www.maledatimes.com በጀቱን ኢሕኣዴግ ( የኢትዮጵያ መንግስት) ይሸፍነዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጀቱን ኢሕኣዴግ ( የኢትዮጵያ መንግስት) ይሸፍነዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ

By   /   February 28, 2014  /   Comments Off on በጀቱን ኢሕኣዴግ ( የኢትዮጵያ መንግስት) ይሸፍነዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 55 Second

በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል በተደረገው የድንበር ጉዳይ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ወደግዛቷ 62.6 ኪሎ ሜትር ዘልቆ የሚገባ እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚያፈናቅለውን የመሬት ርክክብ በምስጢር መፈጸሟን ተከትሎ በዚሁ ሱዳን በምትረከበው ድንበር አከባቢ የመሬት ጥያቄ የሚይነሱ የሚያምጹ እና የሚሸፍቱ ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ወያኔ የሱዳን ሰራዊት እና የራሱ ምልምል የሆኑ ትውልዳቸው ሱዳን የሆነ ኢትዮጵይውያንን አሰልጥኖ ህገወጦችን መቆጣጠር በሚል ሽፋን የድንበር አከባቢ ተወላጆችን ለማስመታት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል::

ይህ ይቋቋማል የተባለው የጋራ የጦር ሰራዊት ህገወጥ ብሎ የፈረጃቸውን እና የመሬት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የአማራ ገበሬዎች ለመምታት የታቀደ እና እንዲሁም ይህንን ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አማጺያን ሰርገው ይገባሉ በሚል ስጋት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳን ወያኔ ወደ ካርቱም ልኮ ሚኒስትሩ ሳምንት ካርቱም ሰንብተው ወደ ሃገር ቤት መጥተዋል::

በሰሜን ጎንደር በምእራብ ጎጃም በቤንሻንጉል እና በጋምቤላ አከባቢዎች ወያኔ ፋታ የማይሰጡ የለውጥ ጥያቄ ያላቸው ታጣቂ አማጽያን ጦር ወድረው እየተኮሱበት መሆኑን ያማረረው ኢሕኣዴግ የሱዳንን መንግስት በመማጸን የጋራ የጦር ሰራዊት በማቋቋም በጀቱን ኢሕኣዴግ ከህዝብ ቀረጥ ከሚከፍልበት ገንዘብ የሚሸፍን መሆኑ ተረጋግጧል::ምንሊክ ሳልሳዊ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 28, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 28, 2014 @ 11:36 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar