www.maledatimes.com በአምባገነናዊ የአፈና ሥልትና በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነፍዘን እስከመቼ ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

በአምባገነናዊ የአፈና ሥልትና በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነፍዘን እስከመቼ ?

By   /   February 17, 2014  /   Comments Off on በአምባገነናዊ የአፈና ሥልትና በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነፍዘን እስከመቼ ?

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 59 Second

ገረመው አራጋው ክፍሌ-ከኖርዌ

አምባገነኖች ወደ ስልጣን የሚመጡት የህዝብን ቋንቋ እየተናገሩ ነው፡፡ የአገርንና የህዝብን ችግር መነሻ አድርገው የህዝብ ተቆርቋሪ ለህዝብ መብትና ጥቅም የተቆጨ መስለው ይጮሐሉ፡፡ የህዝብን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚታገሉ ህዝብ ከጐናቸው እንዲቆም ይለፍፋሉ… ሥልጣኑን ከያዙ በኋላ ህዝቡን ይረሱታል፡፡ ተገልብጠው ህዝብን ይሳደባሉ፡፡ በመሳደብ ሳያቆሙ ያስራሉ ይደበድባሉ ይገላሉ፡፡ የአገርንና የህዝብን ሀብት ለግላቸው ይዘርፋሉ ያዘርፋሉ፡፡ በተለያየ ዘመን በዓለማችን ላይ የተነሱት አምባገነኖች ያስተማሩን ይህንኑ ነው፡፡

በአገራችን የተንሰራፋው የወያኔ አምባገነናዊ መንግስትም እየፈፀመ ያለው ይህንኑ ነው፡፡ አርቴፊሻል የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን በማቋቋም እጅግ አደገኛ የሆኑ የአፈናና የሰብአዊ መብት ረገጣ ተቋማትን ሲገነባ ቆይቷል፡፡ የህዝብን ሀብት እየነጠቀ ወደ ተለያዩ የወያኔ ኩባንያዎች ለወያኔ አባላት ያድላል፡፡ ዜጐችን ከመኖሪያና ከሥራቸው እያፈናቀለ ለረሃብ ለቤት ችግርና ለእርዛት ዳርጓል፡፡ ህገ መንግስቱን ተማምነው ሥርዓቱን በህጋዊና ሠላማዊ መንገድ የሚታገሉ የሠላም አርበኛና ነፃ ጋዜጠኞች እጣ ፈንታቸው እያየን ነው፡፡

አምባገነኖች የሚያደምጡት ራሳቸውን ነው፡፡ ለአገርና ለህዝብ የሚጐዳ ተግባራቸው ሁሉ ለሥልጣናቸውና ሀብት ለመሰብሰብ እስከ ጠቀማቸው ድረስ ቅዱስ ነው፡፡

ማሰርም፣ መግደልም፣ ማስራብ እና ቤት ማሳጣት እርዛት መፍጠር ለአምባገነኖች ምናቸውም አይደለም፡፡ የህዝብ እንባና ሮሮ አያስበረግጋቸውም፡፡ እንዲያውም የበለጠ ልባቸውን ያደነድናቸዋል፡፡ ትናንት የሚናገሩት የህዝብ ቃል ሥልጣን ከያዙ በኋላ አያውቁትም፡፡ ተቃዋሚዎቻቸውን ተቺዎቻቸውን አስረዋል፣ ገለዋል፡፡ ህዝብን ይሳደባሉ፡፡ እነሱ ያሉትን ያልተቀበሉ ሁሉ በእነሱ ሚዛን ወንጀለኞች ናቸው፡፡ የወያኔ መሪዎችም የሚፈጽሙት ይህንኑ ነው፡፡ ዛሬ በየወረዳው በየቀበሌው የተንሰራፋው አስተዳደር ፍትሐዊነት የጐደለው ነው፡፡ ህዝብ የሚያውቃቸው የህዝብ አስተዳዳሪዎች ከየት ተሹመው እንደሚመጡም አይታወቅም፡፡

ተልዕኮአቸው የህዝብ ጥያቄን መፍታት አይደለም፡፡ የአፈና ሥራ መሥራት እና ዝርፊያ ማከናወንበሐሰት ፕሮፓጋንዳው፡፡ እያንዳንዱን ጉዳይ የሚመለከቱት ከአገርና ከህዝብ ጥቅም ሳይሆን ከወያኔ ሥልጣንና ከግል ጥቅማቸው አንፃር ነው፡፡ የወያኔ ሠላም ህሊናን ለወያኔ ዘረኛ አስተዳደር፣ ለወያኔ ሙስና አስተዳደር፤ ለወያኔ ኢ-ዴሞክራሲዊና ኢ-ሰብአዊ አስተዳደር፤ ለወያኔ ፍርደገምድል ዳኝነት፣ ለወያኔ ተቋማዊ ዝርፊያ አሚን ብሎ መገዛት ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ህጋዊና ሠላማዊ ሰው ነው ለመባል የወያኔን ወንጀል ልማት አድርጐ መቀበል ነው፡፡

ወያኔ የህዝብ ጥያቄን ሁሉ ጊዜ በብልጣብልጥነትና በአምባገነናዊ የአፈና ሥልት ማለፍ ይፈልጋል፡፡ ግን እስከመቼ? ስንት ዓመት ዜጐችን ማታለል ይፈልጋል፡፡ 22 ዓመት ሙሉ በጠብመንጃ ተገዝተናል፣ 22 ዓመት ሙሉ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነፍዘናል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ሌላ 50 ዓመት እንገዛችኋለን እያሉን ነው፡፡ ምኞታቸው ቀላል አይደለም፡፡ ዴሞክራሲ ህገ መንግስት እነሱ ዘንድ ትርጉም የሚሰጣቸው ለመድረክ ማድመቂያ ለወንበራቸው ማስጠበቂያ ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሰው በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ መብት አለው የሚለው ህገ መንግስት አንቀጽ 14 የአይን ቀለሙ እስካላማራቸው ድረስ የወያኔ ሎሌዎች ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ፡፡

ወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው  ፤ ወያኔ ፀረ-አማራ ነው  ፤ ወያኔ ፀረ-ሃይማኖት ነው ፤ ወያኔ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ዴምክራሲ ነው ፤ ወያኔ ኢትዮጵያንና ትውፊቶቿን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ ኃይላት ብቸኛ ወኪል ነው፡፡ይህን ካወቅን መፍትሔው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች በተገቢው ደረጃ ሕዝብን ማደራጀትና መርሆና፣ እቅዳቸውን ማስረፅ እንዲሁም ለለውጥ የተዘጋጀ ትግሉን ከዳር ሊያደርስ የሚችል ፍርሃትን የሰበረ የህብረተሰብ ሃይል ሊገነቡ ግድ ይላቸዋል፡፡የምንታገለው በሃገራችን በነፃነት የመኖር ሰዋዊ መብታችንን በአፋኝ አምባገነን መሪዎች በመነጠቃችን ነው፡፡ መብታችንን ለማስመለስ አስገዳጅ የትግል ስልት ካልቀየስን በስተቀር ወይም የስርዓቱን አፋኝ ህግጋቶች ላለመቀበል እምቢ እስካላልን ድረስ ከአምባገነን ስርዓት ተፈጥሯዊ ባህሪ አንፃር በነሱ ይሁንታ የምናገኘው ፍታዊ ምላሽ አይኖርምአ፡፡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በህዝብ ትግል ነው የሚከበረው፡፡  ከአምባገነንና ከብልጣብልጥ ድርጅት ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መጠበቅም አይገባም፡፡

ኢትዮጲያና ኢትዬጲያዊነት ለዘላለም ይኖራል። ወያኔ ግን በተባበረ የኢትዮጲያዊያን ጠንካራ ክንድ ይወገዳል!!

g.araghaw@gmail.com

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 17, 2014 @ 7:04 pm
  • Filed Under: AFRICA

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar