www.maledatimes.com የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል !

By   /   March 2, 2014  /   Comments Off on የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል !

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 33 Second
* የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለወገኖቻችሁ ድረሱላቸው!
* ተጸወእኖ ፈጣሪዎችም እታድክሙን ፣ ሂዱና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ!

ሰሞኑን ከጅዳው የሽሜሲ ጊዜያዊ የእስር ማቆያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወራት በእስር ተንገላታን ሲሉ የመረረ ሮሯቸውን ገለጹልኝ ። ሮሯቸወ ሰሚ ማጣቱን አምርረው የገለጹልኝ ወገኖች ከእኔ አልፎ ተርፎ ለጀርመን ራዲዮ የዝግጅት ክፍል ሳይቀር ምሬት ሮሯቸውን ማስተላለፋቸውን ገልጸውልኛል።

ዛሬ ረፋድ ላይም በተንቀሳቃሽ ስልኬ ደውለው እጃችሁን ስጡ ተብለው በሰጡ እየደረሰባቸው ያለው መጉላላት በመክበዱ ወደ የሞት ሽረት አድርገው ቁርጡን ለማወቅ እንደሚገደዱና ይህንንም ” ለጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ለአለም ድምጻችን አሰማልን !” ሲሉ እያለቀሱ ሃሳባቸውን ሲያስረዱኝ መጭውን ለመገመት አዳጋች አልነበረም!

የግፉአኑ የአደራ ቃል አለብኝና ስልኬን እንደዘጋሁ ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ወደ ተጠባባቂው ቆንስል ጀኔራል ሸሪፍ ከይሩ ደወልኩ ። ስልካቸው ይጠራል ግን አያነሱትም! ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም … ተስፋ ሰንቄ ወደ ሌላኛዋ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩበ። እርሳቸውም አያነሱም! ደጋገምኩት ፣ መልስ ግን የለም ! የሚያዝ የሚጨበጥ ማጣት እንዴት ያማል?

ከሰአታት በኋላ እኩለ ቀን ከዚያው ከሽሜሲ ተደውሎለወኝ ስልኩን ሳነሳው የሰው ጫጫታ ፣ እሪታ ፣ አኡኡታና የጥይት ድምጽ ሰማሁ … ደዋዩን ወንድም ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? አልኩት “መረረን ፣ ድረሱልን አልን ፣ የሚሰማን አጣን ፣ እስር ቤቱን ሰብረን ወጣን !” አለኝ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰልኝ … ከዚያን ሰአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከሽሜሲ የሚደርሰኝ መረጃ ደስ አይልም ! የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአካባቢው የተገኙ ቢሆንም መፍትሄ ማምጣት ግን የቻሉ አይመስልም !

የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለመረጃ ቅርብ ሁኑ ! ወገንን ለመደገፍ ትጉ ! የወገኔን የወገናችሁን ክፉ ደግ መረጃ እንዳላቀብል ፣ አታስተላልፍ ከፖለቲካው ጋር እያገናኛችሁ ከመወንጀል እስከ ተራ አሉባልታ የምትሞጅሩኝ የምትሞግቱኝ ተሰሚነት ያላችሁ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሆይ ! አታድክሙን ! ስሙኝ ? እነሆ እየሆነ ያለውን ሂዱና ተመልከቱ ! የምትቆረቆረቆሩት ለወገኖቻችሁ ከሆነ እነሆ ድረሱላቸው !

በቃ ! ሌላ ምን ይባላል ?

ነቢዩ ሲራክ

Photo: የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል   ! 
* የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለወገኖቻችሁ ድረሱላቸው!
* ተጸወእኖ ፈጣሪዎችም እታድክሙን ፣ ሂዱና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ! 

 ሰሞኑን ከጅዳው የሽሜሲ ጊዜያዊ የእስር ማቆያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወራት በእስር ተንገላታን ሲሉ የመረረ ሮሯቸውን ገለጹልኝ ። ሮሯቸወ ሰሚ ማጣቱን አምርረው የገለጹልኝ ወገኖች ከእኔ አልፎ ተርፎ ለጀርመን ራዲዮ የዝግጅት ክፍል ሳይቀር ምሬት ሮሯቸውን ማስተላለፋቸውን ገልጸውልኛል። 

 ዛሬ ረፋድ ላይም በተንቀሳቃሽ ስልኬ ደውለው  እጃችሁን ስጡ ተብለው በሰጡ እየደረሰባቸው ያለው መጉላላት በመክበዱ ወደ የሞት ሽረት አድርገው ቁርጡን ለማወቅ እንደሚገደዱና ይህንንም " ለጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ለአለም ድምጻችን አሰማልን !" ሲሉ እያለቀሱ ሃሳባቸውን ሲያስረዱኝ መጭውን ለመገመት አዳጋች አልነበረም!  

   የግፉአኑ የአደራ ቃል አለብኝና ስልኬን እንደዘጋሁ  ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ወደ ተጠባባቂው ቆንስል ጀኔራል ሸሪፍ ከይሩ ደወልኩ ። ስልካቸው ይጠራል ግን አያነሱትም! ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም ... ተስፋ ሰንቄ ወደ ሌላኛዋ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩበ። እርሳቸውም አያነሱም!  ደጋገምኩት ፣ መልስ ግን የለም  ! የሚያዝ የሚጨበጥ ማጣት እንዴት ያማል?

   ከሰአታት በኋላ እኩለ ቀን  ከዚያው ከሽሜሲ ተደውሎለወኝ ስልኩን ሳነሳው የሰው ጫጫታ ፣ እሪታ ፣ አኡኡታና የጥይት ድምጽ ሰማሁ ... ደዋዩን ወንድም ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? አልኩት "መረረን ፣ ድረሱልን አልን ፣ የሚሰማን አጣን ፣ እስር ቤቱን ሰብረን ወጣን !"  አለኝ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰልኝ ... ከዚያን ሰአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከሽሜሲ የሚደርሰኝ መረጃ ደስ አይልም  !  የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአካባቢው የተገኙ ቢሆንም መፍትሄ ማምጣት ግን የቻሉ አይመስልም  ! 

    የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለመረጃ ቅርብ ሁኑ ! ወገንን ለመደገፍ ትጉ  ! የወገኔን የወገናችሁን ክፉ ደግ መረጃ እንዳላቀብል ፣ አታስተላልፍ ከፖለቲካው ጋር እያገናኛችሁ ከመወንጀል  እስከ ተራ አሉባልታ የምትሞጅሩኝ የምትሞግቱኝ ተሰሚነት ያላችሁ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሆይ  ! አታድክሙን  !   ስሙኝ  ? እነሆ እየሆነ ያለውን ሂዱና ተመልከቱ  !  የምትቆረቆረቆሩት ለወገኖቻችሁ ከሆነ እነሆ ድረሱላቸው  !

በቃ  !  ሌላ ምን ይባላል ?

ነቢዩ ሲራክ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 2, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 2, 2014 @ 2:58 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar