www.maledatimes.com የመን በፍንዳታ ተናወጠች ( በግሩም ተ/ሀይማኖት) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመን በፍንዳታ ተናወጠች ( በግሩም ተ/ሀይማኖት)

By   /   February 3, 2014  /   Comments Off on የመን በፍንዳታ ተናወጠች ( በግሩም ተ/ሀይማኖት)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 5 Second

በአንድ ጀምበር አራት ፍንዳታ…በየመን
ትላንት ለዛሬ አጥቢያ ማለትም እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት መኝታዬ ላይ ወጥቼ እገላበጣለሁ፡፡ እንቅልፍ ከእኔ ዘንድ አልነበረም፡፡ እንዳልጽፍም መብራቱን መተውታል ተብሎ የየመንዋ ዋና ከተማ ሰነዓ የገና ክሪስማርስ ላይ እንደተንጠለጠለ መብራት ቦግ ድርግም ትላለች፡፡ ደልታቷት ሳይሆን ጎድሎባት ልጆቿ አጥቶ ጠፊ ሆነው መብራቱን መቱት እየተባለ በሻማ ምሽት መክረምን ለምደነዋል፡፡ ላፕቶፔ ደግሞ ቻርጅ የለውም፡፡ አማራጭ በማጣቴ ሞባይሌን አንስቼ ጌም ከፈትኩ፡፡ ጠላታችሁ ክፍት ይበል ሲከፈት እና ያለሁበት ቤት ሲያረግድ አንድ ሆነ፡፡ ደነገጥኩ፡፡ ‹‹..አረገደች ምድር አረገደች ምድር…›› የመዝሙር ዮሀንስ (የጸሀዬ ወንድም) ዜማ ትዝ አለኝ፡፡
የፍንዳታው ድምጽ ደስ ባይልም ሀገር ላገር ይሰማ ነበር፡፡ ከዳር ዳር ስሙኝ ብሎ አስደንግጧል፡፡ በእርግጥ ለየመን ፍንዳታ አዲሷ፣ አስደንጩዋ አይደለም፡፡ እዚህ ቦታ ፍንዳታ ፈነዳ፣ ባለስልጣን ተገደለ…ሁሌም የሚደመጥ ዜና ነው፡፡ ‹‹ደግሞ የት ይሆን የፈነዳው?..›› አልኩኝ በውስጤ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግፋ ቢል ተኩል ሰዓት ቆይቶ ራቅ ካለ ስፍራ ድጋሚ የፍንዳታ ድምጽ ሰማሁ፡፡ ‹‹..ሁለት..›› አለ ውስጤ ለውስጤ ሲነግረው፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ እንቅልፍ አይኔነን ሊከድን ትግል ገጠመ፡፡ ሶተኛውን ፍንዳታ ይሁን የከባድ መሳሪያ ተኩስ መለየት ባልቻልኩበት ሁኔታ ሰማሁ፡፡
አሁን ተሸንፌ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ጠዋት ላይ ዜና እወጃው በአንድ ሌሊት አራት ቦታ መፈንዳቱን አበሰረን፡፡ ቤታችንን ንቅንቅ አድረጎ አረገደቸ ምድር የሚለውን ዜማ ያስታወሰኝ በወፍ በረር ቢለካ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት በማይሞላ ቦታ አልኩሜም የሚባለው ቦታ የፈነዳው ነው ለካ፡፡ በእርግጥ በፍንዳታ እንታመስ እንጂ ኢትዮጵያዊያንን የነካ አይደለም፡፡ እባክህ አምላኬ በስደት ወጥተን በሰወ ሀገር እንዳንቀር አደራ….፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 3, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 3, 2014 @ 8:57 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar