www.maledatimes.com ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ ተድላ ጌትነት ጀርመን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ ተድላ ጌትነት ጀርመን

By   /   February 23, 2014  /   Comments Off on ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ ተድላ ጌትነት ጀርመን

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 30 Second

አርብ የካቲት 14ቀን 2006ዓ/ም በተላለፈው የ ኢትዩጵያ ህዝብ አይንና ጀሮ የሆነው ኢሳት እዲዘጋ ወያኔወች ፈረንሳይ ለሚገኘው የሳተላይት ድርጅት መጠየቃቸውን አሰምቶናል በዜናው ደንግጫለሁ አሁንስ የወያኔ መንግስት አበዛው በ ኢትዩጵያውስጥ በርካታ የዜና ማሰራጫ መስሪያ ቤቶች አሉት የቁጥር መብዛት ሳይሆን የሚያስፈልገው ጥራት ነው ለመጥቀስ ያህል ኢትቪ ፤ፋና፤ኤፍኤም፤ኢትዩጵያሬድዩ፤ስማቸው ያማረ አሉት ግን ዘወትር ውሸት የሚደሰኮርባቸው አንድም ቀን እውነት ተላልፎባቸው አያውቅም  የ ኢትዩጵያ ህዝብ ምንም አይነት ወቅታዊ መረጃ በማያገኚበት ወቅት አንድለናቱ የሆነና ያለን ቢኖር መቸ ስአቱ ደርሶልን እያልን በጉጉት የምንጠብቀው እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳለት የ ኢትዩጵይውያን አይንና ጀሮ የሆነውን አንዲዘጋ አምባገነኖቹ ወያኔወች መጠየቃቸው እጅግ ያሳዝናል ከማሳዘንም አልፎ ኢትዩጵያውያንን የሚያናድድ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ነው ለነገሩ እኮ በወያኔወች ከተደፈርን ቆየን

ከተዘጋ ይልቅ ኢሳት ሳይሆን ምንም የማይጠቅመውና መስማት የማይችለው የውሸት መፈልፈያው የሆኑትን በሀገር ቤት ያሉትን የዜና ማሰራጫወች እንጂ  ኢሳትን አይደለም

እኔ ለ ኢትዩጵያ ህዝብ እንኳን ደስአያለን እላለሁ ምክንያቱም በ አንድ ኢሳትሬድዩና ቴሌቨዝን ጣቢያ ወያኔ ይህን ያህል ከተንቦቀቦቀ ተጠንክረን 1ና2 ተጨማሪ ቢከፈት እኮ ወያኔ በፕሮፖጋንዳ የሚፈርስ ድርጅት መሆኑን እያሳየ ያለ ነው ለዚህም መድሀኒቱ በ ኢትዩጵያውያን እጅ ነው እሱም መስማት ብቻ ሳይሆን ኢሳት ከዚህ በበለጠ ተጠንክሮ እዲቀጥል ማድረግ የ እኛ በስደት የምንገኚ ኢትዩጵያውያን ነን ይህ መልእክት የስርአቱን ደጋፊወችንም ይጨምራል ለምን የምትሰሙት ሌላ እውነተኛ ዜና ስለማታገኙ መደጎም አለባችሁ

ወያኔ ባሁኑ ጊዜ መያዣ መጨበጫ ያጣ አቅማዳው የተቀደደ ያህል ነው እየተንጠባጠቡ ነው ያሉት የሚያደርገውን አጣ አሁን ደግሞ በ ኢሳትና ባንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦች ጋዜጠኞች የግል ፋይል ላይ የኮሚፒዩተር ቫይረስ መላክ ጀምሮል ግን ኢሳት ከወያኔ ቀድሞ በምሁራን የተደራጀ በመሆኑ ከ4ኪሎ ከወያኔ የሚተኮሰውን የቫይረስ ሚሳኤል ከሀገሩ ሰይወጣ በጸረቫይረስ እስከድሚሳኤል እዲመታ ተደርጎ እዛው መከላከያ ሚኒስቴርና አካባቢው ፍንጥርታሪው በካድሬወች ሶፍትዌር ላይ እዲወድቅ ተደርጎል

ባሁኑ ጊዜ ወያኔወች ካወቁበት ከ ኢሳት ብዙ ጥሩ ጥሩ ሞያወችን መቅሰም ይችላሉ ደግሞም እያሰተማራቸው ነው ኢሳት ለማንም አይወግንም አያዳላም የሚወግነው የተቋቋመው ለሚጨቆኑ ለሚፈናቀሉ ለሚታሰሩት ለሚገደሉት ንጹሀን ዜጎች ድምጽ የሚሰማበት እንጂ የማንም አይደለም የግል ነው ከተባሉ ኢትቪ፤ፋና፤ኤፍኤም፤ኢ/ሬድዩ፤ያማራክልል፤የደቡብ ክልል፤የ ኦሮሚያ ክልል፤የትግራይ ክልል፤የ አፋር ክልል፤የሱማሌ ክልል፤የ አዲስአበባ ክልል ጣቢያወች የ አንድን ድርጅት ድምጽ ብቻ የሚዘምሩት  ተቃዋሚወች በምንም መልኩ ለ ኢትዩጵያ ህዝብ በደላቸውን ሀሳባቸው የማይገልጹበት በመንገድ ሲያልፉ ካልሆነና ቀና ብለው ማየት የማይፈቀድበት ጣቢያ እንጂ ኢሳትን አይመለከትም ከገለልተኚነቱ የተነሳ የወያኔ  ባለስልጣናትን ደውሎ መረጃ ሲጠይቅ ገና ከ ኢሳት ነው ሲባሉ ይንቀጠቀጣሉ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ አይሰጡም ግን ሁሉም ማታ ወደዱም ጠሉም ቤታቸውን ዘግተው ያደምጡታል በዘገባውም ይረካሉ ታዲያ በ11 ጣቢያወች እውነት ሳይነገር ቀርቶ በ እኛው የ3 አመት ታዳጊው በ ኢሳት እውነቱ ሲገለጥ ምን አስደነገጣቸው ኢሳት የሚዘግበው እጅግ ጥቂቱን ነው እንጂ የወያኔን ጉድ ተዘግቦ አያልቅም ሰለዚህ 11ዱ ውሸታሞች በ1ዱ ኢሳት ተሸንፈዋል በቀጣይም ይሸነፋሉ

ወያኔ የሚለው ቢያጣ ኢሳት የግንቦት 7 ነው ይላል አይደለም እንጂ ከሆነም እሰየው ይህም የሚያሳየው ወያኔ ግንቦት 7 አብዝቶ ይፈራዋል ማለት ነው እውነት ያስፈራል ግንቦት 7 የ እራሱ ድምጽ አለው ኢሳት ግን አሁንም በድጋሚ የማንም አይደለም የጭቁን ህዝቦች የብሶት ድምጽ ለ ኢትዩጵያውያን ያለ አድላዊነት የሚያስተላልፍ ነው ኢሳት የተቋቋመው በዜጎች ነው እንደ ኢትቪ በመንገስት አይደጎምም ኢሳት አይዋሽም መረጃ ቆርጦ አይቀጥልም የሀይማኖት የብሔር ልዩነት አያደርግም የሚመራው በካድሬ ሳይሆን በምሁራን ነው ኢሳት አሁንም በርታ አይናችን ድምጻችን ነው አይዘጋም ከ1 በላይ ያድጋል ይመነደጋል ኢሳት የ እኔ ነው ከተዘጋ የውሸት መፈልፈያው ኢትቪ ይዘጋ ጥርቅም ብሎ ይዘጋ አይጠቅምም በመጨረሻም ኢሳት የ ኢትዩጵያውያን የግል ንብረት ነው የ እኔ ነው አሁንም የ እኔ ነው እንበላቸው

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 23, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 23, 2014 @ 9:51 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar