www.maledatimes.com በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች የካድሬዎች መመልመያ እንደሆነ ተጠቆመ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች የካድሬዎች መመልመያ እንደሆነ ተጠቆመ

By   /   February 28, 2014  /   Comments Off on በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች የካድሬዎች መመልመያ እንደሆነ ተጠቆመ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 47 Second

ዩኒቨርስቲዎች (ጥራት ያለው ሳይንሳዊ ስልጠና የሚሰጥባቸው የትምህርት ማእከላት ሳይሆኑ) ታማኝ ካድሬዎች የሚመረቱባቸው ካምፖች ‘የሆኑበት ሁኔታ ነው ያለው’።

ተማሪዎች ለስርዓቱ ታማኝ ካድሬዎች ሁነው ካገለገሉ ሲመረቁ ምርጥ የተባለ ሥራ እንደሚያገኙ ቃል ይገባላቸዋል። እንደውጤቱም ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ይዘው ለመመረቅ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ታማኝ ካድሬ መሆን ይቀላቸዋል።
ግን በመንግስት መስርያቤት ለመቀጠር የሀገር ዜጋ መሆን በቂ ነው። የሁሉም ሰው መብት ነው። ለማወዳደር ከተፈለገ ደግሞ (የፖለቲካ ታማኝነት ሳይሆን) የትምህርት ማስረጃና ብቃት እንደመስፈርት ሊወሰድ ይችላል።
የመንግስት መስርያቤት በፖለቲካ ኣመለካከት፣ ዝምድና (ባጠቃላይ በሙስና) እየተያዙ ብዙ (በስርዓቱ ደህና ሰው የሌላቸው የዩኒቨርስቲ ሙርቃን) ስራ ኣጥተው እየተንገላቱ ይገኛሉ። ኣብዛኛው የስራ ኣጥነት ሁኔታ በፍትሕ እጦት ምክንያት የተፈጠረ ነው።
ስራ የያዙም ቢሆኑ፡ እድገታቸው (የደመወዝ ጭማሪ ኣክሎ) የሚወሰነው በስራ ገበታቸው ባሳዩት የኣፈፃፀም ብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ኣመለካከታቸው ነው። ይህ ተግባር ፍትሕ ያጎድላል፤ ዜጎችም ይጎዳል። ሲል የገለጸው የመቀሌው ዩኒቨርስቲ መምህር እና የአረና የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባል የሆነው አብርሃ ደስታ ነው ። ይኅንን  አያይዞ ሲጠቁምፖለቲካዊ ሙስና በሃገሪቱ ላይ መንሰራፋቱን እና መቆም እንደሚገባው ንጹህ ዜጋዎችን ማፍራት ስንችል ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ ሊያጎበድዱ የሚችሉ ፣ሃገራዊ ግዴታም ሆነ ፍቅር የማኖራቸውን እና ሌሎችን የፖለቲካ አቅጣጫ እንዳያዩ የሚያደርጉ እቅድ ይዞ እንደሚንቀሳቀሱ ጠቁሞአል ። ቀድሞ የሃገር ወይንም የፖለቲካ ለውጥ የሚነሳው ከዩንቨርሲቲዎች በሚነሳ አተካሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ለጥቅም የተገዛ ወጣት ብቻ የሚፈለፈልበት ጉሮኖ ሆኖአል ሲል ጠቁሞአል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 28, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 28, 2014 @ 11:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar