www.maledatimes.com የወያኔ ሴራ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

የወያኔ ሴራ

By   /   February 10, 2014  /   Comments Off on የወያኔ ሴራ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 19 Second

 

ከመቃብር ምሶ፣

ሙታንን  ቀስቅሶ፣

ዘር አጥንት ቆጥሮ ከሰውነት ወጥቶ

እንደራበው ውሻ አጥንት እየጋጠ፣

በስንቱ ቀለደ በስንቱ አላገጠ፡፡

ዛሬን እንዳንቃኝ እንዳናልም ነገን፣

ሁል ጊዜ በፍርሀት እያሸማቀቀን፣

ሽብረተኛ እያለ ሽብር ሲዘራብን፣

እኛም ሚሲኪን ህዝቦች እንቀበላለን፡፡

በጥላቻ ወሬ እግር ከወርች ታስረን፣

እንዳንከባበር በትእቢት ተውጠን፣

አንዱ አንዱን ላይሰማው ስንደነቁዋቆር

ሁሉም በያለበት እየየውን ሲያወርድ፣

የተጫነብንን መርገም እንደማውረድ፣

አንድ መቶ አመታት የሁዋሊት ተጉዘን፣

ከሙታን መንፈስ ጋር እንፋለማለን፡፡

ሀገርን ባቀና ክብርን ባስመለሰ፣

የምንሊክ ሀውልት ይላል ካለፈረሰ፡፡

ወያኔ የሚባል የባንዳ ስብሰብ፣

ከከርሳቸው ውጪ ምንም የማያስብ፣

መርዝ እንደቀመመ ተንኮል እንዳደራ፣

በጅምላ እንዳሰረ ካገር እንዳስወጣ፣

ሌላ ማዘናጊያ አኖሌ ሚል መጣ፡፡

ስንት ሰዎች አለን ግራ የተጋባን፣

የሰጡንን ስራ ሰርተን ያልጨረስን፡፡

አንዴ አብዮታዊ ሲለው ልማታዊ፣

ፌደራልም አልከው ወይም ክልላዊ፣

በቃላት ጋጋታ ህዝብን እያምታታ

መልክ እና ጸባዩን እየለዋወጠ

ስልጣን ኮርቻ ላይ ከተቆናጠጠ

ዘመናት ነጎዱ

ስንት ኩነት ሄደ ስንት ኩነት መጣ

ወገኔ ከችርግ ከዋይታ ሳይወጣ፡፡

አንዱአለም፣ ውብሸት፣

በቀለ እና ርዮት

በሰላሙ መንገድ ህዝብን የሰበኩት

ነጻነትን ሲሹ ፍትህ የተጠሙት

ላገሩ በጮኸ ለፍትህ በጻፈ፣

እስክንድር ታሰረ  ብእሩ ነጠፈ፡፡

ሀገር እየሸጡ ሀብት እየዘረፉ፣

በጅምላ እያረዱ ዘርን እያጠፉ፣

የጌቶቹ ልጆች ጮማ እየቆረጡ፣

ስንቶች ማደሪያ አጥተው ከቤታቸው ወጡ፡፡

እምዬ ንገሪኝ ምንድን ነው መርገምሽ፣

አልወጣልሽ ያለው መከራ ከቤትሽ፡፡

ሀዘን ሀዘን ወልዶ ልቤን እየነካው፣

የትናነቱ ቁስል ሳይጠፋ ጠባሳው፣

ወደብ አልባ መሆን እያንገበገበኝ፣

ዛሬ የባስ ብሎ ድጋሜ አስደፈረኝ፡፡

ከእንግዲህ ይበቃል ምን ሊመጣ ሌላ፣

ዘር ቀለምን ሳልለይ ወይም እምነት ጎራ

አብሬ ልሰለፍ ከነአንዱአለም ጋራ፣

እንደሰው ልቆጠር እኔም ታሪክ ልስራ ፡፡

ፌብሩዋሪ 2014

በዳዊት መላኩ (ከጀርመን)

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 10, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 10, 2014 @ 1:56 am
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar