www.maledatimes.com ኦነግ ስንት መልክ አለው? ከቃሊት የግል ማስታወሻዬ። (አንተነህ ጌትነት ሙላቱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኦነግ ስንት መልክ አለው? ከቃሊት የግል ማስታወሻዬ። (አንተነህ ጌትነት ሙላቱ)

By   /   February 18, 2014  /   Comments Off on ኦነግ ስንት መልክ አለው? ከቃሊት የግል ማስታወሻዬ። (አንተነህ ጌትነት ሙላቱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:82 Minute, 49 Second

ኦነግ እና ኦብነግ በሻቢያ እና በአህዛቡ ወያኔ ተጠፍጥፈው የተሰሩ ናቸው።በመሆኑም ከጠፍጣፊዎቻቸው እና ከጌቶቻቸው አረቦች እና ምዕራባዊያን ውጭ ማሰብ የማይችሉ በመሆናቸው የጀመሩት የትግል ስልት አዋጭ እንዳልሆነ ቢያውቁም እንኳን ሌላ ስልት ለመንደፍ ሲሞክሩ እንኳን አልታዩም። በመሆኑ የያዙት መንገድ እጅ እጅ ቢላቸውም ምንም ማድረግ ስለማይችሉ እየተደነባበሩ መጓዛቸውን ቀጥለዋል።
የሚከተሉትም መንገድ ምዕራባዊያን እና አረቦች ነድፈው ለአስፈጻሚዎቻቸው የእናት ጡት ነካሾች ሻቢያና አህዛቡ ወያኔ ተቀብለው የሰጧቸው ኢትዮጵያን የመበታተን ሴራ ለማሳካት ደፋ ቀና ከማለት ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላቸው ጭራሽ ሂሊና የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው ጉዶች ናቸው። ደርግ የናት ጡት ነካሾች ማለቱ ወዶ አይደለም። እነሱ ከታዘዙ የናታቸውን አይደለም የራሳቸውን ጡት ከመንከስ የማይመለሱ ይሁዳዎች ናቸው።
እውን ኦነግ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አለው?
የዛሬ ጽሁፌ መነሻ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የቃሊቲ ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል የሚለው አነጋገር ነው።ይህን የሚል ሰው ኦነግ በሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ተቀባይነት እንዳለው ለማስመሰል እንጂ የቃሊቲ ቋንቋ የወለጋ ኦሮምኛ እና በጥቂቱ የአምቦ ኦሮምኛ ሆኗል ቢባል እውነታውን ይገልጻል።ይህንንም የምልበት ዞን ሦስት እና ዞን ሁለት በታሰርኩባቸው ጊዜያቶች ያረጋገጥኩት
ሃቅ ነው።ይህን በተመለከተ በኦነግ ምክንያት ከታሰሩ ግለስቦች እንደተረዳሁት እዚህ እስር ቤት ብቻ ሳይሆን ኬኒያ ስልጠና ላይ በነበሩ ጊዜ የነበረው ከዚህ የተለየ አልነበረም። ኬኒያ ወታደራዊ ስልጠና ወሰዶ የተመለሰ የኦነግ አባል የነበረ ጓደኛ እንዳጫወተኝ ኬንያ በሰለጠንበት ጊዜ በሥልጠናው የነበሩ በብዛት የወለጋ ኦሮሞና በተወሰነ ደረጃ ደግሞ የአምቦ ኦሮሞዎች
ሲሆኑ በጣት የሚቆጠሩ ደግሞ ከሸዋ እና ቦረና ኦሮሞዎች እንደነበሩ አውግቶኛል። ይህ ለምን የሆነ ይመስለሃል ስለው?
ስልጠና በነበርኩት ጊዜ በተለይ የጉጂ ና የቦረና ኦሮሞዎች ያለሰለጠኑ እንደሆኑና የሸዋ ኦሮሞ ደግሞ የአማራ ስሜት የሚጸናወታቸው ጎበናዎች ናቸው እየተባለ በሰፊው የሚነገር ስለነበረ እንዲሁም የሐረር፣የአሪሴ፣ባሌ እና ጂማ ኦሮሞዎችን ደግሞ የእስልምና ስሜት የተጠናዎታቸው የአረብ ተላላኪዎች ናቸው በማለት እንደሚፈርጇቸው አስታውሳለሁ። እኔም
የዚህ ስሜት ተጋሪ እንደነበርኩ አስታውሳለሁ። ከስልጠና በኋል ግን በቦረናና ጉጂ አካባቢ እንቀሳቀስ ስለነበር ያረጋገጥኩት ሃቅ በጭራሽ ኦነግ የምትሉትን ወኦነግ ( ወለጋ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር) ለምን አትሉትም የሚል ምላሽ ከተለያዩ ቦታዎች በማግኘቴ ከፍተኛ የሆነ ግራ መጋባት በውስጤ መፈጠሩን በወቅቱ አስታውሳለሁ። አንድ ቀን ያቤሎ ከተማ ለሥራ ተልኬ
ሄጄ በነበርኩበት ጊዜ አንድ በዕድሜአቸው የገፉ የትልቅ ሆቴል ባሌቤት ጋር የመገናኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር። የጫወታዬ መጀመሪያ መከረኛ አማራን ማማት ስለነበረ አማራ የኦሮሞ ልጆች እንዳይማሩ በማድረጉ ለከፍተኛ ጭቆና ተዳርገን መቆየታችንን እያወጋኋቸው እያለ በመሃል ጭቡ አትናገር ልጄ እኔ በኃይለስላሴ ጊዜ የማውቀውን ልንገርህ ንጉሡ ከቦረና
15 ልጆችን ለማስተማር አስመርጠው ከጨርሱ በኋል ለመውሰድ ወላጆቻቸውን ሲጠይቁ ሁሉም አሻፈረኝ በማለታቸው እንደቀሩ አስታውሳለሁ። ይህ ታዲያ ጥፋቱ የአማራ ነው ወይስ የኛ? ተው ተው ጭቡ መናገር ጥሩ አይደለም የልቁንስ የቦረና እና የጉጂ ኦሮሞ ከምንጊዜውም በላይ እየተበደለ ያለው በወለጋዎች እና በአሪሲዎች ነው። በቦረናና ጉጂ ግዛት
በሙሉ ስልጣኑን እነሱ ይዘውት መከራችንን እያበሉን ናቸው። እንግዲህ አማራ የምትላቸው እነሱ ከሆነ ልክ ነህ እኛን መከራ እያበሉን ያሉት ወለጋና አሩሲዎች እያሉ እባክህን ልጄ አማራ አማራ እያለክ ጭቡ አትናጋር እንደድሯችን ፍቅሩ ይሻለናል ብለው ኮስተር ሲሉብኝ ከዚህ በላይ ማለፉ እንዳማያዋጣኝ ስለተረዳሁ ውይይቴን ወደሌላ ርእስ አዞርኩት።
ያቤሎ የገባሁት ነጋዴ በመምሰል ስለነበር ከነጋዴውም፣ከወጣቱም፣ ከሴቴኛ አዳሪውም፣ከአስተማሪው እና ከተማሪውም በተለያየ አጋጣሚ የመገናኘት ዕድል ያገኘሁ ቢሆንም ያገኘሁት ምላሽ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ የመጨነቅ እና የመበርገግ ስሜት ነበር የተሰማኝ።በውስጤም ወለጋዎች እና ጥቂት አምቦዎች ብቻ የሚደግፉት ድርጅት ነው? የሚል ስሜት ተሰምቶኝ
ነበር። በኦነግ፣በኦብኮ፣በኦፊዴን እና በኦሮሞ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶ በአብዛኛው በወለጋና አምቦ ኦሮሞዎች መመራታቸው እንዲሁም ኦህዴድ በየተራ በወለጋና አሪሲ ኦሮሞች መመራቱ ሌላው የኦሮሞ ማህበረሰብ የተማረ ሰው በማጣቱ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት ያለ ይመስልሃል? ላልኩት ጥያቄ የሰጠኝ መልስ ይህን ነገር የተረዳሁት በጥቆማ ተይዤ
ቃልቲ ከመጣሁ በኋላ ነው። በተለይ ከሸዋ፣ባሌና ጅማ ኦሮሞዋች ጋር የመገናኘት እድል በማግኘቴ የኦነግ ድጋፍ ከወለጋ እና አምቦ ያለፈ እንዳልሆነ በትክክል ተረድቻለሁ።ለጠየከኝ መልስ አጎቴ እንደነገረኝ መኢሶን የነበሩ የወለጋና አንቦ ልጆች በኋል ወደ ኦነግ በመምጣታቸውና በትምህርትም የተሻሉ ስለሆነ ይመስለኛል ብሎ አጫውቶኝ ነበር።እኔ ግን በትምህርት ሳይሆን
ከገጠመኞቼ እንደተረዳሁት እኛ ወለጋዎች ጠባብነት በጣም የሚያጠቃንና ከሌሎች ኦሮሞችን የተሻልንና የሰለጠን ነን ብለን ስለምንመጻደቅ ሌሎች ወደ ስልጠን ሲመጡ እንኳን ለመቀበል ፈቃደኞች አይደለንም። ታዲያ ኦነግ ለስልጣን ቢበቃ ከወለጋ ውጭ የሆነውን ኦሮሞ እንዴት ለስልጣን ያበቃው ነበር ትላለህ? ለምን ታስጎመጀኛለህ? ኦነግ ለስልጣን አይበቃም ብለህ
ታስባለህ? ጨካ እያለሁ ነበር ኦነግ ለስልጥን ይበቃል ብዬ አስብ የነበረ!!! አሁን ቃሊቲ ከገባሁ በኋል እውነቱ የት ላይ እንዳለ ስለተረዳሁ ይህን ጥያቄ እንለፈው። እንግዲህ ከዚህ የምትረዱት የቃሊቲ ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል ማለት ትክክል አለመሆኑን ሲሆን እውነታው ግን የቃሊቲ ቋንቋ የወለጋ ኦሮምኛ ሆኗል ማለት ነው ።አንዳንድ ሰዎች የቃሊቲ ቋንቋ ኦሮምኛ
ሆኗል የሚሉት ኦነግ በሁሉም ኦሮሞ ማህበረሰብ ተቀባይነት እንዳለው ለማስመሰል ካልሆነ በስተቀር ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ክርስቲያን የሆነው የኦነግ አባል ሰፊ ድጋፍ ያለው በወለጋ አካባቢ ሲሆን እንዲሁም እስላም የሆነው የኦነግ አባል
በሐረር አካባቢ እንዲሁም በመጠኑ በአረሲና በጂማ አካባቢ ተቀባይነት እንዳለው ተረድቻለሁ ለምን ቢባል ለእስልምና
አክራሪነታቸው ከለላ እንዲሆናቸ ስለሚፈለጉ ብቻ እንጂ ኦነግን እንደማይፈልጉ ግንዛቤ አግኝቻለሁ። በሌላው ክልል ግን
ድጋፋቸው እዚህ ግባ የማይባል እና ጭራሹኑ የማይታወቅባቸው ቦታዎች ሁሉ እንዳሉ በእስር ቤት የተረዳሁት ሀቅ ነው።
በአጠቃላይ የኦነግ መሪ ተብዬዎች ግባቸው ሥልጠን እንጂ ሌላ ምንም አይደለም።የስልጣን ጥማት ጌታቸውን ኢሳያስን
እብድ አደረገው እንጂ ያገኘው ነገር የለም።የኤርትራ ሕዝብ ለነጻነት ሳይሆን በተቃራኒው ለባርነት፣ ለችግርና ስደት
እንዲዳረግ አደረገው እንጂ። አብዮት ልጇን ትበላለች እንደሚባል ኢሳያስም አብረው የታገሉትን የበላ አውሬ ሆነ እንጂ
የለወጠው ነገር የለም።ምን አልባት አንድ በቅዱ መሰረት እየተገበረው ያለው ነገር የኢትዮጵያን የ100 ዓመት የቤት ሥራ
በእኛ ጂላጅሎች እያስፈጸመ መገኘቱ ብቻ ነው።
ምኞት የቁም ህልም ነው።በሐሳብ ተቀርጾ በቅዥት የሚወለድ ነው።( ዜና መዋዕል)።
ኦነግ በኦሮሞ ማህበረሰብ ተቀባይነት እንደሌለው ቢታወቅም ምኞች አይከለከልም እንደሚባለው ቃሊቲ
ዞን 2 በነበርኩበት ጊዜ አንዱ “ ኢላማን ኩሸቲኪ የሚል ደቡብን የጨመረ ካርታ” ያለበት ከነቴራ ለብሶ
ሳይ ደግሞ ጉድ ሳይሰማ ዶሮ አይጮህም እንደሚባለው ዓይኔ የሚያስገርም ጉድ አሳየኝ። እኝ ሰዎች
የደቡብ ህብረተሰብን ጽኑ ኢትዮጵያዊነት እንኳን ሳያውቁ በደመነፍስ የሚንቃሳቀሱ ፍጡሮች መሆናቸውን
ያሳየኝ አጋጣሚ ነው። የሆነውስ ሆኖ የቅንጅት ሰዎች ለምን የቅንጅት አርማ ያለበትን ከነቴራ ለበሳችሁ
ተብለው የሚያዩት የነበረው ስቃይ ሁሉም የሚያውቀው ነው። አይደለም ቃሊት አዲስ አበባ እንብርት
ከተማችን እንኳን የተከለከል በመሆኑ በለገሰ ዜናዊም ትዛዝ ጣት እንዲቆረጥ ተደርጓል። ቃሊቲ ያሉ
የአህዛቡ ወያኔ ደናቁርት የትግራይ ተወላጅ ፖሊሶች ይህንን እያዩ ዝም ያሉበት ምክንያት ከላይ ከህወሃት
የወረደላቸው መመሪያ ስላለ እንጂ ህወሓትን መቃወም ማለት በዓይናቸው ላይ መምጣት ማለት ነው።
በቃሊት ትምህርት ለመማር በቅንጅት የታሰሩት እስረኞች ሲከለከሉ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመው የታሰሩ የኦነግ ጀሌዎች ግን እንዲማሩ ይፈቀድላቸው ነበር።ይህ የሚያሳየው አህዛቡ ወያኔ ከኦነግ ጋር የከረረ ፀብ
እንደሌለው በተጨባጭ የሚያሳይ መረጃ ነው።
ኦነግን ሽፋን ያደረገ የእስላም አክራሪነት በሐረር እና በአሪሲ!!!
የሐርር ኦሮሞ እና የአሪሲ ኦሮሞ ለእስልምናው አክራሪነት ሽፋን እንዲሆናቸው እንጂ ወደ ኦነግ ትግል የተቀላቀሉት የኦነግን
ዓላማ ደግፈው አይደለም ይባላል ይህ ምን ይመስለሃል ? ብዬ ለጠየኩት የሰጠኝ መልስ ይንንም የተረዳሁት እዚሁ ቃልቲ
ነው የቃሊቲ ጉድ ብዙ ነው። ከአርሲ እና ከሐረር ኦሮሞዎች ጋር ስንጨዋወት የነገሩኝ ነገር እጅግ ነው የዘገነነኝ።አማራ
ክርስትናን ወደ አካቢያቢያችን አመጣብን እንጂ ክርስትና በጭራሽ በአካቢያቢያችን አይታወቅም ነበር። ስለሆነም አማራ እና
ክርስትና ከአካባቢያችን ተጠራርገው እስካልወጡ ድረስ እረፍት የለንም። በመሆኑም አባ ጃራ(ባንዳው)በሱማሌ
ጦርነት አማራን እና ክርስትናን በተለይ ኦርቶዶቅስን ለማጥፋት ትልቅ መስዋእትነት መክፈሉ በሂሊናችን ተቀርጾ ይኖራል።
የእኔም አባት የሞተው ለሱማሌ ሲዋጋ ነው። ይህ አባቴ የጀመረው ትግል አንድ ቀን በድል ይጠናቀቃል ነበር ብሎ የነገረኝ።
ያለፈው የሱማሊያ ውጊያ ጊዜ የድሬዳዋ ህዝብ የጃራ ጦር ፈጀን ያለው እውነታ ይህ ነው። እንግዲህ ወላጆቻቸው እና
ታላቆቻቸው ሀገራቸውን ከጠላት ጋር ወግነው ማድማታቸውን እንኳን እንደ ጀግንነት የሚያወሩ ጉዶች በለስ ቢቀናቸው
የለመዱትን በቁም ማረድ እንደሚደግሙት ልቦና ያለው ልብ ይበል። ኦነጉ ጓደኛዬ እንዳጫወተኝ እኔ ክርሲቲያን ስለመሆኔ
በጭራሽ አልዞረለትም ነበር። ነገርግን ኦነግ ስለመሆኔና ኬኒያ ስልጠና ወስጄ መመጣቴን እንጂ እኔ የምን እምነት ተከታይ
እንደሆንኩ በጭራሽ ሳያውቁ ነበር እሱና ጓደኞቹ የልባቸውን የዘከዘኩልኝ። ይህን ማድረግ እንዴት ይቻላል? ብዬ
ስጠይቃቸው የሰጡኝ መልስ መሪዎቻችን እንደነገሩን ከሳውዲ፣ከሶሪያ፣ከሱዳነና ከግብፅ ከፍተኛ ድጋፍ ስላለን ትግላችን
እንደሚሳካ ጥርጥር የለንም። አላህ ብሎ ከእስር ከተፈታን ተመልሰን ለዓላማችን እንሞታለን ብለውኝ እርፍ።ታዲያ እኝህ
ሰዎች ከአማራና ሌሎች ኢትዮጵያን ክሪስቲያኞች በኋል ወይስ ከአማራ ጋር የኦሮሞን ክርስቲያን የሚያጠፉት ብዬ ሳስብ
ዘገነነኝ። ነገሩ ስለጎመዘዘኝ እንዲህ ከሆነ የኦነግ ትግል እንዴት ሊሳካ ይችላል? ስላቸው ክርስትናንና አማራን ከሐረር ዙሪያ
ካጠፋን በኋል የኦነግ ትግል ይቀጥላል የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ነበር የሰጡኝ ።ኦሮሞ ክርስቲያን እንዳለው አታውቁም
ስላቸው እናውቃለን ክርስትና አማራ ያመጣባቸው ጣጣ በመሆኑ ወደ ዋቄፈታ እንዲመለሱ ከዚያም ደግሞ እስልምናን
እንዲቀበሉ እናደርጋለን።ክርስትናችንን አንተውም ብለው እምቢ ቢሉስ? እንደዚህ ካሉማ አማራ ሆኑ ማለት ነው።የሚል
ቁርጥ ያለ ምላሽ ሲሰጥኝ ኦነግ ለካ የለችም ሃሌ ሉያ በህይወት አትርፈህ ቃሊቲ እንድታሰር ላረከኝ ጌታ ብዬ በልቤ
አመሰገንኩት ከዛች ቀን በኋል ኦነግ የሚል ስም ከምንም በላይ ያንገሽግሸኝ ጀመር።እንግዲህ አስብ እነሱ በአማራውም ሆነ
በሌላው ኢትዮጵያዊ ጅሃድ ሲያውጁ እኔ ክርስትናን ለመጠበቅ ዘብ የማልቆም ጂላጂል መሰልኳቸው እያልኩ በልቤ
ረገምኳቸው ጠላቴም አረኳቸው።
ኦነግን የተቀላቀሉ የኦሮሞ ወጣቶች በትክክል የኦነግ ዓላማ ገብቷቸው ነው?
ቃሊቲ ታስረው ያሉት ወጣቶች የኦነግ ዓላማ በቅጡ የተረዱት ይመስልሃል? አንተ ሰው በሆዴ ያለው እንዳይቀር
የምትፈልግ መሰለኝ። ልቀልድ ነው እንደዚህ ስተነፍስ ውስጤ ሰላም ያገኛል።እዚህ ታስረው የምታያቸው ሁሉም ማለት
ይቻላል ኦነግን ሳያውቁት ፈጀኝ ፈጀኝ እያሉ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤችና በኮሌጆች ግቢ ሲለፈልፉ የተያዙ ቱልቱላዎች
ናቸው።ነገረግን ኦነግ ማለት ምን ማለት ነው የሚሉኝ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ና የኮሌጅ ተማሪዎች እንዴት ኦነግ
ተብለው እንደታሰሩ ግራ ይገባኛል? አንዳንዶቹ ኦነግ የሆኑ ቃሊቲ ከገቡ በኋል ከሌሎች ጥቂት ኦነጎች ተምረው ነው።
በአብዛኛው ስለኦነግ ምንነት የማያውቁ እስረኞች ናቸው።ሲተኙ እንኳን አታያቸውም ከሌሎች እስረኛ ጋር ከተቀላቀሉ ኦነግ
ያለሆኑ ስለሚመስላቸው እንደማይቀላቀሉ።ከሸዋ ኦሮሞ ልጆች ጋር በተደጋጋሚ ለመጋጨት ሲሞክሩ እኛ በመሃል እየገባን
ፀቡን ባናበርድ ኖሮ የሚፈጠረው ችግር ምን እደሚሆን አስብ ።አታስታውስም ደረጀ ከአንድ ኦነግ ጋር ተጣልቶ ድንጋይ
አንስቶ ሊፈረክሰው ሲል እኔ ና አንተ ደርሰን ነፍሱ ያተረፍነው።እንዲሁም ገመቹ የቡራዩ ኦሮሞ ከአንድ ኦነግ ጋር ተጣልቶ
ከፍተኛ ፍጥጫ ላይ ደረሰው እንደነበረ። ታዲያ ወያኔ ለምን ያስራቸው ይመስለሃል?ጥያቄህን አንተ ራስህ መለስለኝ?
እኔ የሚመስለኝ ወያኔ ቃሊቲ የሚያስራቸው ነገ ከሥልጣኑ ቢባረር ኢትዮጵያን የሚያተራምሱ ጎጠኞች እያደራጀ
ይመስለኛል እንጂ ኦነግ እንዳልሆኑ በትክክል ያውቃል። ስንት ሰውን ያረዱ፣ያሳረዱ ና ያስገድሉ እውነተኛ ኦነጎችን በይቅርታ
እየለቀቀ ምንም የማያውቁትን ማሰሩ ታዲያ ምን ምክንያት ቢኖረው ነው። አንተስ ምን ይመስልሃል? ምን አልባት ኦነግ ነን እያሉ ቱልትላቸውን ሲነፉ የተያዙ ይመስለኛል። ታዲያ ነፍሰ ገዳዮችን በይቅርታ እየለቀቀ ወሬ ስለአወሩ ብቻ ማሰሩ ለምን
ይመስልሃል? እንዳለከው ሌላ ምስጢር ያለው ይመስላል። አንተ ታዲያ አሁን ምን ታስባለህ? ከዚያ በኋላ ኦሮሚያ ማለት
የቷ እንደሆነች ግራ ስለገባኝ እኔ ማን ነኝ የሚል ጥያቄ እያቃጨለብኝ ስለሆነ ከአንተጋር ተወያዬሁ እንጂ አማራ አልወድም
ነበር። ታዲያ አሁን አንተ ማን ነህ?ኢትዮጵያዊ፣ክርስቲያንና ኦሮሞ ግን ኦነግ አይደለሁም። ያን ሁሉ መስዋእትነት
የከፈልክበትን ድርጀት በቀላሉ መተው ይቻልሃል? እውነት የማይለውጠው ምንም ነገር የለም!!! እንግዲህ አማራ ሆንካ
ማለት ነው? ሳቅ ካ…ካ…ካ። በዚሁ ውይይታችንን ቋጨን።
እማማ ሮማን “ ቅቤና ቅልጥም ምን ይገጥም።” እንዳሉት ኦሮሞና ኦነግ በምንም አንድ እንዳልሆኑ እየታወቀ አህዛቡ
ወያኔ ደጋግሞ ውሸት ሲነገር ይሰርጻል እንደሚለው ኦነግ ነን ባዮችም “ማስረጽን” እንደ ግል አዳኛቸው ቆጥረዋት ዘወትር
ያደነቁሩናል። የአኖሌ( የነነሁልሌ) ሐውልትም አሪሲ መሆኑ ለምን ይሆን? የአሪሲ ልጆች ዓላማ ምን ይሆን? የሚል ጥያቄ
ያጭርብኛ። ጁሐርስ ማን ነው? ብዙ ጊዜ እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ እውነትን በድፍረት በመናገር ተወዳዳሪ የሌለው
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እና ደፋር ሰው እስከአሁን አልገጠመኝም። በቅርቡ በአሲንባ ፓልቶክ የሰጠው ቃለመጠይቅ
በሀገርቤት፣በውጭ ሀገርና ኤርትራ ውስጥ ስለሚገኙ እና የነሱ ስለሆኑ ሚዲያዎች እንዲሁም ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ እዳለች
ቁልጭ አድርጎ አብራርቷል።በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ታስረው ስላሉት የእስላም መሪዎችና ተከታዮቻቸው ዝርዝር አድርጎ ከዚህ
በፊት በጽሁፍ ማቅሩቡን አስታውሳለሁ እውነትን እንደወረደች በማቅረቡ ሚዲያዎች ሁሉ የሱን ጽሁፍ ለማውጣት
ቢርበተበቱም ግንቦት7d በማውጣቱ ምስጋናዬ የላቀ ነው። የኢትዮጵያ አምላክ ዕድሜውን ያርዝመው እውቀቱንም
ይጨምርለት። አቶ ጌታቸው በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ በእስር ታስረው ከሚገኙት ውስጥ የተወሰኑት የእስልምና መሪ ተብየዎች
እና ሌሎች የእነሱ ዓላም አራማጅ እስላሞች ከኢትዮጵያዊ ወንድሞቻቸው ይልቅ የሌላውን ሀገር እስላም እንደ ወንድማቸው
ያዩታል ያለውን ሙሉ በሙሉ እቀበለዋለሁ። በአንድ ወቅት በአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከአልጀሪያ ጋር ስትጫወት ጥቂት
የማይባሉ እስላሞች ከኢትዮጵያ ይልቅ አልጀርያን ሲደግፉ ሳይ የተስማኝ ሃዘን ወስን የለውም። ስለታሱሩ ብቻ
ልንደግፋቸው አይገባም።የታሰሩ ሁሉ እውነተኛ ኢትዮጵያን ቢሆኑ ኖሮ እግራቸው ሥር ውድ የአዲስ አበባ ወጣቶች
የተደፉላቸው ዶ/ር ብርሃኑና ወ/ሮ ብርቱካን ሚዴቅሳ እንደዚህ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚከዱበት ወኔ አይኖራቸውም ነበር ።
በወቅቱ የታገሉት ለስልጣንና ለግል ዝና ነው።ሌላው ቢቀር ወ/ሮ ብርቱካን በታሰረች ጊዜ ለብሳው የነበርው ጥቁር የሀዘን
ልብስ ጥላው ካልሆነ በቀር በአህዛቡ ወያኔ ወታደሮች አልሞተኳሽ አረመኔ ወታደሮች እግሯ ሥር የተደፉ ብርቅዬ ጀግኖችን
የፈረንሳይ ለጋሲዮን ልጆች ያስታውሳት ነበር።በቅንጅት የታሰረ ሁሉ ሀገር ወዳድ ነው ብለን እንደተጃጃልነው በአሁኑ ሰዓት
ቃሊቲ ታስረው ከሚገኙ የእስልምና ተወካዮች ውስጥ አህዛቡ ወያኔ በ1984 እና በ1985 አካባቢ በሱዳን እና በተለያዩ
የአረብ ሀገሮች ልኮ ያሰለጠናቸው የአረብ ቡችላዎች እንዳሉበት ምስጢር አይደለም። ይህንንም ለመረዳ አቶ ጌታቸው ረዳ
“በፖለቲካና በሐይማኖት የማሻኮር በሃሪ” የሚለው ጹሁፋቸው ማንበብ በቂ መረጃና ምስክር ነው።ታዲያ እንዴት ብዬ
እነዚህን እስረኞች አህዛቡ ወያኔ ስላሰራቸው ብቻ በጅምላ ለመደገፍ ልቦናዬ አይፈቅድም። ጁሃር መሐመድም የነዚህ ወገን
ስለሆነም ነው ኦሮሞነቴ ይቀድማል ያለው። ግራኝ መሐመድ በአባቱ ክርስቲያን ቄስ በእናቱ እስላም ነው ስለሚባል መሰለኝ
ጁሐርም ደግሞ በአባቱ እስላም በእናቱ ክርስቲያን ነኝ የሚለን።ይህን ማለቱ የግራኝ መሐምድ ወራሽ ነኝ እወቁልኝ ማለቱ
እንደሆነ ከዚህ መረዳት የሚያቅተን አይመስለኝም። የእነዚህ የጥቂቶቹ አክራሪዎች ፈልግ ተከታይና በወያኔ የሰለጠነ
ስለሆነም ነው ጅሃድ እያወጀብን የሚገኘው።ኦነግ ለእሱ ሽፋን እንጂ የኦነግ ዓላማ አራማጅ አለመሆኑን ሥራው
እየመሰከረበት ነው!!! አዲስ አበባ ውስጥ በአብዛኛው የቴኳንዶ ት/ቤት ባሌቤቶ እስላሞች ሲሆኑ ትልልቆቹ በአላሙዲን
የሚረዱ ናቸው። በአንድ ወቅት በእስላም ባለቤትነት በተያዘ ቴኳንዶ ት/ቤት ምረቃ በዓል ላይ ልጁን ለማስመረቅ የተገኘው
ጓደኛዬ እንዳጫወተኝ ከ200 በላይ ከሚሆኑት ተመራቂዎች ውስጥ ክርስቲያን የሱ ሴት ልጅ ብቻ እንደነበረች ነበር ያወጋኝ።
ይሁንና ያስደነገጠው ነገር ይህ ብቻ አልነበረም።የቴኳንዶ ት/ቤቱ ባለቤት እስላም ሲሆኑ ለጊዜ ስሙ ስለጠፋብኝ ይቅርታ
እጠይቃለሁ። የተናገሩት ግን እጅግ አስደንጋጭ ነበር። የተናገሩትም “ወላጆች ሆይ እኚህ ልጆች አንድ ቀን
ስለሚጠቅሙን በእንክብካቤ እና በጥንቃቄ ያዙዋቸው!!!” ነበር ያሉት። እንግዲህ
እግዚአብሄር ያሳያችሁ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ምን መልክት ነው ለሙስሊሞች እያስተላለፈ ያለው?እንግዲህ ወደፊት
በሀገራችን የሚመጣው ችግር ምን ያህል አስፈሪ እንደሆነ አስቡ። በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግ ለወደፊቷ
ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ የጎላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የሚል እምነት አለኝ። ይህን ስል ቅን የሆኑ እስላሞች እንዳሉ አልክድም።
የእኔ የቅርብ እና እጅግ የምወዳቸው የእስላም ጓደኞች አሉኝ። እነዚህም ጓደኞቼ የዚህን ዓይነቱን አክራሪነት ከኔ በላይ እጅግ
አምርረው እንደሚጠሉት አውቅ ነበር ። ልቦና ያለው ልብ ይበል!!! የኦነግ ሰዎች ከወላጆቻቸው ሻቢያና ወያኔ ቅጥፈት ለመማር ያቃታቸው ለምን
ይሆን ?
“ ፖለቲካ ውስጥ እውነት ከቀላቀልክ ፖለቲካ የሚባል ነገር አይኖርም!!!”ዊል ሮጀርስ።ለዚህም ነው ቻርልስ
ደጎል ፖለትከኛ ራሱ የሚናገረውን ራሱ አያምንም።ነገርግን ሌሎች ሲያምኑት ግርም የሚለው ያለው። ኦነግ ነን ባዮች
ምኒሊክ 5,000,000 ኦሮሞችን አስፈጂቷል ይሉናል።እንግዲህ በምኒሊክ ጊዜ 10,000,000 ህዝብ ነበር ብንል እጅግ
አብዝተን ካዛ ውስጥ ኦሮሞ ግማሹ ነው ቢባል እንግዲህ ኦሮሞ ጠቅላላው አልቋል ማለት ነው።ታዲያ አሁን ያሉት
ኦሮሞዎች በእንኩቤተር የተፈለፈሉ ፍጥሮች ናቸው ማለት ነው?????? ይህ የኦሮሞን ህዝብ ለማጃጃል ከመሞከር ያለፈ
አይደለም። እነዚህ ይሉኝታ ያለፈጠረባቸው ጁሐርና ተከታዮቹ ገና ብዙ እንደሚሉን መጠበቅ አለብን። ፊደል ቆጠርን
የሚሉት የወለጋ ልጆች እና ጥቂት የአንቦ ልጆች በኦነግ በፕሮፓጋንዳ ተታለው ስላልገባቸው ነገር ሲለፈልፉ ተይዘው ቃሊቲ
ሲገቡ ከእንቅልፋቸው ይነቁና የሚይዙት የሚጨብጡትን እንደሚያጡ ያየሁትና የታዘብኩት ነው።በዚህ ሰዓት
ለተመለከታቸው እንዴት አንጀት እንደሚበሉ ለመግለጽ ቃላቶች ያጥሩኛል። ምንም ቢሆኑ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ስለሆኑ
በወጣትነታቸው ለእስር በመዳረጋቸው እጅግ ያሳዝኑኛል።ሌላው ደግሞ ኤርትራ በረሃ አዲሼጋላ የምትባል በግምት ከሃሬና
15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በነበርኩ ጊዜ ያገኘሁት የኦነግ ታጋይ ደግሞ ከሚስቱና ከአራት ልጆቹ ከተለያየ ከዛሬ 3 ዓመታት በፊት
እንደነገረኝ ከ25 ዓመታት በላይ በረሃ እንዳሳለፈ ሲነግረኝ ምን ያህል እንደዘገነነኝ አስታውሳለሁ። አሁን ላይ ሆኘ
ሳስታውሰው እግዚአብሄርን ከነዚህ የተረገሙ ሻቢያዎች መንጋጋ በማውጫው ስላወጣኝ ዘወትር ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ።
በእድሜው ጠና ያለ ሰው ስለሆነ አሁን ምን እያደረክ ነው ስለው እነዚህን የኦነግ ፍየሎች እየጠበኩ ነው ። በኦነግ
ፕሮፓጋንዳ ተታሎ ውጤት ሌለው ነገር ከሚያፈቅራቸው ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ፍየል ጠባቂ ሆኖ መቅረት ምን ያህል ዘግናኝ
እንደሆነ አስቡ። ልጆች ያሉት እራሱን በዛ ቦታ አድርጎ ቢያየው ከባድነቱን ለመረዳት አያቅተውም።ከሁሉም በላይ ከባድ
የሚሆነው በጠላት መሐል ተከልሎ ጠላትን ለማጥቃት ጠመንጃ ማንሳት ምን ያህል አስፈሪና ተስፋ አስቆራጭ እንድሆነ
ሲያስቡት ደግሞ ለእርድ ከቀረበች በግ የተለየ አይደለም።ኤርትራ ውስጥ መታገል ውጤት የሌለው እንደሆነ የተረዳሁትም
እሱን ካገኘሁ በኋላ ነው። ስለ ኦነግ መሪ ተብዬዎች ጭካኔ ሳስብ ከፋሽስቶች በላይ ፋሽስት እንደሆኑ ሥራቸው
ይመሰክራል።ይህ ሰው ከውድ ባለቤቱ እና ልጆቹ ሳይገናኝ ፋይዳ በሌለው ነገር ሂይወቱ እዚያ በረሃ እንደሚያለፍ ሳስብ
እጅግ ይዘገንነኛል።እግዚአብሄር በመውጫው አውጥቶ ከቤተስቡ ያገናኘው።
“ገልቱ ባል ያላት ሴት ለሌላው ሚስት ትሆናለች!!!” የምለው አባባል ኤርትራ ውስጥ መሽገው ያሉትን
ተቃዋሚዎችን ያስታውሰኛል።የነሱ ገልቱነት ለአህዛቡ ወያኔ ሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉት ርዕስ የፈጠርለት
በመሆኑ ለምሳሌ፦ የኦነግ፣የኦብነግ፣የግንቦት7 እና የመሳሰሉት ድርጅቶች አባል ናችሁ በመባል የታሰሩትን ንጹሃን ዜጎች
ቤት ይቁጥራቸው።የቅርቦቹ እነ አንዱዓለም እና እስክንድርን ብንወስድ እንኳን ግንቦት7 የሚል ስም በክሳቸው
እንደተለጠፈና ለሃሰተኛው ክሳቸው ማጠናከሪያ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም።ስለዚህ ኤርትራ ውስጥ ያሉ በኃይል
እንታገላለን የሚሉ ድርጅቶች እውነት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ናቸው? በእኔ እይታ በጭራሽ የነጻነት ትግሉን ለማሰናከል
የቆሙ ባይሆኑ ኖሮ ኤርትራ ውስጥ ምንም ለውጥ እንደማይመጣ እያዩና እያወቁ ዝምታንን ይመረጣሉ ብየ አላስብም።
አርበኞች ግንባርን የመሰሉ አስቀድመው የገቡት አንዳንዶቹ መሪዎች መውጫ ቀዳዳ አጥተው እንጂ እውነታውን
እንደተገነዘቡት አውቃለሁ።ነገርግን ግንቦት7 እና ኦነግ ሌላ ተልኮ ስላላቸው እንጂ የኤርትራ ትግል ውጤት እንደሌለው
በሚገባ ያውቃሉ።የህዝብ ዓይንና ጆሮ ነን የሚሉት ነገርግን የግንቦት7 አፈቀላጤዎች ኢሳትና አብዛኛዎቹ ድህረ ገጾች
ታማኝነት በማጣታቸው በውጭ ከሚኖረው እና ከሀገር ቤት የገንዘብ ድጋፍ የነጠፈባቸው ሲለሆነ የገንዘብ ምንጫቸው
ከወዴት ነው ለሚለው ጥያቄ መልሱ ከማይታወቅ አካል ነው።ያ አካል ማን ነው? የኢትዮጵያ ጠላት ካልሆነ ማንም ሊሆን
እንደማይችል ዶ/ር ብርሃኑ ከዚህ በፊት በሰጠው መግለጫ ግልጽ አድርጎታል።
እንግዲህ ኦነግ(“ ወኦነግ” ወለጋ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር) ትግል ከጀመረ ከ50ዓመታት በላይ የሆነው ቢሆነም ራሱን ቆም
ብሎ ለማየት አልተፈቀደለትም ወይም አዙሮ ማየት ተስኖታል።አንድ አባባል አለ “ የአንድ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ
በሩጫ ውድድር ሁለተኛ የወጣውን ሰው ጠይቅ።” የተባለው የጊዜ ጥቅም ምን ያህል መሆኑን ላማሳየት ነው። ኦንግ
(ወኦነግ ወለጋ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር) ይህን ያህል ዓመታት ታግሎ ያመጣው ለውጥ እንደሌለ እያወቀ ቆም ብሎ ካላሰበ
ከአንድ ምዕተ-ዓመት ( 1000ዓመታት) በኋላም ለድል ይበቃል ብሎ ማሰብ ማሞ ቂሎ መሆን ይመስለኛል። መሐመድ አሊ” አንድ የሃምሳ ዓመት ሰው ዓለምን በሃያ ዓመቱ እንደሚያያት ካያት ሳላሳ ዓመቱን በከንቱ አባክኗል።”
እንዳለው ኦነግ (ወኦነግ) ጊዜውን በከንቱ ማባከኑን መቸ እንደሚረዳው ለራሱም የገባው አይመስለኝም። ጊዜ በረዘመ ቁጥር
የኦሮሞ ማህብረሰብ ሰቆቃን ማራዘም ካልሆነ በቀር ፋይዳ የለውም።ይህ ደግሞ እቆረቆርለታለው ለሚለው የኦሮሞ
ማህበረስብ ደንታ ቢስ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው።እንደ ሻቢያ እና አህዛቡ ወያኔ ህዝብን አታሎ ወደስልጣን መምጣት
ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ኦነግ(ወኦነግ) ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተቀላቅሎ መታገል ወይም አርፎ መቀመጡ የሚያዋጣው
ይመስለኛል።
አህዛቡ ወያኔ፣ኦነግ(ወኦነግ) ፣ ኦብነግ እና እንደ ጁሐር ያሉ የምዕራቡ እና የአረቡ ዓለም ተላላኪዎች በአማራው፣በተቀረው
ኢትዮጵያዊ እና በክርስቲያኑ ላይ የምለኩሱት የጥፋት እሳት የማያቆሙ ከሆነ “ ጨካኝ እና ጨካኝ ሲላተሙ ቆሞ
የሚያይ ርህራሄ ይማራል።ነገርግን ጨካኝ እና አዛኝ ሲጋጩ ግን እንኳንስ ቆሞ የሚያየው አዛኝም ጭካኔ
ይማራል!!!” እንደሚባለው ከአህዛቡ ወያኔ እና ሻቢያ ጋር እየተባበራችሁ በአማራው በክሪስቲያኑና በተቀረው ኢትዮጵያዊ
ላይ የሚታደርሱት ሰቆቃ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቃኔ እንዲማር እና ትግስቱን እንዲሟጠጥ የሚያደርግ እንደሚሆን መገንዘቢያ
ጊዜያችሁ እያለፈ ይመስለኛል። ይህ የጥፋት ሴራችሁ ከጉድጓዷን ርቃ የድምት አፍንጫ እንደምታሸት አይጥ ዓይነት
ሊያደርገችሁ ስለሚችል ዛሬ መስከኛ ጊዜያችሁ ነው። ኢትዮጵያ በህዝብ የተወከለ መንግስት ሲቋቋም እናንተ የምትኖሩበት
ሀገር ማንቁርታችሁን አንቃ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደምያስረክባችሁ ጥርጥር የለኝም።የፖለትካ ዘለቄታዊ ወዳጀነት
አለመኖሩን ወያኔ ሲወድቅ የምታዩት ይሆናል።
“ ከመጽሐፍ በተገኙ ጥቅሶች ሀገርን ከሚመሩ ሰዎች የበለጠ ለአንድ ሀገር አደገኛ ሰው የለም።”
እንደተባለው ደርግ፣ ሻቢያ፣ለገሰ ዜናዊና አቦይ ስብሃት የሚባሉ እና ጥቂት የኦነግ (ወኦነግ) መሪዎች ከመጽሃፍ ባገኙት
ጥቅሶች ሀገር እንመራልን በማለታቸው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰው፣ እየደረሰ ያለው ችጋር እና መከራ እጅግ ዘግናኝ
በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ካለ እናንተን አያድርገኝ።ነገርግን ለህዝብ ደንታ የሌላቸው ይህ ሁሉ ምንም ስለማይመሰላቸው
አሁንም በህዝባችን ላይ ስቆቃ ከመፈጽም አልተቆጠቡም። በአረቦች የሚላኩ እንደጁሃር መሐመድ ያሉ “ ሱማሌ በግ
ገዛች አረብ አለሁ ብላ አላስረባም አለ ነበር እየበላ!!!” ተብሎ የተዜመውን የዘነጋችሁት ይመስለኛል ከትልልቆቻችሁ
ጠይቁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ በሚነሳበት ሰዓት ያ ድል እንደሚደገም ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም።
እኔ ሁል ጊዜ የማይገባኝ የኦነግ(ወኦነግ) ማላዘ ነው። “ ሆድ ዕቃው የተቀደደበት እያለ ልብሱ የተቀደደበት
ያለቅሳል።” እንደሚባለው ከጥንት ጀምሮ ኦሮሞ በአማራው ያደረሰበት በደል የትየሌሌ ሆኖ እያለ የኦሮሞ ቡድኖች
የሚያላዝኑት ነገር ዘወትር አይገባኝም። ኦነግ እና በጎጥ የተደራጁ ቡድኖች የግንጠላ ተልዕኳቸው የሚሳካ የሚመስላቸው
አማራውን ገፍቶ በመጣል ከሆነ እጅግ ተሳስተዋል በኋል ጣጣ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ ቆም ብለው ቢያስቡ
የሚጠቅማቸው ይማስለኛል። በአጠቃላይ በምኒሊክ ጊዜ እንዲህ ሆነ ብሎ ማላዘኑ ምንም ትርጉም የሌላው ተረት ተርት
ነው። ኦሮሞ ሳይወክላቸው የተሰባሰቡ ጥቅት የወለጋ ጠባብ ቤሔሬተኞች ስለዓለም የሚያውቁት ውስን ስለሆነ ወይም
ሂልናቸው በጎጠኝነት የታወረ በመሆኑ እንጂ ዊኒስተን ቸርችል እንዳለው “ በጠቅላላው የዓለም ታሪክ በድብሩ
ሲታይ፤ሀገሮች ጠንካራ ሲሆኑ ሁል ጊዜ ፍታዊ ሆነው አይገኙም።ፍታዊ እንሁን ባሉ ጊዜ ደግሞ ጠንካራ
ሆነው አይገኙም።” ብሎ ተናግሮ ነበር። ለዚህ ማሳያ የቅኝ ግዛት ዘመን የእንግሊዝን ሁኔታ ብቻ ማየት በቂ ይሆን ነበር።
እንግዲህ የዓለም ሁኔታ እንዲህ ሆኖ እያለ እነ አፄ ምኒሊክ፣ እነ አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሃንስ የጀመሩትን የተበታተነን
ህዝብ አንድ የማድረግ ታሪክ ሀጢያት ከሆነ እንደ ሻቢያ፣ወያኔ፣ኦነግ(ወኦነግ) እና ኦብነግ ሀገርና ህዝብን ለመበታተን ማሴር
ምን ሊባል ይሆን? ይገርማል! “ የትምህርት ተቀዳሚ ምዕራፍ አብሮ የመኖር ጥበብ መቅሰሚያ ነው!!!” ሲባል
እንጂ ችላንፎ ያደርጋል ሲባል አልነበረም። ነገርግን በአደንዛዥ ዕፅ እንደደነዘዙ በጎጠኝነት የደነዘዙት የኦነግ መሪ ነን ባዮች
ግን ፊደል በዞረበት ያልዞሩ ይመስላሉ። ቀ.ን.ነ.ኃ. “ መማር በራሱ አዕምሮ አይደለም፤የአዕምሮ መደገፊያ
እንጂ!!!” እንዳሉት በተፈጥሮ የተጣመመ አዕምሮ ያላቸው የሻቢያ፣የትግሬ፣የኦሮሞ አብዛኞቹ ሙሁራን ግን ትምህርት
አዕምሮአቸውን እንዳለወጠው ሥራቸው እየመሰከረ ነው ። ጠማማ የሆነ ሰውን ትምህርት ሊለውጠው እንደማይችል
በጎጠኞቹ ያየነው እውነታ ነው። አርቲስት ዓለምፀሀይ ወዳጆ “ሟችም ገዳይም የሚሸሸግባት ሀገር የኛዋ ሀገር ነች።” ማለቷ እውነት ነው።ምክንያቱ ሻቢያንና አህዛቡን ወያኔ የማይቃወም ከሆነ ኢትዮጵያን የሚያክል የነፍሰ ገዳዮች መሸሸጊያ ሀገር
በጭራሽ አይኖርም። በሐረር በበደኖ እና በሌሎች ቦታዎቻ አማራንና ክርስቲያን የሆነውን ሌላውን ኢትዮጵያዊ እንደከብት
ያረዱ የኦነግ ነፍሰ ገዳዮች ሞት ተፈርዶባቸው በመጀመሪያ ዓመት በመቶ አለቃ ግርማ ፍርሚያ ዕድሜ ልክ እና ከዚያም
በዓመቱ በ፪፲፻፩ ዓ.ም በይቅርታ ተለቀቁ የሚለውን ዜና በወያኔ ቴሌቭዥን ስሰማ ኦነግ እና ወያኔ ስማቸው እንጂ ዓላማቸው
አንድ እንደሆነ በተጨባጭ ያረጋገጥኩበት ነው።እንዲሁም በጋንቤላ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ሰውን የፈጁ እና
ያስፍጁ እንደልብ ተንደላቀው ሲኖሩ ማየት ኢትዮጵያን የነፍሰ ገዳዮች ምርጥ መኖሪያ ቦታ እንድትሆን አድርጓታል።እነ
ጁሓርም አሜሪካ ካልተመቻቸው ኢትዮጵያ መግባት የሚከለክላቸው እንደሌለ ስለሚያውቁ ጅሃድ ያለ ፍርሃትት
አውጀዋል።
ማጠቃለያ
“አንድ ሰው ህይወቱን መስዋዕት ስላደረገ ብቻ የሞተለት ዓላማ የግድ እውነት ነው ማለት
አይደለም።” እንደሚበለው የኦነግ መሪ ነን ባዮች ያልተረዱት ይህን ነው። ይህን ለማረጋገጥ የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ
ታስረው የሚገኙ እስረኞችን ማነጋገር በቂ ማረጋገጫ ነው።እንዴት ተታለው ወደትግል እንደገቡና አሁን ከተለያዩ
አካባቢዎች ከመጡ ኢትዮጵያዊያን ጋር ሲዋሀዱ የተሰማቸውን የጥፋተኝነት ስሜት ማየት በቂ ነው። ሀገረማሪያምና
አካካባቢው በተቀመጥኩባቸው ጥቂት ወራቶች እና ለሠርግ ያቤሎ በቆየሁባቻው ሁለት ሳምንታት ከገበሬው፣ከነጋዴው
ከአስተማሪዎች እና ከተማሪዎች ጋር በተገናኘሁባቸው ጊዜያቶች በጉጂ፣በቦራናና በሌሎች አናሳ ብሔሮች ምንም ድጋፍ
እንደሌላቸው አረጋግጫለሁ።ይህንን ለማረጋገጥ ሀገረማሪያም እና ያቤሎ መሄድ በቂ ነው።
ከነገስታት አንዱ ዘመን እንደምን አለች ብሎ ሲጠይቅ?” ዘመን ማለት አንተ ነህ አንተ ሰላምናዊ ስትሆን
ሰላም ትሆናለች አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች።” ብሎ መለሰለት ይባላል። ሰላማቸውን አጥተው ሰላም
የሚያሳጡን ሻቢያ፣አህዛቡ ወያኔ፣ኦነግ፣ኦብነግ፣ኦብኮ፣ኦፊዴን የመሳሰሉት ጎጠኛ ድርጅቶች እርቅ ይፈልጋሉ ማለት የሞተ
ሰው ይነሳል ብሎ መቃብሩ ቦታ ተቀምጦ መጠበቅ ዓይነት ጅልነት ይመስለኛል።ጎልጉልና አንዳንድ ድኅረ-ገጾች አህዛቡ
ወያኔ እርቅ መፈለጉን የሚሰብኩን ለምን እንደሆነ አልገባ ብሎኛል። ወያኔ እርቅ ቢፈልግ በተሌቭዥኑና ሬዲዮኖቹ ፍንጭ
ይሰጥ ነበር ነገርግን ተጨባጭ ያለሆነ ነገርን በድህረ ገጽ ማውጣት ምን የሚሉት ዜና እንደሆነ አልገባ ብሎኛል። ይህ
የህዝብን ትግል ለማዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፋይዳ የለውም። አህዛቡ ወያኔን ወደ እርቅ ማምጣት የምንችለው
ጉልበታችን ሲፈረጥም ብቻ ነው።አለበለዚያ ሁል ጊዜ በጉልበቱ የሚያስብ እንዴት በጭንቅላቱ ሊያስብ ይችላል?
ኦነግ (የሐረሮች) እና ኦነግ የወለጋዎች በአጠቃላይ አፄ ምኒሊክ እንዲህ አደረጉን እያሉ በሐረር፣ አረባጉጉና የተለያዩ ቦታዎች
እንዲሁም በወለጋ ከደርግ ጀምሮ በአማራው እና በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ያደረሱት ግድያ ቤት ይቁጠረው። እነሱ የዛሬ
መቶ ዓመት የሆነውንም ያለሆነውንም አሳብጠው ይናገራሉ።ታዲያ እናንተ በቅርብ የፈጸማችሁት እና እየፈጽማችሁ
ያላችሁት ምንድን ነው ሲባሉ እንደለመዱት ብቀላ ነው ይሉናል። መጽሐፍ ቅዱስ “ በሌላ የነቀፍከውን አንተ
ከሰራኸው ራስህን መንቀፍ አይደለምን።” ይላል። የኦነግ ሥራ በተጨባጭ የሚነግረን እራሱን በግልጽ እየነቀፈ
እንደሆነ ነው። በጠቅላላው በኢሳት እና እሱን በመሰሉ ቡድኖች ፕሮፓጋንዳ እውነት ልትለወጥ አትችልም።አባ ጃራን ጀግና
ያደረገው ኢሳት እንዴት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ይሆናል?ተቃዋሚ መስለው የነጻነት ትግላችንን የሚያደናቅፉ ቡድኖችን
ስንነቅፍ ዋናው ጠላት ወያኔ እያለ ለምን ተቃዋሚዎችን ትተናኮላላችሁ ይሉናል አበበ ገላውም ይህን ጥያቄ በፌስቡኩ ላይ
ለማቅረብ መሞከሩ አልገባ ብሎኛል። እሱ ከግፈኛው ግንቦት7 ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ኢትዮጵያን እወዳለሁ ማለት ከማላገጥ
የዘለለ እንዳልሆነ የገዛ ልቦናው ይፈርድበታል። ግንቦት7፣ኢሳትና አበበ ገላውን የምመክራችሁ የጠላት ትንሽ እና ትልቅ
የለውም ነው።እንዲህ ለምትሉት “ ጠላት እማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መግደል
አሾክሻኪውን ነው።”የሚለው የጥንቱ ቅራርቶ መስማት መልስ የሚሆናችሁ ይመስለኛል።ኤርትራ ውስጥ የመሸገ ሁሉ
የሻቢያ አሽከር እና ተላላኪ ነው። ሻቢያ ደግሞ የኢትዮጵያ ጠላት ነው። ለእኔ ኦነግ፣ኦህዴድ፣ኦብኮ፣ኦፊዲን በወለጋ እና አምቦ ጠባብ ጎጠኞች የተቋቋሙ በመሆናቸው ልዩነታቸው የስም እንጂ ሌላ ምንም አይደለም።ስለዚህ ከኢትዮጵያ ህዝብ
ጋር በኢትዮጵያዊነት ከለላ ሆነው ያማይታገሉ ከሆነ የነሱ ተቃዋሚነት ምኑ ላይ ነው?
ኦነግና ኦብነግ ታሪክ ለማጥፋት ለምን ይሯሯጣሉ?
ታሪክን በታሪክነቱ መቀበል እንጂ ሌላ ታሪክ በመፍጠር የህዝብን ጥያቄ የሚመልሱ መስለው መታየት ምንም ፋይዳ
የለውም!!! ለምሳሌ – ፩ኛ= ምንም ታሪክ የሌለውን አርማ አሰፍተው ባንዲራ ነው ተቀበሉን ማለት ምን ማለት ነው? ይህ
ሀገርንና ታሪክን አሳንሶ የማየት ከዝቅተኝነት የመነጨ በሽታ እንጂ ምንም መንሻ ታሪክ የሌለውን ነው። አርማን ባንዲራ
ማድረግ ሱስ እንጂ መቸውንም ተቀባይነት የሌለው ነው። ለምሳሌ ኦነግ እና አኦብነግ ባንዲራችን የሚሉት ሻቢያና አህዛቡ
ወያኔ ወንድሞቻቸውን ሲገድሉ የሚፎክሩበት የነበር በደም የተጨማለቀ አርማ እንጂ ምንም ታሪክ የሌለው ሲሆን ኦነግና
ኦብነግም የነሱን ፈለግ በመከተል ባንዲራችን የሚሏት አማራውን እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ወገናቸውን ያረዱበት
ማስታወሻቸው ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ታሪክ የሌለው ጨርቅ ነው።ይህንንም በደም የጨቀየ አርማቸውን በጭራሽ
መቼም መቼም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይቀበለው ያውቃሉ። ይህ ደግሞ ለትዝብት እና ለጥላቻ ይዳርጋቸዋል እንጂ
ምንም ተቀባይነት ሊኖሮው አይችልም። ይህን ለማረጋገጥ በተለያዩ ክብረ በዓላት፣በሰርግ እና በውድድሮች የኢትዮጵያ
ህዝብ የሚይዘው ባንዲራ የኢትዮጵያን ባንዲራ እንጂ ሌላ እንዳለሆነ ልቦናችሁ ያውቀዋል።ስለዚህም ነው አህዛቡ ወያኔ
ስለባንዲራ ደንብ ለማውጣት የተገደደው። “ደሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ምን ይውጠው ነበር።” እንደሚባለው ኦነግና
ኦብነግ በቅዥት ባይኖሮ ኖሮ ምን ይውጣቸው ነበር። ተከታዮቻቸው በጣም እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ አርማቸውን
ባንዲራ በማለት ስለሰቀሉ ሀገር እየመሩ እየመሰላቸው በቅዥት ዓለም መኖርን ስራየ ብለው በመያዛቸው ከቅዥታቸው ሲነቁ
ራሳቸውን እንደሚያስደነብራቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።የኢትዮጵያን ባንዲራ በተመለከተ የግንቦት7 ሊ/መ ዶ/ር ብርሃኑ
በተገኘበት ከኦነግ ጋር ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት አርማና ባንዲራን እኩል አድርገው ኦነጎች የኢትዮጵያ ባንዲራ ከተሰቀለ
የኛም ይሰቀል በሚለው ባለመግባባታቸው የነፍሰ ገዳዮች አርማም ሆነ የተከበረችው የኢትዮጵያ ባንዲራ ሳትውለብለብ
ስብሰባው እንዲቀጥል ተደርጓል። ለኢትዮጵያን ሕዝብ ይህ የሞት ሞት ከመሆኑም በላይ ህዝብን እጅግ ማሳነስ፣ መናቅና
ሀገርን ማዋረድ እንደሆነ ሳይረዱት ቀርተው አይደለም። የኮሪያ ዘማቾች ከመቃብር ለአንዲት ደቂቃ መነሳት የሚችሉ ቢሆን
ምን ያህል ልባቸው ይሰበር ነበር። ባንዲራችን ዝቅ ብላ ከምትውለበለብ ሂይወታችን ብትጠፋ ይሻላል በማለት ስንቶቹ
ውድ ሂይወታቸውን ለባንዲራቸውና ለሀገራቸው እንደሰዉ በታሪክ የምናውቀውና ታሪካቸውም በወርቃማ መዝገብ ሰፍሮ
መቀመጡን የምናውቀው ነው። ጎበዝ ባንዲራችን ከአንድ በወገን ደም ከጨቀዬ ጨርቅ ጋር የሚያወዳድሩ ጉዶች እኛ
ኢትዮጵያዊያን ምን ያህል እንደተናቅንና እንደዘቀጥን እየታዘባችሁ ነው?ከዚህ በላይ ሞት በጭራሽ ሊኖር አይችልም።
ባንዲራ ማለት ሀገር ማለት ነው።ባንዲራን እያዋረዱ እንታገላለን ማለት ምን ማለት ነው? ታማኝም በየነም በአንድ የኦነግ
ስብሰባ ከዚች ባንዲራ ፊት ለፊት እቀመጣለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም ማለቱ ምን ማለቱ ነው? ይህ ሰው ኢትዮጵያዊ ነኝ
ብሎ የመናገር የሞራለ ብቃቱ ይኖረዋል? ሀገሩን እንደሚወድ ዜጋ እንባውን እየረጨ ስለኢትዮጵያ ሲናገር በአንድ ስብሰባ
የተቀረጸ ቪዲዮ ላይ ተመልክቸዋለሁ። ይህ ሰው እዚህ ስብሰባ ላይ ከሚያለቅስ ይልቅ ኦነጎች ኢትዮጵያዊያኑን፣ አማራውንና
ክርስቲያኑን በበደኖና በሌሎች ስፍራዎች ሲያርዱ ያንጠለጠሉትን አርማ ባንዲራ ነው በማለቱ ቤተክርስቲያን ሄዶ ንሳውን
ለእግዚአብሔር እያለቀሰ ቢነግረው ኖሮ ነፍሱ ምንኛ ባረፈች ነበር።አሁንም እግዚአብሔር ንሰሃን የሚወድ አምላክ በመሆኑ
ንሰሃ እንዲገባ የወንድምነቱን እምክረዋለሁ።የታማኝ ይህ ብቻ አይደለም የእስላም ጎራዴ ይሻለኛል ባለውም ንሰሃ ቢገባ ያ
የጥንቱ ሀገር ፍቅሩ ተመልሶ በልቡ ይሰርጽበት ነበር።ነገርግን በዚያው አስነዋሪ ተግባሩ መዝለቁ ኢትዮጵያ ወንድ ልጅ
አይውጣልሽ ተብላ ተረግማለች የሚለው እርግማን በትክክል እየተፈጸመ እንደሆነ በትክክል እያየነው ነው።
፪ኛ= በታሪክ አጋጣሚና በቅኝ ግዛት ዘመን ለተለያዩ ቦታዎች፣ሰፈሮች እና መንገዶች የተለያየ ስም ቢሰጥም እስከአሁን ያንኑ
ስም ይዘው ያሉ አያሌ ናቸው። ለምሳሌ በኛ ሀገር እና በአፍሪቃ የተስጡ ስሞች መርካቶ፣ፒያሳ፣ዊንጌት እና ሌሎች።በደቡብ
አፍሪካ ጀዋንስበርግ፣ኬፕ ታወን እና የመሳሰሉት።እንዲሁም በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገሮች እና በሌሎች ዓለማትም እንዲሁ።ይህ
ታሪክ ስለሆነ በታሪክነቱ እንዳለ ሳይለወጥ ተቀምጧል።ነገርግን በአሁኑ ጊዜ በኛይቱ ሀገር ግን የተለየ ነው። በሻቢያና በወያኔ
ገፋፊነትና አስፈጻሚነት የኦሮሞ ክልል ተብሎ በወያኔ በተከለለው ቦታ ለምሳሌ ናዝሬት፣ደብረዘይት፣ዓለማይ፣ኢልባቦር፣
አዲስ አበባ፣አሥመራ መንገድ(ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል መሆኗን ለማጥፋት) እና ሌሎችን ቦታዎች የስም ለውጥ መደረጉ
የቅርብ ጊዜ አሳፋሪ ታሪክ ነው። ይህ ሁኔታ ምንም መሰረት የሌለውና ዘለቄታ የማይኖረው ቢሆንም ለጊዜው በሻቢያ፣
በአህዛቡ ወያኔ፣ኦነግና ሌሎቹ ኢትዮጵያን የመበታተን እና ታሪኳን የማጥፋት የባእድ ተልኮ ያነገቡ ህሊና ቢሶች ተቀባይነትን ያገኘ ቢመስልም ወደፊት ግን በጭራሽ በየኢትዮጵያ ሕዝብ ተቀባይነት እንደማይኖረው ጠንሳሾችምና አስፈጻሚዎች እንዲሁ
ተላላኪዎቻቸው ጠንቅቀው የሚያውቁት ሀቅ ነው።ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪኩ ላይ ቀልድ እንደማያውቅ
ያውቁታልና።አሁንም በጠላት እጅ ከወርች በመያዙ እንጂ እንዳልተቀበለው ከማንም የተሰውረ አይደለም።
መጽሃፍ ቅዱስም መዝ ፸፫ ፬ “የማያውቁትን ምልክት ምልክታቸው አደረጉ ይላል።” ደርግ
ባንዲራ መቀየር አስተማረ ሌላው ሁሉ ባንዲራ መቀየር ቀልድ አደረገው።”የአንበሳ ምልክት
ያለበት ባንዲራችንን ማስመለስ የኮሪያ ጀግኖቻችንን ማክበር እና ማስታወስ ነው!!!”
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ሊያውቀውና ቆርጦ ሊታገለው የሚገባ የደርግ ሥርዓት ሲወድቅ ምርኮኛ የነበሩ
ውድና ብርቅ የነበሩ የኢትዮጵያን ወታደሮች በግፍ የጨፈጨፈና በአሁኑም ጊዜ በዚያ አረመኔ ተግባሩ በመቀጠል እነ
ኮሌኔል በዛብህን፣ኮሌኔል ታደሰን እና ሌሎችን ጀግናና ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያንን ከበላና ከሰወረ እንደ ሻቢያ ከመሰለ አውሬ
ጋር አብሮ የሚሰራ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም። እኝህን የመሰሉ ባንዳዎች
ለታሪክ ፍርድ እንደሚቀርቡ ፍጹም ጥርጥር የለኝም። ውድ ኢትዮጵያን እኝህን ጀግኖች በምንጽፈው ጽሁፍ ሁሉ
እድናስታውሳቸው አደራ እላለሁ። የኛ ተጽዕኖ ካለ ሻቢያ ወደፊት የሚመጣውን ጣጣ ስለሚረዳ የተሰወሩትን በግዱ
ሊፈታቸው ይችላል።
የአዲስ አበባ መካነአዕምሮ ተማሪዎች ያው ዕድሜ ነውና ዕድሜ ይሰጠ ለዕድሜ
ብለው እንደዘመሩት ዕድሜ ይስጠን ሁሉንም እናየዋለን።
አንተነህ ጌትነት ሙላቱ (የሶማው ከባዳ ሀገር አውስትራሊያ)Email: yqobadishegala@gamil.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 18, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 18, 2014 @ 9:04 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar