www.maledatimes.com መንግስታዊ ውሸት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መንግስታዊ ውሸት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል::

By   /   March 2, 2014  /   Comments Off on መንግስታዊ ውሸት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል::

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 37 Second

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለመቀራመት አሰፍስፈው በጥላቻ ፖለቲካ ለሚዳክሩት ሁሉ ሊሰለጥኑ እንደሚገባ ልንነግራቸው ይገባል::ካልሆነ እንደኢሕኣዴግ ያሉ የሃያላኑ ስልጡን ማፊያዎችን መጣል ከባድ ይሆናል::ጥያቄው የለውጥ ጥያቄ ነው ::ኢሕኣዴግ መስማት ከቻለ ጥያቄው ይህ ነው :: የፖለቲካ ተሃድሶ እንዳልን ሁሉ የኢኮኖሚ ተሃድሶም ያስፈልገናል::ያለውን የኢኮኖሚ እደምታ ለመገምገም ሳይሆን መጪው ጊዜ በለውጥ የታጀበ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲኖረን ለማሳሰብ ነው:: ባለፊት አመታት እያልን እንደፈረደብን ማላዘን ሳይሆን መጪውን ጊዜያት ማሰብ ካለብን ለዚህ የባከነ ትውልድ እረፍት እንሰጠዋለን::

የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ህዝብን ማእከል ያደረገ ድህነት እንዲፈጠር አድርገዋል::ሃገርን ለኪስራ ዳርገዋል::የሕወሓት ድርጅቶች በሞኖፖል የተቆጣጠሩ እና ፖለቲካው የሚያሽከረክራቸው የንግድ ድርጅቶች ለሃገር እድገት ጋሬጣ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለሙስና መስፋፋት ለስልጣን መባለግ እንዲሁም ለድህነት መንሴ ሆነው ተገኝተዋል::እነዚህ ድርጅቶች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችን ከገበያ አባረዋል::አክስረዋል በመቶሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ከሃገር አሰድደዋል::በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመንግስት አዘርፈዋል ዘርፈዋል:; በትሪሊኦኖች የሚቆጠር ገቢን መንግስትን አሳጥተውታል::ህዝብን ማእከል ያደረገ ድህነት እንዲፈጠር አድርገዋል::ሃገርን ለኪስራ ዳርገዋል::በተጭበረበር ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ ዋጋቢስ ነው::

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለመቀራመት አሰፍስፈው በጥላቻ ፖለቲካ ለሚዳክሩት ሁሉ ሊሰለጥኑ እንደሚገባ ልንነግራቸው ይገባል::ካልሆነ እንደኢሕኣዴግ ያሉ የሃያላኑ ስልጡን ማፊያዎችን መጣል ከባድ ይሆናል::የሃገራችንን ኢኮኖሚ የመሰረቱት ከብሄራዊ ጥቅማቸው አኳያ ቅጥኛ የሆኑ ኢኮኖሚስቶችን አስርጎ በማስገባት ላለፉት 35 አመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ እንዲመሰረት አድርገውን ለኪሳራ አሳልፈው ሰተውናል::ህዝቦች ባልተጠና እና በቶሎቶሎ በተዘጋጀ የኢኮኖሚ ፖሊቺ እየተመሩ የሄዱበት ጉዙ እልህ አስጨራሽ ብቻ ሳይሆን ከስኬት ይልቅ ለኑሮ ኪሳራ ዳርጓቸዋል::ይህ ደሞ ሃገሪቱን እመራዋለሁ ከሚለው መደብ የተፈጠረ ዝብርቅርቆሽ ነው::

መንግስታዊ ውሸት በራሱ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል:: የመንግስት መገናኘ ብዙሃን በተለመደ መልኩ ውሸት ሲደጋገም ውነት ይሆናል በሚል ፈሊጥ ህዝባን እያታለሉ የልተፈጠረ እና ያልተደረገ ነገር እየደሰኮሩ ሃገርን ለኪሳራ መዳረጋቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ይህ ውሸት ደሞ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይደለም ::
በተጨማሪ ሃገር በባዶ ካዝና እየተመራ ባለበት በዚህ ወቅት ከውጪው አለም የተለያዩ ብድሮችን በማምጣት 3 መጪ ትውልድ ሊከፍለው በማይችለው እዳ ውስጥ ሃገሪቷ እንድትነከር አድርገዋል::የመጣውን ብድር ህዝቦች ከድህነት እንዲላቀቁ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሃገር የኢኮኖሚ ዋልታዎች ማደግ ከማዋል ይልቅ መንገድ እና ህንጻ በመስራት ገንዘቦችን ወደ ድንጋይ እንዲለወጡ መደረጉ ያለው አስተዳደር የአገዛዝ ብልሹነት እና የመልካም አስተዳደር እጦት ያመለክታል:: ይህ ደሞ ኢኮኖሚያችን በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ እንደተገነባ ያመለክታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar