www.maledatimes.com ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጠለፈ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጠለፈ።

By   /   February 17, 2014  /   Comments Off on ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጠለፈ።

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 17 Second

ጠላፊው በቁጥጥር ስር ውሏል። ጥያቀው የፖለቲካ ጥገኝነት ነው።
የአውሮፕላኑ ጠላፊ የአውሮፕላኑ ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ነው።
ጠላፊው በስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት ማግኘት ይፈልጋል። የወያነ መንግስት በዘር እና በሃይማኖት ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ የሚቃወም እንደሆነ ታውቋል።

ዛረ ሰኞ ማለዳ የበረራ ቁጥሩ ET702 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ወደ ሮም በመብረር ላይ እንዳለ የሱዳንን አየር ላይ በመጠለፉ በግዳጅ በስዊዘርላንድ ጀነቭ እንዲያርፍ መደረጉን የስዊዘርላንድን ፖሊስ ጠቅሰው ዘገባዎች ሲያመለክቱ ጠላፊው በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ተሳፋሪዎቹም በመልካም ደህንነት እና ተንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የተናገሩት የጀነቭ ፖሊሶች አውሮፕላኑ ውና መድረሻውን ሮምን አልፎ በጀነቭ እንዲያርፍ በጠላፊው የተገደደ እንደሆነ እና ሮይተር ያናገራቸው የኢትዮጵያ ባለስልጣን አውሮፕላኑ በሱዳን ካርቱም ለትራንዚት ማረፍ የነበረበት ቢሆንም በጠላፊዎቹ አስገዳጅነት መድረሻውን ሮምን ጥሎ በጀነቭ እንዲያርፍ ጠላፊዎቹ እንዳስገደዱት ተናግረዋል።
የቦይንግ አውሮፕላኑ ካፒቴን ወደ መጸዳጃ ቤት በሄደበት ወቅት አውሮፕላኑን የተቆጣጠረው ረዳት ፓይለቱ አውሮፕላኑን ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ ካሳረፈ በኋላ ከአውሮፕላኑ በመስኮት በገመድ ተንጠላጥሎ በመውጣት እጁን ለፖሊስ በመስጠት ጥገኝነት እንደጠየቀ ታውቋል፡፡

በትዊተር ማህበራዊ ገጽ ላይ በተለቀቀ የፓይለቱ ወይም የረዳት ፓይለቱ እንደሆነ በግልጽ ባልታወቀና ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ጋር በተደረገ የሬድዮ ግንኙነት ላይ “ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን እንደማንሰጥ ማረጋገጫ ወይም ጥገኝነት እንዲሰጠን እንጠይቃለን” የሚል መልዕክት ተደምጧል፡፡

በአየር መንገዶቹ የራዲዮ መልእክት ሏጥ እንደሚያመለክተው የጠላፊው ጥያቀ ጥገኝነት የማግኘት ሲሆንበኢትዮጵያ የፖለቲካ አሊያም የኢኮኖሚ ሁነታ የተማረረ ሰው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 17, 2014 @ 9:40 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar