www.maledatimes.com እስኪ ጠይቁልኝ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እስኪ ጠይቁልኝ

By   /   February 24, 2014  /   Comments Off on እስኪ ጠይቁልኝ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 43 Second

የ አማራው ም/ፕሬዘዳንት (ይግዛው እያሱ)
ለአቶ አለምነው መኮንን
እስኪ ጠይቁልኝ

ይፋ ተናገሩ ማንንም አትፍሩ

ለሆዳችሁ ቀርቶ ለህሌና እደሩ።

የተናገርከውን ባደባባይ ክደህ

ህሌናህን ሽጠህ ለሆድ ብቻ ካደርህ

ሰውነትህ ቀርቶ ከእንስሳም አልተሻልህ።

የምን መዘባረቅ ያሉትን መካድ ነው

ያዋጣኛል ካሉ አምኖ መቀጠል ነው።

ለምን ሰደቡና ለምን ይክዳሉ

ለካድሬ ብቻ ነው የሚነገር ቃሉ?።

ካድሬማ አንዴ ገብቷል አምኖ ተቀብሎ

ሲሰድቡ ሊሰድብ በመና ተታሎ።

ለምን ሁለተኛ ማንቋሸሽ ይማራል
በውሸት ላይ ውሸት ሁሌ ይነገራል።

ነው እንዳይክዳቸው ጉድ እንዳያወጣ

ወይስ የሚሰራ ስራ ስለታጣ።

በእርግጥ ምን ይሰራል በውሬ ያደገ ስልጣን ላይ የወጣ

የባንዳ ልጅ አሽከር ይህ መድረሻ ያጣ።

እስኪ ጠይቁልኝ ትውልድ አመጣጡን

ልዩ ሰው መሆኑን በጫማ ማደጉን።

በጫማ አለመሄድ ለእሱ ነውር ሆኖ

ህዝብን ያንቋሽሻል መሪ ሆኖ ቀርቦ።

ታሪክ ከማይረሳው ከበደል ላይ በደል

እየጨመረ እንጂ ሊሻሻል የማይችል

የጫካ ወንበዴ ያለውን አንግቦ

ሲዘምር ይኖራል ቃል በቃል ተግብሮ።

ለዚ’ህ’ እድል አንሰጥም ያለው የቁርጥ ቀን ልጅ

መግለጫ አሰምቶ ተናግሮ በአዋጅ
ቁጣውን ሊያሰማ ባህርዳር ላይ ወጥቶ

በባዶ እግሩ ሄደ ነጻነቱን መርጦ።

ህዝብን ያንቋሸሸው ለፍርድ እስከሚቀርብ

ወደ ኋላ እንዳትል ወገን ተረባረብ።
ፌብሯሪ 2014

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 24, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 24, 2014 @ 5:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar