www.maledatimes.com እ ቃ ወ ማ ለ ሁ !! ALEX Abrehame - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እ ቃ ወ ማ ለ ሁ !! ALEX Abrehame

By   /   February 26, 2014  /   Comments Off on እ ቃ ወ ማ ለ ሁ !! ALEX Abrehame

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 45 Second

(ALEX Abrehame – በነገራችን ላይ)

የኢትዮጲያ መንግስትና ህዝብ ሊደራደርበትም ሆነ በለዘብተኝነት ሊያልፈው የማይገባ ጉዳይ ቢኖር በተመሳሳይ ፆታወች መካከል ስለሚደረግ ፆታዊ ግንኙነት ነው ! ይሄ ተራ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የትውልድን የሞራል ድንበር የሚያፈራርስ አካላዊም ስነልቦናዊም ‹በ ሽ ታ › ነው !! ይህን በሽታ ከሌሎች በሽታወች የሚለየው የድርጊቱ ፈፃሚወች በፍላጎታቸው ፈቅደውና ወደው የመሃበረሰቡን የከበረ ባህል እምነትና ማንነት በመናቅ እንስሳዊ በሆነ ድርጊት እንስሳዊ ደስታ ለማግኘት ወደራሳቸው የሚጋብዙት ፀያፍ ድርጊት በመሆኑ ነው !!

ወጣቱ ደፍሮ ይህን ነገር ሲቃወም ‹ፋራ … ያልገባው …ወግ አጥባቂ › እና ሌላም የሚያሸማቅቁ ስሞችን በመስጠት ዝም ለማስባል የሚደረጉ የማይረቡ የስነልቦና አጥሮችን በማለፍ ይህን ‹ቆሻሻ› ድርጊት ልንቃወም ይገባል ! ይህን ድርጊት ለመቃወም የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን አያስፈልግም ሰው መሆን በራሱ በቂ ምክንያት ነው !

በመሰረቱ ጤናማ ወሲብ በሰውም በፈጣሪም ፊት ‹‹ህጋዊ ጋብቻ ›› በፈፀሙ ሴትና ወንድ መካከል የሚፈፀም ድርጊት ብቻ ነው ፡፡ ዛሬ ላይ ይህን አመለካከት ተራና ቅዠት አድርገው ሊያሳዩን የሚፈልጉ በርካቶች ቢኖሩም እና ብዙወች በዚህ እውነት መኖር ስላልቻሉ ከዚህ ውጭ ቢሆኑም ብዙወች ተሳሳቱ እንጅ ስህተቱን ትክክለኛ ነገር አደረጉት ማለት አይደለም፡፡

ከጋብቻ ውጭ ወሲብ ብዙወቻችን የምንፈፅመው ትክክለኛነቱን በማመን ሳይሆን ስህተቱን በመላመዳችን ትክክል እና ቀላል ነገር መስሎን ነው ! ምክንያቱም የዘገየ ጉዳት ከቀረ ይቆጠራል አይነት እምነት አድሮብናል ! ከጋብቻ ውጭ የምንፈፅመው ማንኛውም የወሲብ ድርጊት ‹ፍቅር› ‹መፈቃቀድ› ምናምን የሚል ስያሜ ሰጥተን ብንሸፋፍነውም እውነታው ወዲህ ነው ‹‹ዝሙት›› ይባላል! ‹‹ማመንዘር›› ይባላል ፈፃሚወቹም ይህን ከፈፀምን ‹‹አመንዝራ ›› እንባላለን ! ይገባኛል እውነት ያማል ! ግን አመንዝራ እንባላለን ! ይህ ደግሞ በየትኛውም እምነት በየትኛውም ዘመናዊ ሳይንስ ከጊዚያዊ እርካታ ያለፈ ጥቅም እንደሌለው እንደውም በግልም ይውህ ማህበራዊ ሂወት ጉዳቱ እንደሚያመዝን ሚሊየን ማረጋገጫወች አሉት !

እንግዲህ በተቃራኒ ፆታ መካከል ከጋብቻ ውጭ የሚደረግ ወሲብ ይህን ያህል ፀያፍ ከሆነ ሰሞኑን በተለይ እነአሜሪካ ሽር ጉድ የሚሉለት የተመሳሳይ ፆታወች ርኩሰት ጉዳይ ለእኛ ለሰው ልጆች ምን ማለት እንደሆነ ልብ እንበል ! የትኛውም ሳይንሳዊ ቢደረደር ማንኛውም እርዳታና ስጦታ ቢግተለተል ከማንኛውም አገር ጋር ግንኙነታችን ቢበላሽ ይህን ድርጊት ልንደራደርበት ሁሉ እንደማይገባ የተለየ አቋም መያዝ ይኖርብናል ! ሲጀመር ይህ ሰበአዊም ይሁን ዲሞክራሲያዊ መብት ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም ! ይሄ በትውልድ ላይ የታወጀ ፀያፍ እና አስከፊ ጦርነት ነው ! ማንኛውም አገር ደግሞ በህዝቡ ላይ የተቃጣበትን ጥቃት ማንንም አገር ሳያስፈቅድ የመከላከል ሙሉ መብት አለው ! እርዳታ እንድሰጥህ እጅህን አጣጥፈህ ህዝብህ ሲጠፋ ተመልከት የሚል መካሪ ካለ ሌላ ጉዳይ ነው !

አንዳንድ ‹‹የተማሩ ጋጠወጦች ›› ግብረሰዶማዊነትን በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል ችግር አድርገው ‹‹ምን ያድርጉ እግዜር የሰጣቸውን ›› ሊሉንና ሊያሳምኑን ይሞክራሉ…. እስካሁን ግን በተመሳሳይ ፆታ መካከል ስለሚኖር የወሲብ ፍላጎት የተደረጉ ጥናቶች (አጥኝ ተብየወቹ ሌላ አላማ እስከሌላቸው ድረስ ) ሰወች ፈልገው በውስጣቸው የሚያሳድጉት መረን የለቀቀ የብልግና እና የሴሰኝነት ፍላጎት ብቻ እንጅ በተፈጥሮ አብሮ የሚፈጠር ስሜት እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት !

ሌላው አንገብጋቢ ጉዳይ ደግሞ አንዳንድ ‹ሃይማኖተኞች› ሳይቀሩ በአጉል ትህትናና መንፈሳዊነት ተሸፍነው ይሄንኑ ፀያፍ ድርጊት ሲያበረታቱ ይስተዋላሉ ! አንዱ እዚሁ ፌስቡክ ላይ ‹‹ከእናተ ሃፂያት የሌለበት ይውገራት ›› በሚል የቅዱስ መፅሃፍ ቅዱስ ቃል ፀያፍ ድርጊቱን ሊሸፋፍን አጣሞ ለማጣቀስ ሲሞክር መመልከቴን አስታውሳለሁ…. ሁላችንም ሃፂያተኞች ነንና ወንድም እህቶቻችን ሲጠፉ የራሳቸው ጉዳይ እንበል? …ያለን እልፍ አእላፍ ቋጠሮ የሚጎትተን አንሶ የማንንም የቅንጦትና የሴሰኝነት ርኩሰት ምድራችን ላይ ሲፈነጭ እንዳሻቸው ይሁኑ ብለን እንተወው ? ‹‹ወይንስ አንተ ማነህና ሰው ትወቅሳለህ›› እባላለሁ በሚል ስጋት አፋችንን አፍነን እንቀመጥ ?

እነዚህ ሰወች እኮ (ሰው ከተባሉ) ህፃናት ወንዶችን ሲደፍሩ ወደዚህ ርኩሰትም ሲያስገቡ የኖሩ አሁንም የሚሞክሩ የሰው ልጅ ሁሉ ጠላቶች ናቸው የሰላማዊ ኑሮ ነቀርሳወች ናቸው ….ድሮ በጨለማ መንገድ የሚሄድ ወንድ እዘረፋለሁ ብሎ ነበረ የሚፈራው ዛሬ እኮ ‹‹እደፈራለሁ ›› ብሎ በአገሩ ላይ እንዲፈራ እንዲሸማቀቅ ለማድረግ የተነሱ ጉዶች ናቸው ! ወጣት ሁነን ዛሬ በግዴለሽነት ብንደነፋ በትቂት አመታት ውስጥ እንወልዳለን ልጆች ይኖሩናል ‹‹ልጅህ ተደፍሯልና ሆስፒታል ድረስ ›› ስትባል ያኔ ከእናተ ሃፂያት የሌለበት ምናምን አትልም !

አንተን እራስህን አንዱ ወጠምሻ መንገድ ላይ አስቁሞ ‹‹አፍቅሬሃለሁና እሽ ካላልከኝ ወየውልህ ›› ብሎ እጅህን የማይጠመዝዝበት ምክንያ የለም ፡፡ ጉዳየን ፈፅምልኝ ያልከው ባለጊዜ ዛሬ እህትህን ፍቅረኛህን እንደሚጠይቀው ነገ አንተን ወደአልጋ የማይጎትትበት ምክንያት የለም የዛሬ ቸልተኝነትህን ነገ ላይ ቁመህ ካየኸው ውጤቱ ይሄው ነው ! እንደዛሬው ጓዳ ለጓዳ ብቻ አንገታቸውን ደፍተው የሚኖሩ እንዳይመስልህ ! ይሄ ነገር በወንዱ ብቻ እንዳይመስልህ ነገ ሚስትህ ከሴት ጓደኛዋ ጋር ልደር ብትልህ መፍራት እንደማትጀምር እንዴት ርግጠኛ ትሆናለህ ! ዛሬ ላይ አይመለከተኝም የምትለው ጉዳይ ነገ ጡንጫው ፈርጥሞ ቁልቁል እየተመለከተህ ታገኘዋለህ !

የሃይማኖት አባቶችም ብትሆኑ ዘመን ካመጣው አስተሳሰብ ጋር ትምህርታችሁን አታስተካክሉ የፈጣሪን ቃል እንደወረደ አስተምሩ !! የሚፀየፈውን ፀያፍ በሉ የሚያመሰግነውን ቅዱስ !! ስልጣናችሁም ይሄው ብቻ ነው ! የእናተ በማይሆን ነገር መለሳለስ ትርፉ የፈጣሪን ቁጣ በምድራችን ላይ መቀስቀስ ነው ! ዛሬ በብድር በስጦታና በእርዳታ ድጋፍ የሚያደርጉልን አገራት የሚራወጡት በውለታቸው ተሸብበን ፀያፍ ድርጊታቸውን ምድራችን ላይ ይደግሙት ዘንድ እንድንፈቅድ ነው !

ኤች አይ ቪ የፈጀን በነማን ጦስ ነበር ? እች አገር ስንት አመት ወደኋላ ተጎተተች ?ስንት ትውልድ ጠፋ ? በእኛ መጥፎ የወሲብ ባህሪ ቢስፋፋም መነሻወቹ ግን እኛ አልነበርንም ! አሁንም የከፋው ነገር ከፊታችን ተጋርጧል ! ፈረንጅ ያደረገው ነገር ሁሉ ፅድቅ በሚመስለው ወጣት ተከበን…. እግሩ አገራችን ላይ ያረፈ ክፋት ሁሉ አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት ባህላችን እየሆነ በዚህ ነገር ላይ መለሳለስ ትርፉ እች አገር ዳግም እንዳትነሳ አድርጎ ማፈራረስ ነው ! የአገር ድንበር በትውልድ ይከበራል የፈራረሰ የትውልድ ሞራል የባልና የእምነት ድንበር ግን ዘላለም እንደፈራረሰ ይኖራል !!

ግብረ ሰዶም ቆ ሻ ሻ ድርጊት ነው !! በምድራችን ላይ መቸም ይሁን በምንም ሁኔታ መፈፀም የለበትም! መንግስት ከሽብርተኝነት በላይ አገርን ከሚያፈራርስ ህዝብን ከሚፈጅ ማንኛውም አደገኛ ድርጊት በላይ በቁጥር አንድ አደጋ ሊፈርጀውና ጠንካራና ተፈፃሚ ህግ ሊያወጣበትም ይገባል !! ጎን ለጎንም ይህን ርኩሰት እንደመልካም ነገር አይተው በዙሪያው የሚያንዣብቡ ታዳጊወችን ስለዚህ አስፀያፊ ጉዳይ አስከፊ ችግርነት የማስተማር ስራ ወሳኝ ጉዳይ ነው! ይህም መንግስትን ትውልድን በመታደግ ረገድ ስሙን ለዘላለም ሲስጠራው ይኖራል ! በመጨረሻም ያደጉት አገራት የእውነት ስለዴሞክራሲም ይሁን ስለሰው ልጆች ሰበአዊ መብት የሚቆረቆሩ ከሆነ በአገራችንም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገራት የተጣሱ በርካታ የዴሞክራሲ መርሆች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ !

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 26, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 26, 2014 @ 4:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar