www.maledatimes.com ከረቀቀና ከተቀነባበረ ዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት እንዴት ነፃነታችንን እንጎናፀፍ !!!? (ገረመው አራጋው ክፍሌ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

ከረቀቀና ከተቀነባበረ ዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት እንዴት ነፃነታችንን እንጎናፀፍ !!!? (ገረመው አራጋው ክፍሌ)

By   /   February 18, 2014  /   Comments Off on ከረቀቀና ከተቀነባበረ ዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት እንዴት ነፃነታችንን እንጎናፀፍ !!!? (ገረመው አራጋው ክፍሌ)

    Print       Email
0 0
Read Time:29 Minute, 35 Second

ገረመው አራጋው ክፍሌ – ከኖርዌ   ወያኔ ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ በሕዝብ ላይ ያደረሱትና አሁንም እያደረሱት ያለውን መከራ፤ የማስተዋል ሕሊና ላለው ሰው የተሰወረ ድርጊት አይደለም። እንደዚህ ያለው የሕዝብ መከራና ጦርነት፤ ፍትሕ ማጣትና አድለዎ፤ስደትና ሞት፤መደፈርና መዋረድ፤የማንነት ማጣት፤የራስ ፍለጋና ጎሰኝነትና የጽንፈኛ ሃይማኖት አክራሪነት…፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲከሰት ያጠነጠኑት ሴራ እነማን እንደሆኑና የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገቡ የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም የተሰማሩ የባእዳን ሃይሎች ታማኝ ቅጥረኞች ናቸው፡፡ለዚህ የጥፋት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያም ባእዳን ሃይሎች ለወያኔዎች እንደ ስራ ማስኬጃ በኢትዮጵያ ጭቁንና ድሃ ህዝብ ስም በእርዳታና በብድር እየሰጡ የጥፋታቸውን ደመዎዝ ወይንም ምንዳ ይሰጧቸዋል፡፡ወያኔዎችም በዚህ የግፍ ገንዘብ የራሳቸውን ትልቅ የኢኮኖሚ ኢምፓየር መስርተዋል፡፡ ታዲያ ይህንን የጥፋትና የግፍ ገንዘብ ከባእዳን ሃይሎች ተቀብሎ ዝም ማለት አይቻልምና ይህንን የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም ከሁሉ በፊት ቅድሚያ የግድ ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ማጥቃት ማዳከምና ከቻሉ ደግሞ ማጥፋት አለባቸው፡፡ብዙ ልብ ያልገዙ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞችና ምሁራን እርዳታና ብድር በወያኔ እየተዘረፈ ወደ ውጪ ወጣ ይላሉ ነገር ግን ባእዳን ሃይሎች ለምን አስቀድሞ እርዳታና ብድር በገፍ ለወያኔው መንግስት ወይንም ለእኛ ኢትዮጵያውን ይሰጣሉ የሚል ወሳኝ መሰረታዊ ጥያቄ አያቀርቡም፡፡እውን ባእዳን ሃይሎች ወያኔ በብድርና በእርዳታ የሚመጣውን ዶላር እየዘረፈ ውጪ እንደሚያሸሽ እንደዚሁም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ የሚሊታሪ የደህንነት የሚዲያ  ወዘተ በአንድ የትግሪኛ ዘር ተናጋሪ በሞኖፖል ጠቅልሎ እንደሚቆጣጠር ጠፍቷቸው ነውን?ፈፅሞ !!! ባእዳን ሃይሎች ይህንን ጠንቅቀው ያውቃሉ እንደዚሁም ወያኔም ቢሆን ባእዳን ሃይሎች ይህንን እንደሚያውቁና በርታ ግፋበት ከማለት ውጪ ምንም እንደማያደርጉት እራሱም ያውቀዋል፡፡

በአጭሩ በመካከላቸው ከፍተኛ የሆነ የእከክልኝ ልከክልህ የጥቅምና የአላማ ትስስር እንዳለ ማወቅ አለብን፡፡ስለዚህም ዲያስፖራዊ ኢትዮጵያውያን በየአደባባዩ የሚጮሁት እንዲያው ለማሳወቅ ያክል ካልሆነ በስተቀር ዋሽንግተን ውስጥ ወይንም ለንድን ወይንም አውሮፓ ውሰጥ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ምእራባውያን ወያኔን ከአንጀታቸው በቆራጥነት ይህንን ነገር ተው ይላሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ወያኔም ይህንን እንደማያደርጉ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡እንዲያው በሀገራችን አባባል እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው አይነት አልን ለማለት ያክል ካልሆነ በስተቀር ምእራባውያን የአዞ እንባ ከማንባት ውጪ ለእኛ ምንም የሚፈይዱት ነገር የለም፡፡ምእራባውያን ሃይሎች በጓሮ በር ወያኔን እንዲህ አድርግ ይህንን እናደርግልሃለን እያሉ ያስወቅጡናል ያስረግጡናል የዘርፉናል በሳሎን በር በፊት ለፊት ደግሞ ወያኔን የፕሬስ ነፃነትና ሰብዓዊ መብት የሚገፍ አምባገነን እያሉ የውሸት እንባ ለእኛ ያነቡልናል እኛም በዚህ ልብ እንዳልገዛ ህፃን ልጅ ለጊዜው ደስ ይለናል፡፡ምእራባውያን በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ከፍተኛ ቁማር እየተጫወቱብን እንደሆነ መቼ ልብ እንደምንገዛና እንደሚገባን ግን አላውቅም፡፡በተለይም በምእራቡ አለም ውስጥ ያለው ዲያስፖራ ይህ በቅጡ የገባው አይመስልም ወይንም እያወቀው የእንጀራ ጉዳይ ሆኖበት ብቻ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ አይነት እራሱንም ሆነ ሌላውን በከንቱ እያታለለ ነው፡፡

ዛሬ ህዝባችን ተፈናቀለ መሬት ለባእዳን ተቸበቸበ ወዘተ አይነት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ አይነት ከንቱ ድካም ዋጋ የለውም፡፡ምክንያቱም ወያኔ ጥንተንም ደደቢት በረሃ የገባው ነፃነት ዲሞክራሲና ዳቦ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታግሎ ሊሰጥ ሳይሆን በተቃራኒው በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገበ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ በቅጥረኝነት ለማስፈፀም ከዚያም ቀጥሎ እግረ መንገዱንም እንደ ኢፈርት አይነቱን የኢኮኖሚ ኢምፓየር መስርቶ የራሱን ጠባብ ፍላጎት ለማስፈፀም አስቦ ነው፡፡ስለዚህም ዛሬ ለምእራባውያን ህዝባችን ከመሬቱ እየተፈናቀለና ንብረቱ እየተቀማ በመኪና ላይ እየተጫነ ገደልና ወንዝ ውስጥ እንዲገባና እንዲያልቅ እየተደረገ በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ወይንም የዘር ማፅዳት ተፈፀመበት ብሎ የቁራ ጩኸት ማሰማት ለቀባሪው አረዱት አይነት የታሪክ ምፀት ነው የሚሆነው፡፡ወያኔ ሶማሊያ ገብቶ በማይመለከተው የውክልና ጦርነት የሚዋጋው እኮ ቅጥረኛ ስለሆነ ነው፡፡አንድ የአሜሪካ ወይንም የእንግሊዝ ወታደር ለምን ይጎዳል፡፡ስለዚህም ወያኔ ዶላር እየተሰጠው ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት እያለ አንድ ጊዜ ሶማሊያ አንደ ጊዜ ሱዳን-ዳርፎር አንድ ጊዜ ሩዋንዳ ወዘተ ግባ ሲባል ወታደር እያሰማራ እሺ የሚለው የባእዳን ቅጥረኛ ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህም ባእዳን ሃይሎች ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገበ የግሎባል ካፒታሊዝምን ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም የግድ ይህንን ቆሻሻ ስራ እራሳቸው መስራት አይጠበቅባቸውም ወይንም ይህንን እራሳቸው ለማድረግ አይፈልጉም፡፡

የመለስ ራእይ ወይንም ሌጋሲ ይቀጥላል ሲባል ደግሞ ቅኔው ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ እንዳለፉት 22 ዓመታት ወደፊትም ይቀጥላል ማለት ነው፡፡አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር የለም ይህ ሽፋን ነው ያለው ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገበ ፕሮጀክት ትግበራ ነው፡፡ለአብነት አሁን ወያኔ በአማራው ላይ እየፈፀመ ያለው ሰይጣናዊ ስራ ወደፊት የትግሪኛ ተናጋሪውንና አማራውን ፈፅሞ የማይፈታ ትውልድ ተሻጋሪ ቅራኔ ጥላቻና ቂም በቀል ውስጥ በመክተት ይህንን እንደ ምክንያት በማስቀመጥ ወደፊት ትግራይን እንደ ኤርትራ ለመገንጠል ያለመ እኩይ ሴራ ነው፡፡ይህ ደግሞ ለብዙ ዘመናትና በተለይ ደግሞ አሁንም በተጠናከረ መንገድ በታዳጊው አለም ውስጥ በረቀቀና በተቀነባበረ እየተተገበረ ያለ የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ነው፡፡በዪጎዝላቭያ በሶማሊያ በሱዳን በኢራቅ በሊቢያ በሶርያ በናይጄሪያ ወዘተ ዘርን ሃይማኖት ማእከል ያደረጉትና የተፈፀሙት የውስጥ የእርስ በርስ ግጭቶችና ጦርነቶች ሁሉ ተገቢው አስተዋይ ጥንቃቄ ካልተወሰደባቸው የኋላ ኋላ ወደ ማይፈታ ቅራኔ መለያየትና መበታተን ያመሩ ወይንም የሚያመሩ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ስለዚህም ወያኔም ሆነ ባእዳን ሃይሎች በአማራው በጋምቤላው በኦጋዴኑ ወዘተ የሚደረገው ኢ-ሰብዓዊ ሽፍጨፋ ማፈናቀል ወዘተ የኋላ ኋላ ወደ ማይፈታ ቅራኔ መለያየትና መበታተን የሚያመራ እንደሆነ ቀድሞውኑ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ነገር ግን ይህ እንዲሆን በብርቱ ይፈልጋሉ ምክንያቱም ወያኔም ሆነ ባእዳን ሃይሎች ተግባራዊ እያደረጉት ያሉት ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገበ ፕሮጀክት ነውና፡፡

ግሎባል ካፒታሊዝም በራሱ ከፍተኛ የሆነ ታሪካዊ ውስጣዊ ቀውስ ውስጥ ነው እየተዘፈቀ ያለው ስለዚህም ይህንን ቀውስ ለማብረድ ወይንም ለማድረግ ደግሞ የግድ ከጥቂት ሀብታም ካፒታሊስት ልሂቃን ውጪ ያለው መላው አለም በተለይም 3ኛው የታዳጊ አለም ህዝብ  በዘር በሃይማኖት በፆታ ወዘተ አርተፊሻል ልዩነትና ችግር እየተፈጠረለት አጠቃላይ አለመረጋጋትና ቀውስ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ስለዚህም አንድ ሺህ አንድ የሆኑ ብዙ የበሽታውን ምልክቶች ማውራት ቢቻልም ቅሉ ግን ዋናው የበሽታው መንስኤ በራሱ ግሎባል ካፒታሊዝምና እያራመደው ያለው አለም አቀፍ የኒዎ-ሊበራል እና የኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ነው፡፡ስለዚህም አማራ ወይንም ጋምቤላው ወይንም ሌላው ዘር ተፈናቀለ የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ተፈፀመበት ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና ማሳወቁ ዝም ከማለት በራሱ ጥሩ ቢሆንም ቅሉ ግን ለቀባሪው አረዱት አይነት ነው፡፡ምእራባውያን በራሳቸው የውስጥ ስራ-አጥ ዜጋና ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የተጠመዱ ስለሆነ ለእንደዚህ አይነት ጩኸትና አቤቱታ ብዙም ቦታና ጊዜ የላቸውም፡፡ምእራባዊያን ከኢትዮጵያ ጉዳይ ይልቅ ይብልጡኑ የሶሪያ ወይንም የኢራን ወይንም የኮርያ ጉዳይ ነው የሚያስጨንቃቸው፡፡ምክንያቱም የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚተማመኑበት ታማኝ ቅጥረኛቸው የሆነው ወያኔ የያዘው ጉዳይ እንደሆነ ነው የሚረዱት፡፡ምክንያቱም ወያኔ ማንኛውንም ቆሻሻ ስራ ለመስራትና ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለመበታተን የሚያስፈልገው ነገር ዶላር ማላስ ብቻ እንደሆነ ባእዳን ሃይሎች ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡የግራዚያኒን የመታሰቢያ ፓርክ በሰለማዊ ሰልፍ የተቃወሙትን ኢትዮጵያውያን የሚያስር የለየለት የክፍለ-ዘመናችን ነውረኛ እኩይ ሃይል ለታማኝ ቅጥረኛነቱ እንዴት አመኔታ አይጣልበትም፡፡ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያ ዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት ውስጥ ነው ያለቸው፡፡

ዛሬ ወያኔም በኢትዮጵያችን ውስጥ እያደረገ ያለው በተወሰነ መንገድ የምእራቡን አለም በተለይም የአሜሪካን እና የእንግሊዝን የግሎባል ካፒታሊዝም ሞዴል ተከትሎ ነው፡፡በዚህ የተነሳም ወያኔ በመከላከያ በቴሌ በአየር መንገድ በመብራት ሃይል በንግድ ባንክ ወዘተ አሁን እያደረገ ያለው ነገር ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ድርጅትነት ከማዞር ይልቅ በመንገስት ይዞታነት እንዳሉ በማቆየት እነዚህን ድርጅቶች እንደ ኢፈርት ካሉት የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ጋር በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ በማስተሳሰር እነዚህን የመንግስት ድርጅቶች እንደ ላም ማለብና መዝረፍ ነው የተያያዘው፡፡ለምሳሌ አንዱ ግልፅ ሙስና እነዚህ የመንግስት የንግድ ድርጅቶች ያለ ተገቢ ግልፅ ጫረታ ማንኛውንም ኮንትራት ቅድሚያ ለኢፈርትና ተያያዥ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች በውድ ዋጋ በኮንትራት መስጠት ነው፡፡ይህም ብቻም አይደለም እነዚህ የንግድ ድርጅቶችና ሌሎችም የመንግስት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቅድሚያ የወያኔዎችን ፎቆች በውድ ዋጋ እንዲከራዩ ይደረጋሉ፡፡የመለስን ሞት ተከትሎ ህዝብን ለከፍተኛ አላስፈላጊ ወጪ የዳረገውና የሚታየው አይነት የመለስን ሞት አስታኮ የተሰራው ቢዝነስ ሁሉ በዚህ ቅኝት ውስጥ ያለ ነው፡፡ስለዚህም ወያኔ የፖለቲካ የሚሊታሪ የደህነት የኢኮኖሚ የቴክኖክራቲክ ቢሮክራሲ የአካዳሚ የሚዲያ የኢንተርቴይንመነት ኢንደሰትሪውንና መዋቅሩን በሞኖፖል እስከተቆጣጠረ ድረስ ዛሬ የመንግስትም ሆነ የግሉ ዘርፍ የሚባለው ኢኮኖሚው ሁሉ በጠቅላላው የወያኔ ንብረት ነው፡፡ወያኔም የፖለቲካ ስልጣንን የሞት የሽረት ትግል አድርጎ የተያያዘው ዋናው አንዱ ምክንያት ከኢኮኖሚው ጋር በተያያዘ ነው፡፡ስለዚህም የተዘረጋውን የኢኮኖሚ ስርዓቱን በጥልቀትና በስፋት ሳንመረመር ዝም ብለን ወያኔ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚጠቀምበትን የውሸት የምረጫ ዲሞክራሲ እና ለሽፋን የሚያወራውን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማሳሳቻ ብቻ በማየት ስለወያኔ ስርዓት ድብቅ እውነተኛ ምንነት መናገር አንችልም፡፡የወያኔ የቢዝነስ አጋር የሆኑት ሀብታም ልሂቃን በኢንቨስትመንት ሽፋን በማንኪያ እየሰጡ በአካፋ ዘላቂና ትውልድ ተሻጋሪ ችግርን የሚሰጡንና ኢኮኖሚያችንንም እንደፈለጋቸው የሚዘርፉትም ወያኔ ፈፅሞ የለየለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን የጥፋት ተልእኮ ያነገበ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም የተሰማሩ የባእዳን ሃይሎች ታማኝ ቅጥረኞች ስለሆኑ ነው፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ ለጥቂቶች የምድር ገነት ለብዙሃኑ ህዝብ ደግሞ የምድር ገሃነም የሆነችበት እንቆቅልሽም ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ብዙ ኢትዮጰያውያን ምሁራንና ፖለቲከኞች ዲሞክራሲ ሰብዓዊ መብት ነፃ-ፕሬስ ገለመሌ እያሉ ይጮሃሉ ነገር ግን እየተከተልነው ያለነው አለም አቀፍ ስርዓት እና በተያያዥነትም ያለው የኢኮኖሚ ስርዓት ምን እንደሆነ ወይንም ምን መሆን እንዳለበት በግልፅ ማስቀመጥ አልቻሉም፡፡በዚህ የተነሳም በአንድ በኩል ወያኔ የሚከተለው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው ይሉንና በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ከበስተጀርባ የፈጠረውን ኢፍርት የተባለ ትልቅ የኢኮኖሚ ኢምፓየር እንዴት ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋር እንደሚያስማሙት ለመረዳት ግራ የሚገባ ነው የሆነው፡፡ዛሬ በኢትዮጵያችን ብዙሃኑ ህዝብ እኮ ዲሞክራሲን ብቻ አይደለም ያጣው ከዚያም በላይም ከእለት ወደ እለት ወደከፋ ድህነት ውስጥ በመገፋቱ ዳቦ በቅጡ ለመብላትም ጭምር አልቻለም፡፡ከሁለቱም ደግሞ የከፋው በታሪክ ከምንጊዜውም በባሰ ሁኔታ ለምን የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊና ዜግነታዊ ባርነትና ውርደት ውስጥ ገባ?የሚለው ሲታሰብ ነው፡፡ይህንን ስናስብ ዛሬ ኢትዮጵያችን በወያኔ የባእዳን ቅጥረኛነት አማካኝነት አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት ውስጥ ነው ያለቸው፡፡ስለዚህም አጀንዳው መሆን ያለበት ነፃ-ፕሬስ አምባገነን ዲሞክራሲ ሰብዓዊ-መብት ወይንም ሰለማዊ ትግል ገለመሌ አይደለም፡፡ቅድሚያ አጀንዳው መሆን ያለበት ወያኔ ላለፉት 40 ዓመታት ያህል በባእዳን ቅጥረኝነት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ተግባራዊ እያደረጉብን ካሉት የዘመናዊ የውክልና ቅኝ-ግዛት እንዴት ነፃነታችንን እንጎናፀፍ እንደዚሁም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትንም እንዴት ከጥፋት እንታደግ የሚለው ነው መሆን ያለበት፡፡ይህንን ለማድረግ ደግሞ የምንችለው የግሎባል ካፒታሊዝምን ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በጥልቀትና በስፋት በጥሞና ለመረዳት ስንችል ነው፡፡ምክንያቱም መፍትሄና መድሃኒት የሚገኘው በስተመጨረሻ በዋናነት የበሽታውን ዋና መንስኤ በመረዳትና በመለየት እንጂ የበሽታውን አንድ ሺህ አንድ ምልክቶች ዝም ብሎ በማውራት ብቻ አይደለም፡፡

ኢትዮጲያና ኢትዬጲያዊነት ለዘላለም ይኖራል። ወያኔ ግን በተባበረ የኢትዮጲያዊያን ጠንካራ ክንድ ይወገዳል!!

g.araghaw@gmail.com

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 18, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 18, 2014 @ 6:30 pm
  • Filed Under: AFRICA

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar