www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂ ምላሽ ሰጠ- MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂ ምላሽ ሰጠ

By   /   February 25, 2014  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂ ምላሽ ሰጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 38 Second

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አንድነት ፓርቲ ለላከለት ማስጠንቀቂ ምላሽ መስጠቱን የአንድነት ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት በቅርቡ አንድነትን በ“አሸባሪነት” የሚፈርጅ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ ድርጅቱ ምላሽ እንዲሰጥ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለደብዳቤው ምላሽ ባለመስጠቱም አንድነት በድጋሚ የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በጻፈው ደብዳቤ በ15 ቀን ውስጥ ምላሽ ካላገኘ ወደ ክስ እንደሚሄድ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

ማስጠንቀቂያው የደረሰው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ለአንድነት ማስጠንቀቂያ ሁለት ገፅ ያለው ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምላሽ ላይ ከተወያየ በኋላ ምላሹ ትክክለኛ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ጉዳዩን ለፓርቲው የህግ ክፍል እንዲመራ መወሰኑን የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ዘጋቢ ፊልም አንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ በፓርቲው መከሰሱ አይዘነጋም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar