበሳ ላኩን። እዚያም ከፍለን አሳከምናት” ብለዋል፡፡ ሆኖም ህፃኗ በወደቀች አራተኛ ቀኗ ህይወቷ አልፏል፡፡ ህፃኗ እንዴት ትምህርት ቤት ውስጥ ለብቻዋ እንደቀረች የተጠየቁት ርዕሰ መምህሩ፤ ብቻውን እንዳልነበረችና 5 ህፃናት አብረዋት እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ህፃናቱን ለብቻቸው ትተው ስብሰባ መግባታቸው አግባብ ነው ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ስንታየሁ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን በጊዜ እንዲወስዱ ማስታወቂያ መለጠፋቸውንና በቃልም መንገራቸውን ገልፀዋል፡፡ በህፃኗ ላይ ለደረሰው የሞት አደጋ ተጠቂው ማን እንደሆነና የተወሰደ እርምጃ ስለመኖሩ የተጠየቁት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር፤ “ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አራት ሰራተኞች ከስራ አግደናል፤ ሁለት ሞግዚቶችና ሁለት ጥበቃዎች ደግሞ ጉዳያቸው በዲሲፕሊን ኮሚቴ እየተጣራ ነው” ብለዋል፡፡

ት/ቤቱ ለቀብር 2500 ብር ብቻ እንደሰጣቸው የገለፁት የሟች ቤተሰብ፣ ት/ቤቱ ካሣ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር በበኩላቸው፤ ት/ቤቱ የመንግስት እንደሆነና ካሣ ለመክፈል ጉዳዩ በህግ መያዝ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ “እስከዚያው ግን ክፍለከተማን አናግረን፣ በየካ ክፍለ ከተማ ባሉ ት/ቤቶች እየዞርን መዋጮ ለመሰብሰብ አስበናል” ብለዋል፡፡ ይሄ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ፖሊስ የህፃኗን አሟሟት በመመመርመር ላይ እንዳለ ለማወቅ ችለናል፡፡admas

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 31, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 31, 2013 @ 9:14 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar