www.maledatimes.com መቼ ነዉ ኢትዮጲያ የምትሸጠዉ ? ሜሮን አድማሱ / ከኖርዌይ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መቼ ነዉ ኢትዮጲያ የምትሸጠዉ ? ሜሮን አድማሱ / ከኖርዌይ

By   /   February 6, 2014  /   Comments Off on መቼ ነዉ ኢትዮጲያ የምትሸጠዉ ? ሜሮን አድማሱ / ከኖርዌይ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 8 Second

 

 

 

ወያኔዎች ትግራይን ከኢትዮጲያ የመገንጠል ህልማቸዉን ለማሳካት ሲባል ለምትገነጠለዉ ትግራይ መዉጫ ድንበር የሚያገኙት የግዴታ በሱዳን በኩል ከጐንደር ሰቲት ሁመራን ፥ ወልቃይት ፥ ጠገዴንና ጠለምትን የትግራይ አካል ካደረጉ ስለሆነ እነዚህን ለም የእርሻ መሬቶች ከአካባቢዉ ነዋሪዎች በግዴታ ህዝቡን አፈናቅለዉ ፥ እምቢ ያለዉንም አስረዉና ጨፍጭፈዉ መሬቱን ለትግራይ ባለ ሀብቶች እንደተሰጡ የሚታወስ ነዉ።

 

በተለያዩ ከተሞች በብዙ ሚሊዮን ሄክታር የሚገመት የኢትዮጲያ ለም የእርሻ መሬቶች ለተለያዩ የዉጪ ሀገራት እየተሸጠና የሌላ ሀገራቶች የምግብ ዋስትና እየተረጋገጠ ይገኛል። የኢትዮጲያን ህዝብ ጉሮሮን እየዘጋ ያለዉ ወያኔ ብዙዎቹን አርሶ አደሮች በማፈናቀልና ጥያቄ ያስነሱትንም እስከ ሞት ድረስ የሚያደርስ እንግልት አድርሰዉባቸዉና በየ እስር ቤቱ እየተወረወሩ መሬታቸዉን ተነጥቀዋል። በየአካባቢዉ የቀረዉንም ገበሬ በገዛ መሬቱ ለእለት ጉርሱ እንኳን በማይበቃ ገንዘብ እንዲያገለግልና ጉልበቱ እንዲበዘበዝ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት ለዉጪ ባለ ሀብቶች እየተቸበቸበ ያለዉ የኢትዮጲያ ለም መሬት ወደፊት ኢትዮጲያዊ መንግስት ሲመጣ ይዞ የሚመጣዉን ችግር ከአሁኑ መገመት ይቻላል።

 

ለብዙ ሰዉ ጥያቄ እየሆነበት የመጣዉ ስለኢትዬ – ሱዳን ወደብ በአንድ ወቅት ሱዳኖች የኢትዮጲያ መንግስት አሳልፎ መሬቱን እንደሠጣቸዉ በገሀድ አዉጥተዉ የተናገሩ ሲሆን ወያኔ ግን በሚስጥር መያዙ ይታወሳል።  የአካባቢዉ ነዋሪዎችም በሱዳኖች ያላቸዉን ንብረት እየተነጠቁና እየታሰሩ በተጨማሪም ኢህሀዲግ በሄሊኮፕተር በጥይት ቤቶቻቸዉንና እርሻዎቻቸዉን እንደጨፈጨፈ የአካባቢዉ ነዋሪዎችም ገልፀዋል። ኢህሀዲግ ምን አስቦ ነዉ የሰሊጥ ምርትና ነዳጅ አለበት የሚባል ቦታ አሳልፎ መስጠቱን የመረጠዉ ምክንያቱም ከሠሊጥ ምርቱም የሚገኘዉ ገቢ ወያኔ ኪስ ዉስጥ ነዉ የሚገባዉ የኢትዮጲያ ህዝብ እንደሆነ ዋናዉ ገቢዉ መደብደብና መዘረፍ ሆኗል።

 

ወደኋላ ሄደን ታሪክን ስንዳስስ የኢትዮጲያ መሬት መሆኗን የሚገልፅ መረጃዎችን ከብዙዎቹ አንዱ ብንጠቅስ – በሊጉ ኦፍ ኔሽን (League of Nation) ስምምነት ጊዜ ሁሉም ሀገሮች ድንበራቸዉን ሲያሳዉቁ ከአፍሪካ ኢትዮጲያ ከቅኝ ግዛት ነፃ ሀገር ስለነበረች ድንበሯን አሣዉቃለች። በዛም ጊዜ ሱዳን በእንግሊዞች ቅኝ ስር ስለነበረች ከኢትዮጲያም ጋር የተካለለችዉ ድንበር አለመኖሩን ታሪክ ይነግረናል።

እንግሊዞች አባይን እናልማ ብለዉ አፄ ሀ/ስላሴን ሲጠይቁ ፦ ሀ/ስላሴም መጀመሪያ እንዲጠና ፈቅደዉ ተጠንቶ ሲያልቅ አባይን ከመነሻዉ ጀምሮ በሙሉ ተፋሠሱ የሚሄድበትን መሬት ሁሉ እናለማለን ግን ካለማን በኋላ መሬቱ በእንግሊዞች ቁጥጥር ስር ነዉ የሚዉለዉ  ሲሏቸዉ ሀ/ስላሴም ልማቱን እንፈልጋለን ተባብረንም ከልማቱ ተጠቃሚ መሆን ነዉ ያለብን እንጂ መሬቱን እንኳን አሣልፈን አንሰጥም ብለዉ ተቃዉመዋል። ይህንንም በ ህይወቴና ኢትዮጲያ እርምጃ በሚለዉ መፅሀፍ ላይ ለሊጉ ኦፍ ኔሽን (League of Nation ) ሙሉ ደብዳቤ የፃፉት ይገኛል።

 

ኢህሀዲግ  የታሪክ ምንጭ ስላጣሁኝ ነዉ የኢትዮጲያን መሬት ለሱዳን የምሰጠዉ ካለ በአገራችን ዉስጥ ብዙ መረጃዎች እንደሚኖሩ እርግጥ ነዉ ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም አይደል የሚባለዉ።

 

በአጠቃላይ የወያኔ ግፍ ማለቂያ የለዉም ፦ ካለ ህዝብ ፈቃድ ኤርትራን የሚያህል ትልቅ ሀገር አሳልፎ ሰጥቶ ለአንድ አዉራጃ ለባድመ 60 ሺ ህዝብና 25 ቢሊዮን ብር ማጥፋቱ የማይረሣ ቁስል ነዉ። ለምለም የእርሻ መሬቶችን እየሸጠና ህዝብን እያሠቃየ ፣ እየጨፈጨፈ ፣ እያሠደደ ፣ ህፃናትን እየሸጠ ፣ ያለዉ ቅኝ ገዢዉ ወያኔ በአለም ላይ አሠቃቂ የሚባሉትን ሁሉ ግፎች በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ ፈፅሟል።  አሁን የቀረዉ ሙሉ ኢትዮጲያን ለመሸጥ መደራደር ስለሆነ ከዚያ በፊት ከዚህ ከግፈኛና አፋኝ ቅኝ ግዛት መላቀቅ የምንችልበትን መንገድ መፍጠር የምንችለዉ እራሣችን ከዘረኝነትና ከጥላቻ አሶግደን አንድነት በመፍጠርና በመተባበር ነዉ።

 

 

ድል ለኢትዮጲያ

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 6, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 6, 2014 @ 7:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar