www.maledatimes.com በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማደረጉን ንግድ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማደረጉን ንግድ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

By   /   February 7, 2014  /   Comments Off on በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማደረጉን ንግድ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 52 Second

ዜና ድንቅ፦

በዚሁ የዋጋ ክለሳ መሰረት ከየካቲት 1 ቀን 2006 ጀምሮ :-

· ኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ ብር 20.47
· ነጭ ናፍታ ብር 18.55
· ኬሮሲን ብር 15.75
· ቀላል ጥቁር ናፍታ ብር 16.33
· ከባድ ጥቁር ናፍታ ብር 15.65
· የአውሮፕላን ነዳጅ ብር 23.03

በአዲስ አበባ ከተማና በአገር አቋራጭ አውቶብሶች የትራንሰፖርት አገልግሎት ላይ ከየካቲት 1 ቀን 2006ዓ.ም ጀምሮ የዋጋ ማሻሻያ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት የከተማ ሚኒባስ ታክሲ 1 ብር ከ45 ሳንቲም የነበረው 1 ብር 50፣ 2 ብር ከ80 ሳንቲም የነበረው 2 ብር ከ85፣ 4 ብር የነበረው 4 ብር ከ10፣ 4 ብር ከ05 ሳንቲም የነበረው 4 ብር ከ15 እና 5 ብር ከ20 ሳንቲም የነበረው 5 ከ35 ሳንቲም እንዲሆን ተደርጓል።

በተጨማሪ በከተማ ሚድባሶች ላይ ከ8 ኪሎ ሜትር እስከ 21 ኪሎሜትር በሚደርሱ ርቀቶች ከአምስት ሳንቲም እስከ 15 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉ ተገልጿል።

የአንበሳ የከተማ አውቶቡስን በተመለከተ ከ9 ኪሎ ሜትር እስከ 24 ኪሎ ሜትር ላይ ከአስር ሳንቲም እስከ ሃያ አምስት ሳንቲም ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ከ24 እስከ 30 ኪሎ ሜትር የ75 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉን ገልጿል።

በተጨማሪ ከ30 እስከ 47 ኪሎ ሜትር የነበረው 8 ብር የነበረው 9 ብር እንዲሆን መወሰኑን መግለጫው አመልክቷል።

የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ታሪፍን በተመለከተ በአስፋልት መንገድ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአማካይ 1 ነጥብ 50 ሳንቲም በነበረው ታሪፍ ላይ ጭማሪ መደረጉም አብሮ ተገልጿል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 7, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 7, 2014 @ 2:14 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar