www.maledatimes.com ግፍ መሸከም ይብቃን ( በይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ግፍ መሸከም ይብቃን ( በ ይግዛው እያሱ)

By   /   February 27, 2014  /   Comments Off on ግፍ መሸከም ይብቃን ( በ ይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 58 Second

ሀዘንህ አይብዛ ወገን ደስ ይበልህ
ተስፋን ሰንቅ ዛሬ ዓላማ ይኑርህ።
አቅደህ ተራመድ ግብህ እንዲሳካ
ያለፈውን ትተህ በመጪው ተመካ።
እንዲሁ አይኖርም እኛም አንቀጥልም
ተባብረን ከሰራን ውጤት አይርቀንም።
ወይ ነፃነት የለን ወይ ደልቶን አልኖርን
ተንበርክከን ኖረን አጎንብሰን ሞትን።
ቆም ብለን እናስብ ፍጹም አናመንታ
ምን እስኪፈጠር ነው ይሕ ሁሉ ዝምታ።
አኗኗሪ ሆነን መኖር እንኳ ሳንችል
ስንት ዘመን አሳለፍን ቀን ያልፋል እያልን።
ቀን ብቻ መች ሆነ አላፊና ጠፊ
ወገን አለቀ እንጂ በኑሮ ሽራፊ።
ባልተሟላ ኑሮ የመንገድ ጋጋታ
በማናርፍበት ቤት ተይዞ ጨዋታ
አድገናል ይሉናል ጥዋትና ማታ።
ይህ ሚፎክሩበት የድንጋይ ድርደራ
ችግርን አይፈታም የህዝብን መከራ።
ድንጋይ በድንጋይ ላይ በድንጋይ ተሰርቶ
የህዝብ ሀብት ባልሆነው ወያኔ ተኩራርቶ
በመሳሪያ አፈሙዝ ህዝብን አስፈራርቶ
ይፎክርልናል የትእቢት ቀረርቶ።

ሀዘንህ አይብዛ ወገን ደስ ይበልህ
ተስፋን ሰንቅ ዛሬ ዓላማ ይኑርህ።
መነሻህን አውቀህ መድረሻህን ተንብይ
ግፍ መሸክም ይብቃህ አትሁን አድር ብይ።
ለነጻነተህ ቁም ቀና እንዲል አንገትህ
ብታጎነብስም አይቀርም መሞትህ።
ቤትህ ቀየህ ሲፈርስ ዝም ብለህ አይተኸው
ማንነትህ ሲሻር ባትከላከለው
መሬትህ ተሽጦ አገር ልታጣ ነው።
ዛሬ የቆምክባት መሬቷን ሳታጣ
ነገ ለመሰደድ ከቤትህ ሳትወጣ
በምትችለው ሁሉ ባለህ ተረባርበህ
ለልጅ ታሪክ አቆይ አንተ መስዋት ሆነህ።
ይህ የኔ ቃል ነው እዚሕ የሰፈረው
በሁሉም ውስጥ ያለ ግፍ በተሸከመው።

ሀዘንህ አይብዛ ወገን ደስ ይበልህ
ተስፋን ሰንቅ ዛሬ ዓላማ ይኑርህ።
እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው
ማለቱ ይብቃና እኛም እናግዛው።
ሁሌም የምንኖረው ባምላክ ድጋፍ እንጅ
መች በወያኔ ነው በዚህ አገር ክጅ።
አገሩን በመክዳት ድንበሩን የሚሸጥ
እድሜውን ለማርዘም የሰው ደም የሚመጥ
ለአንድነት ያልቆመ የአገር ነቀርሳ በጋራ ለመጣል ቆርጠን እንነሳ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 27, 2014 @ 10:13 am
  • Filed Under: Ethiopia, POEMS
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar