www.maledatimes.com ሃይለመንድህን አበራ ማን ነው ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሃይለመንድህን አበራ ማን ነው ?

By   /   February 18, 2014  /   Comments Off on ሃይለመንድህን አበራ ማን ነው ?

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 9 Second

ሃይለመድህን አበራ እና በተሰቦቹ
“አየርመንገዱ ሰራተኞቹን በብቃት ሳይሆን በዘር ግንድ የሚለካ ነው።”

አይሮፕላኑን በመጥለፍ ጀነቭ ያስረፈው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ በባህርዳር ቤተሰቦቹ ወላጆቹ በጣም ሃብታም ከሚባሉት የመጀመርያ ተርታ ናቸዉ ᎓᎓ በቁጥር በዛ የሚሉት ወንድም እና እህቶቹ በሙሉ የመጀመርያ ድግሪ አላቸዉ 2 የህክምዳ ዶክተሮች እሱን ጨምሮ 3 እንጅነሮች እና ሌላም አንድ ወንድሙ እንዲሁ አየርመንገድ ግራዉንድ ቴክኒሻን ነዉ ታላቅ ወ ንድሙ NASA እንደሚሰራ ይነገራል። 

የሚገርመዉ እዉቀታቸዉ በሁሉም ነክ ስለሆነ በቅርብ የእምናዉቃቸዉ ካልሆን በስተቀር አብዛኛዉ የባሃርዳር ነዋሪ የተለያየ የራሱን ምክንያት ይሰጡታል ለእኔ ግን 3 ወንድማማች እንጅነሮች የተለየ ተአምር የሚሰሩ የእመወዳቸዉ ናቸዉ ᎓᎓ሀይለመድን እግዛብሔር ካንተ ጋር ይሁን ይሔን ከባድ ውሳኔ የወሰንህዉ ፍትህ አጥተህ፣ በብቃት ሳይሆን በዘር ግንድ ሰዉ ከሚለካበት ቦታ ድንገት እራስን አግኝተህዉ ነዉ᎓᎓ይህ ስራህ ምን ላርግ እንጀራየ ነዉ እያሉ በሆዳቸዉ ለሚገዙ ትምህርት ነዉ᎓᎓

ሃይለመድህን አበራ ሃይስኩል የጨረሰው ጣና ሃይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት ነው ። ማትሪክ “ስትሬት A” አምጥቶ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ኢንጅነሪንግ ፋኩልቲ የአምስተኛ አመት የአርክቴክቸር ኢንጅነሪንግ ተማሪ እያለ ነው ለአብራሪነት ተወዳድሮ ያለፈው እና ፖይለት የሆነው ። ሲበዛ የተረጋጋ እና ብሩህ አእምሮ ያለው ልጅ ነው ።

የጋሽ አበራ ተገኝ ልጆች እና ስኬታቸው: –
1 እንዳላማው አበራ የህክምና ዶ/ር
2 መድሃኒት አበራ የህክምና ደ/ር
3 ተክለ መድህን አበራ ኮምፒተር ኢ/ር
4 ብርሃነ መድህን አበራ ኮምፒተር ኢ/ር
5 ሃይማኖት አበራ በጀርመን ሀገር የዩንቨርስቲ መምህር (ፒኤች ዲ አላት)
6 ዜናሽ አበራ በአሜሪካ ሐገር የዩንቨርስቲ መምህር (ፒኤችዲ)
7 ንዋይ አበራ (ይመስለኛል በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የሴት ዶ/ር በፊዚክስ)
8 ሂዎት አበራ በኮምፒተር ሳይንስ የድግሪ ምሩቅ

ሃይለመድህን አበራ ከምን አይነት ቤተሰብ እንደወጣ በቀላሉ መገመት ይቻላል ። ድፍን ጎንደር እና ጎጃም በጋሽ አበራ ተገኝ ስኬት ሁሌም እንደተደመመ ነው። ልጆቻቸው ለብዙዎቻችን የትምህርት ተምሳሌቶቻችን ናቸው ።

ሃይለመድህን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ያለው ዘረኝነት በአማሮች እና በኦሮሞች ላይ የሚደርሰው ግፍ በጣም ያስቆጨው ነበር። የፈለቀበት የአማራ ብሄር… እንግልት ሁሌም እንዳንገበገበው ነው።

ሃይለመድህን ታሪክ ሰራ!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar