www.maledatimes.com ማንነት ዘብዙኋን ======= ፍካሬ ዘስነልቡና ወማህበረሰብ ሳይንስ (ሬገን ሰለሞን ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ማንነት ዘብዙኋን ======= ፍካሬ ዘስነልቡና ወማህበረሰብ ሳይንስ (ሬገን ሰለሞን )

By   /   February 6, 2014  /   Comments Off on ማንነት ዘብዙኋን ======= ፍካሬ ዘስነልቡና ወማህበረሰብ ሳይንስ (ሬገን ሰለሞን )

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 33 Second

ለፖለቲካ ቀኖናቸው ሲሉ የማንነትን ይዘት ለሚያዛቡ የኢትዮጵያ ልሂቃን ወየሁላቸው:: በስምንተኛው ሺህ በእነርሱ መጓተት ምክንያት በፌቡ መደናገር ይሆናልና::

ተስፋ ገ/ስላሴ ዘብሔረ ቡልጋ 

‘የኢትዮጵያ ህዝቦች ምን ምንን ያካትታሉ? ‘ህዝቦች’ የሚለው ላይ አተኩራለሁ ምክንያቱም በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ በእርግጥ አንድ ብሄር አይደለችምና::የራሳቸው የሆነ ቋንቋ፣ አለባበስ፣ ታሪክ፣ የማህበረሰብ አደረጃጀትና ግዛት ካላቸው [በርካታ] ብሄረሰቦች የተሰራች ነች::’

ዋለልኝ መኮንን ህዳር 7,1962

የማንነት ፖለቲካ የቡድን ጥቅምና አመለካከት ማስከበር ላይ ያተኮረ የአንድ የተለየ ማህበረሰባዊ ቡድን የፖለቲካ ክርከር ሲሆን የአንድ ሀገርን ፖለቲካ በዘር፣ በመደብ፣ በሐይማኖት፣ በጾታ፣ በዘውግ፣ በአይዲዎሎጂ፣ በብሄር፣ በጾታዊ ግንኙነት ምርጫ፣ በባህል፣ በገንዘብ፣ በመረጃ ምርጫ፣ በታሪክ፣ በሙዚቃና የስነጽሁፍ፣ በህክምና ሁኔታ፣ በሙያ፣ በትርፍ ጊዜ ድርጊት ና ሌሎች በስሱ በተገናኙና በታወቁ የማህበረሰብ አደረጃጀት ላይ የተቀረጸ ነው::

ማንነት ከዚህ በላይ እንደሚታየው የብዙ ጉዳዮች ስብስብ ነው:: ከአንድ ሀገር ሊሰፋም ሊጠብም ይችላል::አንድ ሰው ከእነዚህ ማንነቶች የተወሰኑት/የአብዛኛው ጥርቅም ሊሆን ይችላል:: አፍሪካዊ/ኢትዮጵያዊ ወንድ/ሴት ኦርቶዶክስ/ፕሮቴስታንት/ሙስሊም/አቴይስት ሠራተኛ/ነጋዴ/ገበሬ ተቃራኒ/ተመሳሳይ ጾታዊ ግንኙነት ኦሮሞ/አማራ/ተጋሩ ማርክሲስት/ሊበራል አብሲንያዊ/ኒዎ-ኢትዮጵያዊ የታሪክ ዕይታ ደምብዛት/ደምማነስ ያለበት/ባት ኢኮኖሚስት/ኢንጂነር/የህክምና ባለሙያ/ፀሀፊ አክቲቭስት እያለ ይቀጥላል::

አማርትያ ሴን ማንነትና ነውጥ: የዕጣፈንታ ቅዠት(2006) በሚለው መጽሐፉ እንደሚለው ሁለት ጉዳዮችን መገንዘብ አለብን:: አንደኛው ማንነት በባህሪው ‘ብዙ’ መሆኑንና የአንዱ ማንነት(መለያ) አስፈላጊነት የሌላውን ማንነት(መለያ) ሊያጠፋው እንደማይችል መገንዘብ ነው:: የኢትዮጵያዊነቴ ማንነት የኦሮሞነቴን/የአማራነቴን ማንነት ሊያጠፋው አይገባም ማለት ነው:: ሁለተኛው ወዳጄ ኖላዊ እንዳለውም ምን አይነት ተነጻጻሪ ክብደት ከተመቸው የማንነቱ መለያዎች ላይ መጫን እንዳለበት የግለሰቡ ምርጫ ነው የሚሆነው:: በተለይም ከብዙ ታማኝነቶችና ማንነቶች ውስጥ ለየትኛው ቅድሚያ እንደሚሰጥ የግለሰቡ/ቧ ጉዳይ ነው::

እንግዲህ እያንዳንዱ ግለሰብ ብዙ ማንነት አለው:: ለዚህ ብዙ ማንነት እውቅና መስጠት አለመስጠት የግለሰቡ ጉዳይ ነው ማለት ነው:: እዚህ ላይ የሚነሳው ሌላው ጥያቄ የሚሆነው የግለሰቡ ምርጫ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ይቻላልን? የሚለው ነው::ይህ ሁሉን ምርጫ የማድረግ አባዜ ያለባቸው ሰዎች ብሔራችንን መርጠን አናመጣውም የሚሉትን ክርክር ያመጣል:: በርግጥም ቤተሰቦቻችን በምርጫቸው ይወልዱናል እንጂ እኛ ከዚህና ከዚያ እንወለድ ብለን አልመረጥንም::

ይሁንና ምርጫችን ስላልሆነ ማንነታችንን አይወክልም ማለት አይቻልም:: ሳንመርጥ የምንጋራቸውና የምንሆናቸውም አሉ:: በሌሎች ምርጫም የምንሆናቸው ጉዳዮች አሉ:: ቤተሰብ በዚህ ረገድ ብዙ ምርጫን ይመርጥልናል:: የነሱ ምርጫ የኛ ነው ብለን ካላሰብን በቀር ብዙ ምርጫዎቻቸው ማንነታችንን ይቀርጻል::

ከዚህ የተሻለው ጉዳይ እያደግን በሄድን ቁጥር የምንመርጣቸው ታማኝነቶችና ማንነቶች መኖራቸው አይቀርም:: የብሔር ይሁን የአብሲንያዊ አይዲዎሎጂ(ሁለቱ ተነጻጻሪ ስለሆኑ አይደለም የቀረቡት) ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ምርጫ እናደርጋለን:: በሞራል መለኪያ ሁለቱም እኩል ምርጫዎች ናቸው:: አንዱ ካንዱ የሚሻለው በግለሰቡ እይታ ነው:: ያም ሆኖ ማንነት ሙሉ በሙሉ ምርጫ ነው ከማለት ይልቅ ‘በአብዛኛው ምርጫ ነው!’ ቢባል የተሻለ ነው::በቸር ያቆየን::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 6, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 6, 2014 @ 11:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar