www.maledatimes.com ወጣቱ በቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ(‹‹ኑሮ መኖኛል›› ሲል ተሰምቷል ጽዮን ግርማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወጣቱ በቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ(‹‹ኑሮ መኖኛል›› ሲል ተሰምቷል ጽዮን ግርማ

By   /   February 24, 2014  /   Comments Off on ወጣቱ በቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ(‹‹ኑሮ መኖኛል›› ሲል ተሰምቷል ጽዮን ግርማ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 39 Second
በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ፡፡ ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱ ፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ(እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ በመተኮስ በግምት ወደ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል፡፡ የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል፡፡ የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል፡፡ በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል፡፡አሁን በተገኘ መረጃ ‹‹ኑሮ መኖኛል›› ሲል ተሰምቷል፡፡ እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል፡፡
Tsion Girma's photo.
Tsion Girma's photo.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 24, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 24, 2014 @ 9:15 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar