www.maledatimes.com “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !”ነቢዩ ሲራክ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !”ነቢዩ ሲራክ

By   /   February 27, 2014  /   Comments Off on “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !”ነቢዩ ሲራክ

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 3 Second

የማለዳ ወግ … ጉዞ ወደ ዓድዋ !

    የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ብቻ ነው አልልም ።  ዓድዋ ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት ምንጭ ስለመሆኑ የታሪክ መዛግብትም ሆኑ ባእዳን የታሪክ ልሂቃን ሳይቀር የሚመሰክሩት ሃቅ ነውና ። በዓድዋ የጥቁር ዘር አትንኩኝ ባይበት ሲረጋገጥ የጥቁር ዘር ለነጻነቱ ቀናኢ መሆኑን ለአለም የታየበት መሆኑም የሚታበል አይደለም  !

    የዚህ ታላቅ ድል ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናችን አልፋና ኦሜጋ ሲያኮራን ይኖራል።  የዓድዋን ታሪካዊ የድል በአል በመላ አለም በሚንገኝ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አመት በመጣ ባሰለሰ ቁጥር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በአሉ ሃበሾች በነጭ እብሪተኞች ላይ የተቀዳጀነው የዓድዋ ድል ነውና ቀጣዩ ትውልድ ታሪኩን አክብሮና ጠብቆ  እንዲኖር እገዛ ስለሚያደርግ የበአሉ መከበር ታሪክን ከማወራረስ አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ። የዘንድሮው 118ኛ የዓድዋ ድል በአል ለማክበር በአገርና በቀረው አለም በምንገኝ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰፋ ያለ የመታሰቢያ ማዘከሪያ ዝግጅትን በማድረግ ላይ መሆናችን እውነት ነው ።

      በአረቡ አለም በተለይም ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአሉን አድምቀን እንድናስበው ስለማይደረግ እድሜ ለቴክኖሎጅ በአሉን በማህበራዊ ገጾቻችን ለማክበር ተፍ ተፍ በማለት ላይ እንገኛለን። በሪያድ ኢንባሲና በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎቻችን የዓድዋን ታላቅ ሃገር አቀፍ በአል በአዳራሾቻቸው ተሰባስበን እንድናከብረው ቢያደርጉን ምንኛ በኮራን ነበር ! ዳሩ ግና  የኢንባሲና የቆንስል ሃላፊዎቻችን እንዲህ አስበው አናውቃቸውም እና  እንደ ልማዳችን እናዝናለን ። ቢያንስ የገዥው ፖለቲካ ድርጅቶች እና በጎጥ ለተመሰረቱት የልማት ማህብራት የሚሰጡትን ያህል ለቱባው ኢትዮጵያዊነት ክብር ሰጥተው ዓድዋን ሻማ አብርተን  የጀግኖቻችን ታሪክ ላንድ አፍታ እያነሳሳን እንድናዘክር ፣ እንድንማማርና ጀግኖቻችን እንድናመሰግን አያደርጉም ።  እውነቱ ይህ ሆነና የስደት ፍሬ የሆኑ በአረብ ሃገር ተወልደው የሚያድጉ ልጆቻችን በሚማሩበት እየሰበሰቡ የብሔር ብሔረሰብ የድርጅት በአላትን ሲያከብሩ ማድምቂያ ያደርጓቸዋል። የዓድዋንና የመሳሰሉ ሃገር አቀፍ በአላት ሲከበር ግን ትምህርት ከመዝጋት ባለፈ ስለበአሉ ምንነት ገላጭ የሆነ ትምህርት በብጣቂ ወረቀት ግንዛቤ እንዲሰጠቸው አይደረግም። ዛሬ በአረቡ አለም የተወለዱ ታዳጊዎች ሊኮሩበት ከሚገባው የሃገራቸው ታሪክ ይልቅ ስላደጉበት አገር በአላት የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው እየገፋናቸው በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ። የበአሉን አከባበር ካነሳሁ አይቀር ቀልቤን ወደሳበው እና መነሻየ ወደ ሆነው  በስድስት ትንታግ ጎልማሶች እየተደረገ ስላለው የዓድዋ ታሪካዊ የእግር ጉዞ ላምራ …

      በፍላጎት የተሰባሰቡ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስድስት ጎልማሶች በአሉን በክብር ለማዘከር ወደ ዓድዋ በእግራቸው ተጉዘዋል…

1ኛ / ጋዜጠኛና የፊልም ባላሙያው ብርሃኔ ንጉሴ
2ኛ/ ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ዓለሙ ከኢትዮጲካሊንክ
3ኛ/  መሐመድ ካሣ (ኬር ኤቨንትስ ኤንድ ኮሙኒኬሽን – የባህልና የኪነ ጥበብ ፕሮሞተር)
4ኛ/ ሙሉጌታ መገርሣ (ደብሊው) (የፊልም ባለሙያ)
5ኛ/ አለምዘውድ ካሳሁን (የካሜራ ባለሙያ)
6ኛ/ ያሬድ ሹመቴ (የፊልም ባለሙያ)

ጎልማሶች ወርቅ ጊዜያቸውን ሰውተው በአንድ ውለው በአንድ አስበው ለታሪካዊው 118 የዓድዋ ድል መታሰቢያ ልዩ ዝግጅት አቅደው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴው አመሩ።  ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 በግምት ወደ 40 ቀን የሚወስደውን ረጅሙን ወደ ዓድዋ የሚያደርጉትን የ1,006 ኪሎ ሜትር ርቀት ጉዞ ከአዲስ አበባ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አደባባይ በአንድ እርምጃ ጀምረው ዛሬ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበዋል።

    ታላቁን የዓድዋ ድል ለማዘከር “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም” የሚል መፈክርን ቀዳሚ መመሪያ አድርገው  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድግበው እያውለበለቡ ይህን ጉዞ ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋና አላማ 118ኛ የዓድዋን ድል ቀን በዓድዋ ለማዘከር እንደሆነም ሰምተናል። ትንታግ ጎልማሳ ወንድሞቻችን በትጋት የጀመሩትን ጉዞ ሊያጠናቅቁ የቀራቸው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው።

    አራዳ ጊዮርጊስ ከአጤ ምኒልክ አደባባይ የተጀመረውን ጉዞውን ቀደምት አባቶቻችን የዓድዋ ድል ከ118 አመት ለማስገኘት እየተሰባሰቡ የዘመቱባቸውን ከተሞች ተከትሎ የሚከወን መሆኑ ታሪካዊውን የሃገር ወዳድ ወንድሞች ጉዞ ልዩ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው በማውለብለብ ጉዟቸውነወ በመከወን ላይ የሚገኙት ተጓዦች በየደረሱባቸው ታሪካዊ ከተሞች ሞቅና ደመቅ ያለ አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን ያን ሰሞን ተጓዦች መረጃውን አድርሰውናል።

     እኒህ የብርታት ተምሳሌት የሚሆኑን ትንታግ ወንድም ተጓዦች ቃል አቀባይ ተጓዦች ያን ሰሞን  ኮንቦልቻ እንደደረሱ በሰጠው ማብራሪያ እንዲህ በማለት ያስረዳል “…  ማለዳ በአድዋ ድልድይ ተሻገሩ፡፡ ለገጣፎ – ለገዳዲ – ሰንዳፋ – በኪ – አለልቱ – ፍቼ – ሐሙስ ገበያ – ሸኖ – ሰምቦ – ጥያኪ – ጫጫ – ጠባሴ – ጅሁር መገንጠያ – ደብረ ብርሃን – አንኮበር መገንጠያ – ቀይት – ጉዳ በረት – ጣርማ በር – ደብረ ሲና – ጭራ ሜዳ – አስፋቸው – ሸዋ ሮቢት – አጣዬ – ከሚሴ – ሃርቡ – ፎንተኒና – አልፈው ኮምቦልቻ ደርሰዋል፡፡ በመንገድ ላይ አጤ ምኒልክ እና ሠራዊቱ (የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች) ለአገርና ለሕዝብ ዘብ የቆሙ ወታደሮች የደረሰባቸውን መከራ ይዘክራሉ፡፡ የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ድል ነው፡፡ በዚህ ድል አፍሪካዊያን ይኮራሉ፡፡ የዚህ ድል ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በዚህ የታሪክ ሰንሰለት ተምሳሌቱን ዳግም ለዓለም ለማወጅ ታሪካዊ ጉዞ እያደረጉ ናቸው፡፡ ተጓዦቹ – ሰንቃጣ ወይንም (ስንቅ አጣን) ሲደርሱ የታሪካዊ ጉዞ ፈተና ይቀምሳሉ፡፡ (ይራባሉ – ይጠማሉ፡፡) የስድስቱ ተጓዦች ለመራብ – ለመጠማት መዘጋጀታቸው ልዪ የሚያደርገው ስንቅ እያላቸው መሆኑ ነው፡፡ ስድስቱ የእግር ተጓዦች የካቲት 23 ቀን 2006á‹“.ም አድዋ ይደርሳሉ፡፡ 118ኛ የዓድዋ ድልን በአድዋ ተራራ ያከብራሉ፡፡ በርካታ ታሪካዊ መዘክሮችን አዘጋጅተዋል፡፡ ለምሳሌ ሶሎዳ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ በክብር ለማቆም አቅደዋል፡፡ የአድዋ ክብረ በዓል ላይ የበዓሉን ማብሰሪያም መድፍ ይተኮሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጓዦቹ – ‹‹በየደረስንበት የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገልን ነው፡፡ !›› ብሏል ! ጉዞው አሁንም ቀጥሏል … እኒህ ወንድሞች ትጋትና ቁርጠኝነትን በትጋት እና በተግባት ለማሳየት ፣ የአባቶቻችን ታሪካዊ ተጋድሎ በክብር ለማስታወስ “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !” ሲሉ የእግር ጉዞ አኩርቶኛል!  በእርግጥም እኒህ ወንድሞቻችን ለአባቶች ተጋድሎ ተድበስብሶ እንዳይቀር እና አንጸባራቂውን ድል ለቀጣዩ ትውልድ በክብር ለማውረስ ስራ በመስራታቸው ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል!  ይህን መሰል ፋና ወጊ ታሪክ ለመስራት መታደል በእርግጥም መታደል ነው !

አዎ !  እኔም በአድዋ ድል እኮራለሁና  “ዓድዋ – ይከበር፣ ይዘከር – ለዘላለም !”  እላለሁ  !
የዓድዋን ድል በክብር እዘክራለሁ  ! እናዘክራለን  !

ክብር ለደሙ ለቆሰሉና በክብር ለሞቱ ሰማዕታት ! ክብር ለጀግኖቻች አርበኞቻችን  !

ከሰብር ለእምየ ምኒሊክ ! ክብር ለእቴጌ ጣይቱ !

ክብር ለኢትዮጵያ !

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 27, 2014 @ 3:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar