www.maledatimes.com የኮሙዩንኬሽን ሚኒስትሩ-ስለ አውሮፕላን ጠላፊው (ጽዮን ግርማ አዲስ አበባ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኮሙዩንኬሽን ሚኒስትሩ-ስለ አውሮፕላን ጠላፊው (ጽዮን ግርማ አዲስ አበባ)

By   /   February 17, 2014  /   Comments Off on የኮሙዩንኬሽን ሚኒስትሩ-ስለ አውሮፕላን ጠላፊው (ጽዮን ግርማ አዲስ አበባ)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 53 Second

ትናንት ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ በካርቱም አድርጎ ሮም ሊገባ የነበረው ‹‹ኢቲ 702›› አውሮፕላን መጠለፉን አስመልክቶ የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የአውሮፕላኑን መጠለፍ ከገለጹ በኋላ ፤ጠላፊው የአውሮፕላኑ ምክትል አብራሪ የ31 ዓመቱ ኃይለመድህን አበራ ተገኝ መኾኑን አረጋጠዋል፡፡ረዳት አብራሪው አየር መንገዱ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ማገልገሉ ታውቋል፡፡
አቶ ሬድዋን ‹‹በሌላ መንገድ በሚመጣ መረጃ እስካልተረጋገጠ ድረስ እኛ ባለን መረጃ መሠረት ረዳት አብራሪው ሙሉ ጤነኛ ነው፡፡››ብለዋል፡፡ኃይለመድህን ስዊዘርላንድ ለመግባት የሚያስችል ሸንጋይ ቪዛ እንዳውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ በመኾኑ ነጻ ትኬት ማግኘት እንደሚችል በመግለጽ የትም አገር ሄዶ የመቀጠር ዕድል እያለው እንዲህ ማድረጉ እንዳስገረማቸው በንግራቸው ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም‹‹ በፍርሃት አድርጎታል ሊያስብል የሚችል ምም ዓይነት ወንጀል የለበትም›› ብለዋል፡፡
‹‹እስካሁን ምን ፍላጎት እንዳለው አላወቅንም፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊም ኾነ ፖለቲካዊ ምክንያት ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም›› ብለዋል፡፡
አብራሪውን አሳልፎ መስጠትን በሚመለከት ‹‹ከስዊዘርላንድ መንግስት ጋራ አሳልፎ የመስጠት የጋራ ስምምነት የለንም፡፡ ነገር ግን ሌሎች የተፈራረምናቸው ውሎች አሉን፡፡ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይት ያለውን የጄኔቫ ኮንቬክሽን ስዊዘርላንድ 1971 ዓ.ም ተቀብላዋላች፡፡ ለዚህ ሕግ ደግሞ የትኛውም አገር የመገዛት ግዴታ አለበት፡፡ ከዚህ አንጻር ተላፎ የሚሰጥበት መንገድ ሊኖር ይችላል›› ብለዋል፡፡
140 ጣሊያውያን ፣11 አሜሪካውያን፣10 ኢትጵያውያ እና የኮንጎ፣የስዊ፣ኢንግላንድ፣ሩዋንዳ ዩክሬን፣ ጀመርን፣ ታንዛኒያ፣ ብራዚል እና ሌሎች አገር ዜጎች የተሳፈሩበት ይህ አውሮፕላን ስዊስ ካረፈ በኋላ መንገደኞቹን በሌላ አውሮፕላን ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ከአንድ የውጭ ጋዜጠኛ ‹‹ረዳት አብራሪው የየት አካባቢ ሰው ነው?›› ተብለው የተጠየቁት አቶ ሬድዋን ‹‹ኢትዮጵያዊ›› ነው ሲሉ የመለሱት አቶ ሬድዋን ‹‹ጥያቄዬ ከየት ክልል?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ተወልዶ ያደገበትን አካባቢ አላውቅም›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 17, 2014 @ 11:53 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar