www.maledatimes.com የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ቅጥፈት ሲጋለጥ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ቅጥፈት ሲጋለጥ

By   /   February 8, 2014  /   Comments Off on የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ቅጥፈት ሲጋለጥ

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 56 Second

ከመ/ር ሰናይ ገ/ህይወትና ቴዎድሮስ

በቅድሚያ ዘሀበሻ ድረ ገጽ ሁለቱንም ወገኖች ህሳባቸውን ለማደመጥ የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ። ሆኖም ግን ሃገር ቤት ካለው ሲኖዶስ ጋር እንዲቀላቀል ከሚፈልገው ወገን የሚሰጠውን ሃሰተኛ ዘገባ ዘሀበሻ ለሚዛናዊነት በሚል በቀጥታ ከማስተናገድ ይልቅ ቆም ብላ ብታስብበት መልካም ነው እላለሁ። ዛሬ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ትናንት በዚሁ ድረገጽ ላይ የታተመውን የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢሜይል እና በተለያዩ ዘዴዎች የበተነውን መግለጫ ይመለከታል። ዘገባው እጅግ ሃሰት እንደሆነና ሁሉም ነገር በፍርድ ቤት ውድቅ እንደሆነ የዘገበበትን ቅጥፈት ለማጋለጥ ነው ወደዚህ ብቅ ያልኩት።

ከአንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ወይም መሪ ነኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ ቅጥፈት ተፈጽሟል። ይህም እግዚአብሔርን ያሳዝናል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ዶክመትን እንደሚከተለው አያይዣለሁ፤ አንባቢዎች እንደሚፈርዱም ይህ ያሳያል።

ልብ ብላችሁ ካነበባችሁት በመጨረሻው መስመር ላይ “ከማርች 10 በፊት የሚስማሙ ከሆነ” ይላል። ይህ ማለት የሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ነው። ይህን ደግሞ ዘሀበሻም ቀድሞ ዘግቦታል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዳወራው ቅጥፈት ፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ባወጣው ትዕዛዝ ላይ ስለ ቦርዱ፣ ስለገንዘቡ፣ ወዘተ… የሚያወራው የለም። የእግዚአብሄርን ስም እየጠሩ ቅጥፈት ያሳፍራል።

እኔን የገረመኝ ቤተክርስቲያኑን በተመለከተ ይህን የመሰለ ሃሰተኛ ወሬ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ሲያሰራጭ ደብረሰላምን የሚመራው ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ ውስጥ ይከታል።

ውድ ወገኖች፤ እውነቱ ይኸው ነውና በቀጣዩ የአጠቃላይ ጉባኤ ላይ በመገኘት ለውሳኔ እንዘጋጅ። ቤተክርስቲያናችንን የምናድነው ያኔ ነው።

ተጨማሪ አስተያየት ቴዎድሮስ ከተባሉ የቤተክርስቲያኑ አባል የተሰጠ ይከተላል

የሜኖሶታ: ደብረሰላም: መድሀኒአለም: ቤተክርስቲያንን: የውስጥ: ችግር: ለመፍታት: በ02/05/2014 የነበረው: የፍርድ: ቤት: ውሎ: እና በዳኛዋ: የተሰጠ: ያልተዛባ: ውሳኔ: እንደሚከተለው: ነው።

በመጀመሪያ: ከላይ: በተጠቀሰው: ቀን: የአቶ: ጥበቡ: እና: አቶ: ጥበቡን: አወረድኩ: የሚለው: ቦርድ: በጠበቆቻቸው: አማካኝነት: ጉዳያቸውን: አቅርበው: በተከበረው: ፍርድ: ቤት: የተከራከሩ: ሲሆን፣ የተከበሩት: ዳኛ: ነገሩን: ከነመረጃቸው: ካዩ: ቡሃላ: የሚከተለውን: አጠቃላይ: መመሪያ: ለሁለቱም: ወገን: ጠበቆች: ሰጥተዋል።
1፣ አጠቃላይ: የአባላት: ስብሰባ: ለ02/23/2014 እንዲደረግ (ይህ: የተወሰነው: አቶ: ጥበቡ: ባቀረቡት: የ 355: የአባላት: ግልፅ: እና: እውነተኛ: ፊርማ: ነው።)

2፣ በ 02/23/2014: በሚደረገው: አጠቃላይ: የአባላት: ስብሰባ: ጊዜ: አባላቱ: ማድረግ: የሚፈልገውን: ማንኛውንም: አይነት: አጀንዳ: አንስቶ: የማፅደቅና: የመጣል: ፍፁም: ሙሉና: ያልተገደበ: መብት: አለው።

3፣ ምክትል: ሊቀመንበሩ: ለጊዜው: የሚሰሩ: ስራዎችን: ያከናውናል።

4፣ የባንክ: አካውንቱ: ከመደበኛ: ክፍያዎች: ውጪ: መጠቀም: ወይም: ማንቀሳቀስ: ፈፅሞ: አይቻልም።

5፣ ይህ: ጉዳይ: በአጠቃላይ: ስብሰባው: ካልተፈታ: የተከበሩት: ዳኛ: በ 03/02/2014: ነገሩን: አይተው: የፍርድ: ሂደቱ: ይቀጥላል: ማለት: ነው።

እነዚህ: ናቸው : እንግዲህ: አጠቃላይ: ውሳኔዎቹ።
ማንኛውም: ሰው: እነዚህን: የዳኛ: መመሪያዎች: ከሁለቱም: ጠበቆች: ማግኘት: ይችላል። በጣም: የሚገርመው: ይህ: የተከበሩት: ዳኛ: ውሳኔ: በኢትዮጽያ: ሲኖዶስ: ይሁን: የሚሉትን: ጠበቃ: እና: ደንበኞቿን: ለምን :እንደሚያስፈራቸውና: እንደሚያስደነግጣቸው: አይገባንም። በተለይ: ለምን: አጠቃላይ: ስብሰባን: እንደጦር: እንደሚፈሩት: ሲታይ: በጣም: ይገርማል።
ይህ: አሜሪካ: ነው። ማንም: የማንንም: መብት: የሚገድብበት: መብት: የለውም። በተጨማሪም: የሜኖሶታ: መድሀኒያለም: ቤተክርስቲያን: የህዝብ: እንጂ: የጥቂት: ሰዎች: አይደለም። እናም፣ እንደራሳችሁ: የግል: ቤትና: ንብረት: መቁጠራችሁን: ትታችሁ: የህዝቡን: ድምፅ: ያለምንም: ቅድመሁኔታ: በፍፁም: ትህትናና: አክብሮት: ስሙ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 8, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 8, 2014 @ 7:36 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar