www.maledatimes.com ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና

By   /   March 4, 2014  /   Comments Off on ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 8 Second

በአንድ ማህበረሰብ ዉስጥ ያሉ እሴቶች እንደ ሰደድ እሳት ከአንዱ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በወረርሽኝ መልክ የመተላለፍ ጉልበታቸዉ አስገራሚ ነዉ:: አንዱ ሲያደርግ ያዬዉን ሌላዉ የሚደግመዉ በተበለጥኩ ስሜት ብቻ ሳይሆን ያ አሰራርና እሴት ወካይና ትክክለኛ እየመሰለዉ ጭምር ነዉ::

በተለይም ማህበረሰብ ወደ ጭለማማ ጉዞ ዉስጥ በሚገባበት ወቅት የትኛዉ የማህበረሰብ እሴት ትክክል መሆኑ ድብልቅልቅ የሚልበት ወቅት አለ:: በዚህ ወቅት ስለ ትክክለኛ ነገሮች ማዉራት ያስቸገራል::

በዚህ ወቅት በሆነ አጋጣሚ ባንድ ላይ ሰብሰብ ብለዉ የሚወያዩ ጉዋደኞችን/ቡድኖችን/ የሀሳብ ልዉዉጥ በጥንቃቄ ማድመጡ አሁን ባለዉ ማህበረሰባችን ዉስጥ የቱ እሴት ትክክል የትኛዉ እሴትስ ስህተት መሆኑን ለመለዬት በሚከብድ ሁኔታ ድብልቅልቁ መዉጣቱ ማሳያ ነዉ::

በሌብነት የከበሩ ሰዎች የሚወደሱበት: አስመሳዮች እንደ ጀግና የሚቆጠሩበት: ዘረኝነት እንደ ህጋዊ አካሄድ የሚደነቅበት: አልማጭነትና ስራ ፈትነት እንደ ስልጡን የሚቆጥረበት : ፈሪሃ እግዚአብሄር እንደ ሞኝነት የሚታይበት : ወገን እና ሃገር መዉደድ እንደ ሁዋላ ቀርነት የሚስተዋልበት: በወገን እና በሀገር ላይ መደራደር እንደ ብልጠት የሚቆጠርበት በማህበረሰባችን ዉስጥ እንደ ሰደድ እሳት መስፋፋቱን በልዩ ልዩ ሁኔታ ማስተዋል ይቻላል::

በየዘርፉ አሉታዊ እሴቶች የበላይነት የጨበጡበት ሁኔታ ጎልቶ ይስተዋላል:: በአሉታዊ እሴትና መርህ የሚጉዋዙ ሰዎች አቁዋራጭ ብልጽግና በስፋት ይስተዋላል:: እዉነትን ሙጭጭ ያሉ ሰዎች ግን ቁልቁል የሚዘቅጡበትና የሚኮሰምኑበት ሁኔታ በስፋት ረብቡዋል::

ይህ ሁኔታ በዚህ ወይም በዚያ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም:: ሌላዉ ቀርቶ በቤተ ክህነት ዉስት የክርስቶ አገልጋይ ካህን ሆኖ ለመቀጠር ሀያና አርባ ሽሕ ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አካሄድን በእግዚአብሄር ፊት የሚመላለሱ ሰዎች ብለን የምንላቸዉ ወገኖች እንደ ህጋዊ አካሄድ ሲያነሱና ሲጥሉት ማስተዋል ልብ ይሰብራል::

ለሀገር አስባለሁ ብሎ በተቃዋሚነት ከተሰለፈዉ ጎራ እስከ አገር እመራለሁ ብሎ እስከሚያጨበጭበዉ ቡድን ድረስ እንዲሁም በሀይማኖት የአለሙን ድርቀት አረሰርሰዋለሁ ብለዉ ከሚሰብኩት ሰዎች አምባ እስከ ኢአማኝነት የእዉነት መሰረት ነዉ ብለዉ እስከሚያስካኩት ቡድኖች ድረስ የዘለቀ ደዌ ነዉ::

በሁሉም ብድኖች ዉስጥ ያሉ የዋሃን : ቅኖችና እዉነተኞች ቁልቁል ሲገፉ በአሉታዊ እሴት የሚራመዱ ጨካኝና ምናምንቴዎች ግን ሽቅብ በክንፍ ይበራሉ:: ክፋቱ ታዲያ ይህ ምናምንቴ እሴት በማህበረሰባችን ዉስጥ እንደ ሰደድ እሳት ሀገሩን መዉረሩ ነዉ:: ጥመትን የሚያደርጉት በሙሉ መንገዳቸዉ ቀንቶላቸዋል:: ጉዞአቸዉ ተሳክቶላቸዋል::

በዚህ ወቅት ነዉ እንግዲህ ባለ አእምሮዉ ሰዉ እንዳለ “ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና” ማለትና በጽናት መቆም:: አዎን ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና::

የራስህን ማህበረሰባዊ ግዴታ ግን በበጎነት: በእዉነት: በእዉቀትና በፍቅር ተወጣ:: ይህ ከዲኦንሄር መርሆዎች በጣም ትንሹና አንድ ክቡር የሰዉ ልጅ ሊከተለዉ የሚገባ ነጥብ ነዉ:: ያንተ ዲኦንሄራዊ እርምጃ ማህበረሰቡን ወደ ዝቅጠት ከመዉረድ የሚታደግ አንድ ማህበረሰባዊ ካስማ ነዉና::

ጥመትን በሚያደርግና መንገዱ በቀናችለት ሰዉ አትቅና:: ከቀናህ ወደ ምናምንቴዉ እሴት ትሳብና ማህበረሰቡን የሚታደግ ካስማ ከመሆን ይልቅ በደዌ በተመታዉ እሤት አብረህ ትመታለህና::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 4, 2014 @ 2:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar