www.maledatimes.com አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

By   /   February 17, 2014  /   Comments Off on አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 56 Second

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ፡፡በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል፡፡አቶ አለማየሁ ቀድሞውንም ሥልጣን ሲይዙ በከባድ ሕመም የሚሰቃዩ መኾናቸው እየታወቀ ሲኾን ምንጮች እንዳረጋገጡት አቶ አለማየሁ ወደ መንፈቅ ለሚጠጋ ጊዜ በውጭ አገር በሕክምና ላይ ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ ኮማ ውስጥ ይገቡም ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ጊዜ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተክተው ይሠሩ የነበሩት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ ሲኾኑ የኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸውን ሥልጣን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድር እንደነበሩ ምንጮች ጨምረው አረጋግጠዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 17, 2014 @ 12:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar