www.maledatimes.com ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን! በዳዊት መላኩ( ከጀርመን) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን! በዳዊት መላኩ( ከጀርመን)

By   /   February 23, 2014  /   Comments Off on ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን! በዳዊት መላኩ( ከጀርመን)

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 24 Second

            የሰው ልጅ ካመረረ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ማሰብ አይችልም፡፡ለነፍሱም ፈጽሞ አይሳሳም፡፡ወቅቱ 1998 ዓ.ም ነው፡፡የ97 ሰባቱን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ ስሙን  ለጊዜው የማላስታውሰውን ወጣት ሁኔታ ላካፍላችሁ፡፡በእለቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ረባሻ ነበር፡፡በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብጥብጡ ተዛምቱዋል፡፡ቀደም ብሎ ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዳይገቡ ስጋት ተፈጥሩዋል፡፡ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቡዋል፡፡የከተማው ወጣቶች  ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ተማሪዎችን ይዘው መውጣት ያፈልጋሉ፡፡ተማሪዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ድምጻቸውን ማስማት እና ተቃዉሞአቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡በመሀል ዙሪያውን የከበበው የፌዴራል ፖሊስ በታጠቀው መሳሪያ በማስፈራራት እየተከላከለ ያገኛል፡፡ከውጪ ወደውስጥ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ከውስጥያ ያለው ደግሞ ወደ ውጪ እንዳይወጣ በመሀል ሆነው  ይከላከላሉ፡፡ማሪዎች ያሳደባሉ፤ይጮሀሉ፡፡በዚህ መሀል በአዲሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ በኩል አንድ ረዘም ያለ  መልካማ ወጣት መሳሪያ ደግነው ለግዳይ የሚጠባበቁትን ወታደሮች ከምንም ሳይቆጥር ከወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ መጣ፡፡ወታደሮች ተመለስ! ተመለስ! ትሞታለህ እያሉ ይጮሀሉ፡፡በለው! በለው! ያባባላሉ፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ነፍሱ ፍትህ የተጠማች ወጣት ግቡ ወደ ግቢው በመምጣት ድምጹን ማስማት  በመሆኑ  የወታደሮችንም ጩኸት ሆነ የተደቀነውን መሳሪያ ከምንም አልቆጠረውም፡፡

የወጣቱን ድፍረት ላየ ሰው ሞት የሚባል ነገር ከምድር  እንደሌለው የተረዳው ይመስል ነበር፡፡ሩጫውን ቀጠለ፡፡መግደል የተካኑት ወታደሮችም በሁለት ጥይት አከታትለው መቱት፡፡እንደኛው ጥይት ትክሻውን የመታው ሲሆን ሁለተኛው ጥይት ኩላሊቱን አካባቢ ነው የመታው፡፡እንደዚህም ሁኖ ወጣቱ አሁንም እየሮጠ በሸቦ ከታጠረው የዩኒቨርሲቱው አጥር ሲደርስ አጥሩን አልፎ መግባት አልቻለም፡፡ሽቦው እጥር ስር ወደቅ፡፡በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የወደቀውን ወጣት ለማንሳት ከያሉበት  ሮሩዋጡ፡፡ የሽቦውን አጥርም ፈልቅቀው ወደ ውስጥ ይዘውት ገቡ፡፡ወደያው ወደተማሪዎች ክሊኒክ ይዘውት ሄዱ፡፡በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ  የሚሰሩት ዶ/ር ታጀበ አለሙ እና ነርስ በላይነሽ እርዳታ ቢያደርጉለትም ማትረፍ አልቻሉም፡፡ወጣቱ ህይወቱ አልፋለች፡፡ግቢው ታመሰ፡፡ለቂሶ ዋይታ እየዩ ሆነ፡፡በመሀል የምሳ ሰሀት ስለደረሰ  የተወሰኑ ተማሪዎች ምግብ እንብላ ሲሉ ሌሎች ደግሞ እሬሳ አጋድመን መብላት የለብንም ሲሉ እንብላ የሚሉት ከላይ ትእዛዝ ተላለፎላቸው ኑሮዋል እናንተ ምን ትሰራላችሁ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ስለተባሉ ጉዳዩ ወደ ብሄር ጠብ ተቀይሮ  ተማሪዎች ጎራ ለይተው ድብድብ ተጀመረ፡፡ከዚያም ግቢው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ሽንት ቤት እንኩዋን ለመውጣት የወታደሮችን ፈቃድ ተጠይቆ ነው፡፡ከዶርም እንዳይወጣ ተከለከለ፡፡ትምህርትም ተቁዋረጠ፡፡ከሳምንት በላይ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ቀስ በቀስ ተረጋጋ፡፡

እንግዲህ እንድትረዱልኝ የፈለግሁት የሰው ልጅ ትግስቱ ገበድ እንዳለው ነው፡፡ከዚያ ገደብ በላይ ማለፍ እንደማይቻል በዚህ ወጣት ታሪክ ይነግረናል፡፡፡፡ማናኛውም ነገር ገደብ (tolerance limit) አለው፡፡ለምሳሌ አንድ ላስቲክ ስንስበው እስከተወሰነ ደረጃ ይለጠጣል፡፡ከዚያ ደረጃ በኃላ ይበጠሳል፡፡ውኃ በፈሳሽነት ደረጃ የተወሰነ ሙቀትን ወይም ቅዝቃዜን ተቁቁም ይቆያል ፡፡ከዚያ ደረጃ ሲያልፍ ወይ  ይተናል ወይ ወደ በረዶነት ይለወጣል፡፡የአንድ ብረት ጥንካሬው የተወሰነ ሀይልን ለመቁዋቋም ነው፡፡የሀይል መጠኑ ሲበዛ ይጣመማል ወይም ይሰበራል፡፡የወያኔ አፈና እስከተወሰነ ደረጃ ህዝቡን ለማስጊንበስ ረድቶታል፡፡የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ያለፉትን ጊዜያት በስልጣን ተደላድሎ የሀገርን ሀብት እየዘረፈ እንዲቆያ አግዞታል፡፡ነገር ግን ዘላልም ስልጣን ላይ እንዲቆይ አያደርገውም፡፡ማናኛውም ነገር ከገደቡ ማለፍ ስለማይችል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን መሸከም የሚችለውን  ያክል ታክሻው እስኪጎብጥ ግፍ እና በደሉን ችሎ ተሸክሞትል፡፡ ላለፉት 23 አመታት ሲያነቋሽሹት ፤ሲገድሉት ፤ሲዘርፉት ፤ከመኖሪያው ፣ከቤቱ ፣ከስራው ሲያፈናቅሉት፤ ከሀገር ሲያስወጡት ፤በእምነት በጎሳ እየከፋፈሉ ሲያጫርሱት ብዙ ብዙ ታግሷቸዋል፡፡አሁን  ህዝቡ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነበት ከራሱ አሽቀንጥሮ መጣል ያፈልጋል፡፡ ዛሬ አንድነት እና መኢአድ  በጠሩት ሰልፍ የታየው የህዘብ ስሜት ምን ያክል እየገነፈለ እንደሆነ ነው፡፡ሰላማዊ ሰልፍ የሚነግረን ህዝቡ ምን ያልክ ለውጥ እንደሚፈልግ ነው፡፡እንግዲህ አወዳደቁ እንዳይከፋ ቀስ ብሎ ትንሸራቶ መውረድ ከቻሉ ለወያኔ እና ለደጋፊዎች እሰየው ነው፡፡ካለሆነ ግን ህዝቡ በግድም ቢሆን አንኮታኩቶ ጥሎ መሰባባሩ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ስለዚህ ወያኔ ወይ በራሳቸው ጊዜ ቀስ ብለው ይውረዱ ወይ  በግድ ይወገዱ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 23, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 23, 2014 @ 9:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar